ጠ/ሚ አብይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ያበደረው 387 (ሦስት መቶ ሰማንያ ሰባት) ቢሊዮን ብር ሠረዘ፣

3

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

34et

(ክፍል አምስት) ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ )

በኢትዮጵያ መጀመሪያ የባንክና የፋይናንሻል ዘርፍ ይወድቃል፣ ቀጥሎ የብልፅግና መንግሥት ይወድቃል!
የኮነሬሉ አብይ መንግሥት በሦስት አመታት በትረ ስልጣኑ ከመጋቢት 2010 እስከ 2013ዓ/ም የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 ቢሊዮን ብር ወደ 945 ቢሊዮን ብር ደረሰ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያን ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የኦህዴድ የዘረኛና ተረኛ የግፍ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጭኖል፡፡ የብልፅግና መንግሥት ኦሮሚያን ብቻ በማልማት ለመጭው ምርጫ ለመመረጥ የፕሮጀክት የሪቨን ቆረጣ ላይ ይገኛል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው መጨረሻው ሰዓት ጥለው ቢወጡ ‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቶቹ›› በማይጠበቁበት አገር፣ የሰው ልጆች እንደ እንሰሳ በሚታረዱበት እና እንደ ከርከሮ በሚታደኑበት አገር ምርጫ ብሎ ነገር ቧልት ነው፡፡ ኮማንድ ፖስት በሰባት ክልሎች በወታደራዊ አገዛዝ ስር ህዝብ በሚሰቃይበት አገር፤ አምስት ሚሊዮን ህዝብ በተፈናቀለበት ሃገር፣ ከሃያ ሦስት ሚሊን ህዝብ አስቸኮይ የስብዓዊ ዕርዳታና ድጋፍ በመላ ሃገሪቱ በሚያስፈልግበት ወቅት፣ የኤርትራና የሱዳን መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነታችንን ጥሶ ወረራ ባካሄዱበት ሁኔታ፣ የዘር ፍጅት በአማራ፣በትግራይ ወዘተ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ፣ የፖለቲካ ግድያ በየክልሉ በሚፈፀምበት ሃገር ወዘተ ምርጫና ዴሞክራሲ ዘበት ነው፡፡ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ ያለ አገር ከምርጫ በፊት እርቅና ድርድር አስተማማኝ ሠላም ያስፈልገዋል እንላለን አለዛማ እንደ ዶሚኖ ቲዎሪ (Domino Factors & Theory) እንደ ሰንሰለት የተሳሰረው ሶሻል ፋብሪክ ማህበራዊ ትስስርና ግንኙነት ዋስትና ካጣ፣ እምነት ካጣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ ግንኙነት ተበጣጥሶ አንዱ በአንዱ ላይ እየተረባረበ ከመውደቅ ሌላ አማራጭ የለውም እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ መጀመሪያ የባንክና የፋይናንሻል ዘርፍ እየወደቀ ይገኛል ቀጥሎ የብልፅግና መንግሥት ይወድቃል! ከኢትዮጵያ ህዝብ፣ ከአፍሪካ አገራት፣ ከአሜሪካ መንግሥትና ከአውሮፓ ህብረት አገራት እህል የሚሠፈርለትና ደሞዝ የሚቆረጥለት አንድ ሃሙስ የቀረው መንግሥት ጋር አብሮ መቆም ኃጢያት ነው፣ የሉዓላዊነት ጉዳይ በማለት ህዝብ ለመሳብ ይሻሉ እርቀ ሠላም ይውር ችግራችሁን በሠላም ፍቱ በማለታቸው ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ በሃገራችን የዲፕሎማቲክ ሰዎች እጦት ያለአግባብ የተወሰኑብን ስህተቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የሠላም አስከባሪ ኃይል በመላክ ብዙ አፍሪካ አገራቶች ውስጥ ገብታ ሠላም በማስከበሮ ተመስግናለች እንጂ የሃገራቱን ሉዓላዊነት ጥሳለች ተብላ አልተወነጀለችም!!! ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ስው ይታረዳል፣ ሴቶች ይደፈራሉ፣ በጣርነት ምክንያት የተገደሉ፣ የተራቡ ሰዎችና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ህፃናቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን የጦርነቱ ሠለባ ስለሆኑ የዓለም የሰላም አስከባሪ ይግባ ቢባል ሉዓላዊነታችን እያሉ መፎከር አያዋጣም፡፡ የዓብይን መንግስት በአንድ ሰዓት ውስጥ ድዱን ያራግፉታል፡፡ የኤርትራው የኢሳያስ መንግስት ድዱ ከረገፈ ቆይቶል በዴንቸር ነው፣ ኢሳያስ ያስጥለናል የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ነው፡፡ የኢራቁን ሳዳም ሁሴን፣ የሊቢያ ጋዳፊ፣ የሱማሌ፣ የመን ወዘተ ሃገራት እጣ ፈንታ አይደርሰንም ብሎ መፎከር ማህይምነት ነው፡፡
Since 2018, he has around five million internally displaced people (2.2 million in Tigray and 2.9 million elsewhere), multiple high-profile political assassinations, ethnic cleansing in Western Tigray, more than 75,000 displaced peoples (at least 63,000 Tigrayans and 7,000 other Ethiopians in Sudan), two foreign countries (Eritrea and Sudan) occupying Ethiopian land; and 23.5 million Ethiopians estimated to be in need of urgent humanitarian support………(1)
• በ2013 ዓ/ም የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል። ከ945 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ እዳ ውስጥ 525 (አምስት መቶ ሃያ አምስት) ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቆማት ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡
• ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም፤በብልፅግና ፓርቲ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ወይም (15.73 ቢሊዮን ዶላር)
• የኮነሬሉ አብይ መንግሥት በሦስት አመታት በትረ ስልጣኑ ከመጋቢት 2010 እስከ 2013ዓ/ም የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 ቢሊዮን ብር ወደ 945 ቢሊዮን ብር ደረሰ፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት ተጨማሪ 495.3 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከብሔራዊ ባንክ፣ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡
• የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ 386.8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡ ብድሩ የተሰጠው 386.8 ቢሊዮን ብር ዕዳ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ዘርዝሮ አያስቀምጥም፡
• መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው የቀጥታ ብድር ጣሪያ በ2000 ዓ.ም. እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ፣ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ያለ ገደብ እየተበደረ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ ሥራ ጣልቃ በመግባት ትቶ መንግሥት መውሰድ የሚችለው የቀጥታ ብድር ጣሪያ ዳግም መከበር ይኖርበታል እንላለን፡፡.መንግሥት ካለበት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር ውስጥ 182 (መቶ ሰማንያ ሁለት) ቢሊዮን ብር ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ የተበደረው መሆኑ ይታወቃል፡፡ መንግሥት ያለ ገደብ ከብሔራዊ ባንክ የሚበደርበት ሥርዓት አለ ማለት፣ ውጤቱ ገንዘብ እንደማተም እንደሚቆጠር ይህም ኢኮኖሚው ያላመነጨው ተጨማሪ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲሽከረከርና የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ለዚህ ነው የአንድ ዶላር የውጭ ምንዛሪ 42.30 በባንክ ቤት ህጋዊ ምንዛሪ ሲሆን በጥቁር ገበያ ከሃምሳ እስከ ሃምሳ አምስት ብር ይመነዘራል፡፡ አይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ 65 ብር እንዲሆን ጫና በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡በሃገሪቱ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ በመገኘቶ የተነሳ የኑሮ ውድነት በፋብሪካ ሽቀጦችና የግብርና ምርቶች የዋጋ ግሽበት አስከትሎል፡፡ በሃገሪቱ በታወጀ የጦርነት ኢኮኖሚ በሰባት ክልሎች ኮማንድ ፖስት ሥር በወታደራዊ አገዛዝ ቀንበር ሥር ወድቆል፡፡
• መንግሥት ያለ ገደብ ከብሔራዊ ባንክ የሚበደርበት ሥርዓት አለ ማለት፣ ብሔራዊ ባንክ ማክሮ ኢኮኖሚውን ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አለመቻሉን እንደሚያሳይ ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
• ማዕከላዊ መንግሥት ካለበት 343.7 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ዕዳ ከፍተኛው መጠን ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር የተወሰደ፣ እንዲሁም በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (የጡረታ) ኤጀንሲዎች፣ ማለትም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህም መሠረት ማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ (343.7= 182+98.2+26.5+37) በብሔራዊ ባንክ ላይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት በህግ መወሰን ይኖርበታል ካለዛ የጡረተኞች ተቀማጭ ገንዘብ በመንግሥት ተወስዶ ጡረተኛው የሚከፈለው እንዳያጣ ያስጋል እንላለን፡፡
• ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከጥቂት ወራት በፊት ይህንኑ ሁኔታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስረዳታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ባደረጉት ንግግርም መንግሥታቸው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመውደቅ አደጋ ተጋርጦበት ነበር ማለታቸው አይዘነጋም። መንግሥት እያደረጋቸው ከሚገኙ ሪፎርሞች መካከል የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ የመፍትሄ አማራጭ መሆኑን ታውቆል፡፡›› ኮነሬል አብይ መንግሥታቸው ዋናው ተበዳሪ ሆኖ እያለ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ያልተከፈለ የተቆለለ እዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ አማራጭ ተደርጎ ተቀምጦል፡፡ የመንግሥት የትየለሌ እዳ እያለበት እየታወቀና ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ያለህግ እየመነተፈ የልማት ደርጅቶችን እዳ ወደ መንግሥት ማጠቃለል ማለት እዳቸውን መሠረዝ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
• እዳ የሚሰረዝላቸው ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ከተሰጠው ብድር ውስጥ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 (ሁለት መቶ) ቢሊዮን ብር በላይ ፣ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ብድሩን መክፈል እንደማይችል በመግለጽ፣ ይህንን ጨምሮ በአጠቃላይ 57 ቢሊዮን ብር እንዲሰረዘለት ሰሞኑን ለመንግሥት ጥያቄ እንደቀረበ ተዘግቦ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር፣ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን፣ የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ መርከብ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ ወዘተ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱት ብድር እንዲሠረዝላቸው ይጠይቃሉ ሆኖም እነዚህ መንግሥት ልማት ድርጅቶች ጊዜ ተሰጥቶቸው ሠርተው እዳቸውን ሊከፍሉ ይገባል እንጂ ሊሰረዝላቸው አይገባም እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የልማት ድርጅቶች እዳቸው ከተሰረዘ በኃላ በኢኮኖሚው የተከሰተው የዋጋ ግሽበት ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ እዳ ስረዛ ማለት ብር እንደማተም ነው!!!
• አጠቃላይ የአገሪቱ የብድር ሰነድ መረጃ እንደሚሳየው፣ ማዕከላዊ መንግሥትም ሆነ የልማት ድርጅቶቹ ያለባቸውን የንግድ ባንክ ብድር ላለፉት አምስት ዓመታት ከፍለው እንደማያወቁ፣ ነገር ግን ከ17 ቢሊዮን እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ ላለፉት ዓመታት እየከፈሉ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠውን ብድር ባለመሰብሰቡ ተጠያቂ መሆን ይገባዋል እንላለን፡፡
• ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመኖርና ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለልማት ድርጅቶች የሚሰጠው ብድር ነበር፡፡ ይህ ለልማት ድርጅቶች የተሰጠው ብድር ከባንኩ አጠቃላይ ብድር 85 በመቶ የያዘ ሲሆን፣ ብድሩ በማንኛውም ሁኔታ ሊከፈል ያልቻለ፣ በቀጣይም ቢሆን ብድሩ የመመለሱ ሁኔታ አደጋች የነበረ ነው፡፡›› ………….(2)
ይላሉ አቶ አጥናፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመኖርና ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ያስገቡት የተሰጠው ብድር ከባንኩ አጠቃላይ ብድር 85 በመቶ የያዘ መሆኑ ታላቅ ስህተት ሲሆን የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት መጠን፣ ባንኩ ከሰጠው አጠቃላይ ብድር መጠን ጋር የሚኖረው ምጣኔ ባለማገናዘብና መረዳት ተደጋጋሚ ስህተት በአቶ ባጫ ጊኒ ዘመንም ሲፈፀም እንዳላየ ተሆኖ ለብልፅግና በዘረናና በተረኛና አጨብጫቢ ባለሃብቶች ለመጥቀም ብድር በመስጠት የተደረገ የሙስና ሥራ ነው፡፡ የብልፅግና መንግስት በሦስት አመት ውስጥ ከመጋቢት 2010 እስከ 2013ዓ/ም የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 ቢሊዮን ብር ወደ 945 ቢሊዮን ብር ተመንድጎል በተበደረው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመቅረፅ የሚገነቡት ሥራዎች ሁሉ ከህወሓት ኢህአዴግ አለመማር ካልሆነ የኦሮሞ ህዝብን አይጠቅምም እንላለን፡፡ በኦህዴድ ብልፅግና ሹማምን ኮነሬል አብይ አህመድ፣ ታከለ ኡማ፣ በአዳነቸ አቤቤ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ባጫ ጊኒ፣ አባዱላ ገመዳ በተዘረፈው ገንዘብ ኦሮሚያን ለማልማት በሚል ፈሊጥ ገንዘብ ይዘርፋሉ፡፡ መሬት ይቀራመታሉ፣ ትግራይን፣ ሻሸመኔን፣ አጣዬን ያቃጥላሉ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት መጨረሻው ውድመት ነው፡፡ አብይ አህመድ አሊ ባባና አርባዎቹ ሌቦች የቁማር ጨዋታ በ2014ዓ/ም ድረስ አይቀጥልም፣ በተጭበረበረና ያለተወዳዳሪ ምርጫ ብታሸንፍም ተሸንፈሃል…….የዓለም መንግሥታት እውቅና አይሰጥህም! አሸናፊው ህዝብ ነው፡፡
‹‹ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያ በበኩላቸው፣ መንግሥት ካለበት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር ውስጥ 182 (መቶ ሰማንያ ሁለት) ቢሊዮን ብር ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ የተበደረው መሆኑ አሳሰቢ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ መንግሥታት ከብሔራዊ ባንኮቻቸው በቀጥታ መበደር የሚችል ቢሆንም፣ የብድር ጣሪያው በሕግ መወሰን እንደሚገባውና ብድሩ በተወሰደበት በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲከፈል በሕግ ካልተደረገ በስተቀር፣ ውጤቱ ገንዘብ እንደማተም እንደሚቆጠር ይህም ኢኮኖሚው ያላመነጨው ተጨማሪ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲሽከረከርና የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በተጨማሪም መንግሥት ያለ ገደብ ከብሔራዊ ባንክ የሚበደርበት ሥርዓት አለ ማለት፣ ብሔራዊ ባንክ ማክሮ ኢኮኖሚውን ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አለመቻሉን እንደሚያሳይ ባለሙያው ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው የቀጥታ ብድር ጣሪያ በ2000 ዓ.ም. እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ፣ ከብሔራዊ ባንክ ያለ ገደብ እየተበደረ መሆኑ አሁን ለሚስተዋለው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የራሱ ድርሻ ማበርከቱን አክለዋል ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እስከ አንገታቸው ድረስ በዕዳ የተዘፈቁና ተጨማሪ ካፒታል እንዲያገኙ ቢደረግ እንኳን መዳን የሚችሉ ባለመሆናቸው፣ በሽያጭ ወደ ግል ተዘዋውረው እንዲተርፉ ማድረግ ለመንግሥት የቀረው ብቸኛው አማራጭ መሆኑን፣ ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውይይት ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገልጸው ነበር፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚሸጡትም ድርጅቶች ከላይ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ የተዘፈቁ መሆናቸው ገልፆል፡፡………….. (3)
ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘው :- 25.7 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች የሚከፈል የአገር ውስጥ ዕዳ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል። ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች መከፈል፣ ያለበት ዕዳ ይህ የዕዳ መጠን ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሠልቶ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ሥሌት መሠረት የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል። ከ945 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ እዳ ውስጥ 525 (አምስት መቶ ሃያ አምስት) ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቆማት ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡
አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዕዳ
• አጠቃላይ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 30.6(ሠላሣ ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ፡-
ከአጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አጠቃላይ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 56 በመቶ ማለትም 30.6 ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ይዞል፡፡
• አጠቃላይ የመንግሥት ልማት ድርጅት ዕዳ 24.1(ሃያ አራት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ዶላር፡-
ከአጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 44 በመቶ ማለትም 24.1 ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ይዞል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት አጠቃላይ የዕዳ መጠን መግለጫ ሰነድ፣
• የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ 2.01 (ሁለት ነጥብ ዚሮ አንድ) ትሪሊየን ብር እስከ ሴፕቴምበር 2020 እኤአ መድረሱንና፣ የዕዳ መጠኑ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 50.8 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
• የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥትና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች ተበድረው ያልከፈሉት አጠቃላይ ዕዳ 54.7 (ሃምሳ አራት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ሰነዱ ያሳያል፡፡
• አጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘው 28.99 (ሃያ ስምንት ነጥብ ዘጠና ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር ሲደመር ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘው 25.7 (ሃያ አምስት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር (54.7= 28.99 +25.7)
• አጠቃላይ ዕዳ 2.005 ትሪሊየን ብር ሲሆን ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘው 1.06 ትሪሊየን ብር ሲደመር ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘው 945 (ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት) ቢሊዮን ብር (2.005= 1.06 +945)
• ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘው :- 28.99 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ከውጭ የብደር ምንጮች የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሰልቶ 1.06 ትሪሊየን ብር እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል።
ከአጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ ለውጭ አበዳሪዎች የሚከፈለው 28.99 ቢሊዮን ዶላር ወይም 1.06 ትሪሊዮን ብር ግን አለመክፈል የሚቻልበት ሁኔታ ዝግ በመሆኑ፣ የኢትየጵያ ደግሞ በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ውስጥ በመውደቁ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ የራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህንን የውጭ ዕዳ ኢትዮጵያ መክፈል እንደማትችል ከተረጋገጠ ደግሞ አገሪቱን ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትሰፍርና በቀጣይ የውጭ ብድር ፍላጎቷ በር የሚዘጋ ሁኔታን ሊፈጥር እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
የውጭ ዕዳን ሙሉ በሙሉ ማሰረዝ አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፣ የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግሥታት በአሁኑ ወቅት ከፈረሰችው ሶቪዬት ህብረት ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ፣ አሁንም ድረስ በዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ተብሎ እስካሁን ተመዝግቦ እንደሚገኝ ይገልፃሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ….   አንዷለም አራጌ

በብልፅግና ፓርቲ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም ድረስ ባለው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ምን መሻሻል አሳየ፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮችን የዕዳ መጠን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ዝርዝር የዕዳ መግለጫ ሰነድ እንደሚያስረዳው፣ ………..(4)
• አገሪቱ እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ 1.5 (አንድ ነጥብ አምስት) ትሪሊን ብር ወይም 52.57 (ሃምሳ ሁለት ነጥብ ሃምሳ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡
• የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡
• የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ 111.9 (መቶ አስራአንድ ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ነው፡፡
• የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 (አምስት መቶ ዘጠና አራት) ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
• ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ 412.5 (አራት መቶ አስራ ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
• መንግሥት ከንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ በየዓመቱ እስከ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ብር ወለድ እየከፈለ ነው
• ከተጠቀሰው አጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ 769.08 (ሰባት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ነጥብ ዜሮ ስምንት) ቢሊዮን ብር ወይም 26.93 (ሃያ ስድስት ነጥብ ዘጠና ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ከተለያዩ የውጭ አበዳሪዎች ተገኝቶ ያልተከፈለ ዕዳ ሲሆን፣
• የተቀረው 730.5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ወይም 25.6 (ሃያ አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ከአገር ውስጥ የመንግሥት ባንኮች ማለትም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣ እንዲሁም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (ጡረታ) ፈንዶች ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
• አገሪቱ ካለባት የውጭ ዕዳ ውስጥ የማዕከላዊ መንግሥት (Centeral Government) ዕዳ 449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር (15.73 ቢሊዮን ዶላር) ሲሆን፣ ቀሪው 319.3 ቢሊዮን ብር (11.17 ቢሊዮን ዶላር) ደግሞ የተለያዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መንግሥት በገባላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ (Loan Guarantee)፣ሌሎች ሁለት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ደግሞ ያለ መንግሥት የብድር መክፈያ መተማመኛ፣ በራሳቸው ከውጭ አበዳሪዎች በቀጥታ ተበድረው ያልከፈሉት ዕዳ ነው፡፡
1) የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ወይም (15.73 ቢሊዮን ዶላር)
2) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች 319.3 (ሦስት መቶ አስራ ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ብር ወይም (11.17 ቢሊዮን ዶላር)
• የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሎኮም ያለ መንግሥት ዋስትና የብድር መክፈያ መተማመኛ ከውጭ የተበደሩት እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት ዕዳ 3.9 ቢሊዮን ዶላር ወይም 111.96 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
• ሎሎቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ገንዘብ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገቡላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ በመጠቀም ከወሰዱት የውጭ ብድር ውስጥ እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት የዕዳ መጠን 207.38 ቢሊዮን ብር (7.27 ቢሊዮን ዶላር) መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
• አጠቃላይ የውጭ ብድር ዕዳ እስከ ማርች 2019 ድረስ አገሪቱ ያለባትን ተመሳሳይ ወቅት ድረስ የተመዘገበው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ደግሞ 730.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡
አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ በሚመለከት በማዕከላዊ መንግሥትንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የተወሰደው 730.5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡ በዚህም መሠረት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ (730.5=343.7+386.8)
• የማዕከላዊ መንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ 343.7 (ሦስት መቶ አርባ ሦስት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ሲሆን፣
• የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ 386.8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡
ማዕከላዊ መንግሥት ካለበት 343.7 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ዕዳ ከፍተኛው መጠን ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር የተወሰደ፣ እንዲሁም በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (የጡረታ) ኤጀንሲዎች፣ ማለትም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህም መሠረት ማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ (343.7= 182+98.2+26.5+37)
• ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣182 (መቶ ሰማንያ ሁለት) ቢሊዮን ብር
• በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የጡረታ ፈንዶች፣98.2 (ዘጠና ስምንት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር
• ከንግድ ባንክ ብድር 26.5 (ሃያ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ነው፡፡
• የተቀረው በመንግሥት ቦንድ ሽያጭ አማካይነት ከልማት ባንክና ከሌሎች ምንጮች ተወስዶ 37(ሠላሣ ሰባት) ቢሊዮን ብር እስከተገለጸው ወቅት ድረስ ያልተከፈለ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ ነው፡፡
ከ730.5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት)ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ማዕከላዊ መንግሥትን የሚመለከተው ተቀንሶ የሚቀረው 386.8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ዕዳ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ዘርዝሮ አያስቀምጥም፡፡ ከልማት ድርጅቶቹ አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ 386 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተወሰደ ሲሆን፣ 800 (ስምንት መቶ) ሚሊዮን ብር ደግሞ የልማት ባንክ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ የመንግሥትን አጠቃላይ የዕዳ መጠንና ዝርዝሮቹን ከያዘው ሰነድ የተለያዩ ከፍተኛ ሥጋቶችን መመልከት የሚቻል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጤንነት አደጋ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡ ሰነዱ ከያዛቸው አኃዞች ምልከታ መረዳት የሚቻለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በቀጥታ፣ እንዲሁም የመንግሥትን የዕዳ ክፍያ መተማመኛ ሰነድ (ቦንድ) በማስያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወሰዱት የረጅም ጊዜ ብድር፣ እንዲሁም ማዕከላዊ መንግሥት ከዚሁ ባንክ ተበድሮ ያልመለሰው የገንዘብ መጠን ድምር እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ 412.5 (አራት መቶ አስራ ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡………….(5)
ምንጭ፡-
{1} The politics and problems of Prosperity Party Gospel/4 April, 2021/by Mulubrhan Balehegn)
{2} የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማዳን ጉዞ/https://www.ethiopianreporter.com/article/21968
{3} https://www.ethiopianreporter.com/article/20907/የአገሪቱ አጠቃላይ የውስጥና የውጭ ዕዳ 2.01 ትሪሊየን ብር መድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic/3 January 2021
{4} ሪፖርተር ጋዜጣ/ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ የብድር ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል/ August 19, 2019 ዮሐንስ አንበርብር
{5} በሙስና ተመዝብሮ በአገር ውስጥና በውጭ 130 ቢሊዮን ብር ተደብቆ እንደሚገኝ ተጠቆመ/7 September 2020/

ተጨማሪ ያንብቡ:  "...የጥላቻ ዘርን በመዝራት የፍቅር አዝመራን መሰብሰብ አይቻልም" - አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (መቀሌ)

 

3 Comments

  1. “ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቶቹ›› በማይጠበቁበት አገር፣ የሰው ልጆች እንደ እንሰሳ በሚታረዱበት እና እንደ ከርከሮ በሚታደኑበት አገር ምርጫ ብሎ ነገር ቧልት ነው“

    ያለፉት የወያኔ 5 ምርጫዎች ከአሜሪካ የሚወዳደሩ የተሳካ ምርጫዎች ነበሩ? ብዙ ሀገሮች ጦርነትም እየተካሄደ ያውም ከኢትዮጵያ የሚበልጥ ህዝብ የሚመራውን መንግስት ይመርጣል:: አሁን ዐቢይ ተነስቶ ምርጫ አናደርግም ቢል ነቀፋህና ማብጠልጠልህ ሌላ ይሆን ነበር:: ዘላለም ጨለምተኞች የተሻለ ሀሳብ ድርቀት አለባቸው የሚሰራና የሚተጋን ግን ከመጎተት አይቦዝኑም:: ለውጥ ግን አያመጡም

    • ሚሊዮን ነኝ ነው ያልከኝ? ያልከው ሁሉ ሁኗል ለመሆኑ ምክንያት ከሆኑት እርኩሰ እርኩሳን ጋር ተደራደሩ ነው የምትለን? ትግሬዎች ተገላገልን አሁንም ቀስፈው የያዙንን የትህነግ ምስለኔዎችን አጽዱልን እያሉ እየተማጸኑን ደብረጽዮን ተንገላታ መጥቶ በመንበረ ስልጣኑ ይቀመጥ ማለት ምን ማለት ነው? አረ ለኛም እዘንልን

  2. ወንድሜ ሙት ፅሁፍህን እስካሁን በብዙ ሳደንቅ ነበር ሆኖም ልክ እንደ ነጋበት ጅብ ቁልጭ ወያኔነትህን በብዙ መልክ ፅሁፍህ ጮሆ ያናግራል:: ህውሀት የሞተ ድርጅት ነው:: አዲስ አበባ ድርሽ አይልም:: ሙሾ ደርድር:: game over !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.