በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህዋሃት ቡድን አባላት ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ገቡ

1
193709517 4466888616676313 1238811665137480719 n
193709517 4466888616676313 1238811665137480719 n

አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህዋሃት ቡድን አባላት በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል በሰሜን ዕዝ ላይ እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሰው ወደ ጎረቤት ሀገር ከሸሹ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት መካከል 1ኛ.ሀብቶም ገብረስላሴ ወልዩ፣ 2ኛ. መሰለ ታመነ እሼቱ እና 3ኛ. ኮነሬል መሀመድ በሪሁ ኑር የተባሉት የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉትን የህዋሃት አሸባሪ ቡድን አባላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪዎችን ተረክቦ ጉዳዩን በህግ አግባብ የሚያጣራ መሆኑን ገልጿል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የደህንነትና የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውን የህዋሃት አመራሮችና የጦር መኮንኖችን ከተደበቁት ስፍራ በማደን ለህግ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።

Ethiopian Broadcasting Corporation 

194438216 4466888993342942 6847534952178227646 n
194438216 4466888993342942 6847534952178227646 n
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቧራው ጨሰ!! በስቶክሆልም ባንዳዎች አንገታቸውን ቀና አደረጉ!!

1 Comment

  1. የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ የትግራይ ህዝብ ዳያስፖራውም ጭምር በስፋት ሊብራራልን ይገባል በግምትም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ ምን ያህል ቁጥር ያላቸው ጁንታዎች እንደተማረኩ ፣ ምን ያህል ቁጥር ያላቸው ጁንታዎች እንደተገደሉ እና ምን ያህል ቁጥር ያላቸው ጁንታዎች እየተፈለጉ እንደሆነ በዝርዝር ሊነገረን ይገባል። እየታደኑ እየተፈለጉ ያሉት የጁንታ አባላት ማንነትን ለህዝቡ ብታሳውቁ ጁንታን አሳልፈን ሰጥተን ሰላምን በትግራይ አስፍነን እንገላገል ነበር። አሁን እየሆነ ያለው አሰራር ግን ጁንታዎችን ሳናውቅ በየቤታችን አስገብተን በደባልነት አክርመን ስናበቃ ከእዛ እንደአጋጣሚ ለሥራ ወደ ሌላ ከተማ ሲጉዋዙ ጁንታ ናቸው ተያዙ ሲባል እየሰማን ነው።
    ጁንታን ሸሸጋችሁ እየተባልንም እየታሰርን ስለሆነ እየተፈለጉ ያሉት ጁንታዎች ማንነት በቅድሚያ በዝርዝር ቢነገረን የት እንዳሉ ለማግኘት አይከብድም ነበር፡፡ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተባለው ግለሰብ የሚመራው መረጃ እና ደህንነት ተቋም ይህንን መረጃዎች ባልሰጠን ሁኔታ ማን የጁንታ አባል እንደሆነ ባልተነገረን ግዜ ጂንታን ተባበራችሁ ፣ ጁንታን ሸሸጋችሁ ወይም ለጁንታ ተቀጠራችሁ የሚለው ውንጀላ ይልቁንም ጁንታን እያጠናከረው ስለሄደ ይታሰብበት። ጁንታ አለመሆናችን እስኪጣራ ማን ይጉላላል እያሉ ትግራውያኖች ለስደት ወይም ጁንታን ለመቀላቀል እየወሰኑ ስለሚገኙ በአስቸኳይ የተፈላጊዎቹ ጁንታዎች ማንነት በዝርዝር ግልጽ ይደረግልን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.