የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ኢትዮጵያ አልሸባብን በመከላከል እያደረገች ባለው እና ሌሎች የጸጥታ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

7
አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።
አምባሳደር ዲና 

በአሜሪካ የተጣለው የቪዛ እገዳ ኢትዮጵያ በቀጣናው በምታካሂደው አልሸባብን የመከላከል እና ሌሎች የጸጥታ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ ውሳኔው በቀጣናው ሽብርተኞችን በመከላከል ረገድ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው ስራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።
በአሜሪካ መንግስት የተላለፈው ውሳኔ መልሶ አሜሪካኖቹን መጉዳቱ አይቀርም ሲሉ ነው አምባሳደር ዲና ያብራሩት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫም፤ የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ለመግባት ያለመ ከሆነና ክፍለ ዘመን የተሻገረውን ወዳጅነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ እስከሆነ ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት መለስ ብሎ ለማጤን ይገደዳል ሲል አስታውቋል።
አምባሳደር ዲና በዛሬው መግለጫቸው፤ ሱዳንና ግብጽ የጋራ ጦር ልምምድ ማድረግ ይችላሉ፤ ኢትዮጵያውያን ግን ሉአላዊነታቸውን ለማስጠበቅ ሁሌም ዝግጁ ናቸው ብለዋል።
አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ በአገሩ ሉኣላዊነት ጉዳይ የሚተኛ ህዝብም ሆነ መከላከያ ሰራዊት እንደሌለን ይታወቃል። ሱዳን እና ግብጽ በድንበር አካባቢ የጥምር ጦር ልምምድ ቢያደርጉም ሁልጊዜም እንደምንለው በኢትዮጵያ ላይ ኪሳራ የሚያመጣ መሆን የለበትም። ኪሳራ የሚያመጣ ከሆነ ግን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመጠበቅ የሚሰራው ኃይል ምላሹን ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ደረጃ እእምነት ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም(ኢ.ፕ.ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  "በጓዳችን አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ህልፈት መሪር ሀዘን ለደረሰባችሁ ሁሉ መጽናናትን እየተመኛለን" - አርበኞች ግንቦት 7

7 Comments

 1. አምባሳደር ዲና ዝቅታ ላይ ስንሆን ሞራላችንን ይገነባሉ እናመሰግናለን።

 2. You guys are trying to find any clumsy if not both realistically and politically stupid excuses for a very terrible things you did and you keep doing with no any real sense of regret and trying to make what has gone and is going wrong right !

  Can you tell us why you horribly failed in the very arena of diplomacy ? Is it not self-evidently true that it is because you appointed and assigned your very ignorant if not stupid cadres including those whose hands are directly or indirectly stained with the very blood of so many innocent citizens ? What should we call all horrifying things for three years and still going on with no sound solutions ? Is it not true that what the people witnessed for the past three years is not better than what Alshebab Did and is doing ? Is it not true that the current ruling elites of EPRDf/ Oromuma/Prosperity have created and are creating a fertile ground for those forces you are talking about? I know that you as a talking tool of the ruling elites who could not and cannot cure their politically motivated crimes of three decades. You really cannot tell us the truth but all kinds of nonsensical rhetoric . I strongly argue that your bosses who keep you just a bread winner servant should be at the very forefront of responsibility and accountability before they tell you to blame others ! The people are fed up and sick of your very irresponsible and nonsensical political propaganda every time you face inescapable challenges.
  Like it or not, the country will never be at peace with herself and in the very arena of world politics as long us ruling elites who continued the very dirty and deadly political system they grew in and served by pushing aside their master (TPLF) and taking over the the thrown three years ago determined to remain behaving what they are behaving now . This system has become no cure type of cancer . The only best way for the country to be in peace both within and internationally , this very cancerous political system must be removed by any appropriate and efficient political struggle !
  You guys, try to revisit your own extremely nonsensical but dangerous political behaviors and actions , sincerely regret , wholeheartedly apologize , help your kids or families not to be ashamed of you, and live the rest of your lives with a sense of relief !
  Good luck

 3. በኢትዮጵያ ከአማራ ንጉሳዊ ቤተሰብ የተወለድኩ የአማሪካን ዜጋ says:

  በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ከኢትዮጵያ መንግስት የባሰ አሸባሪ የለም። በትግራይ ነጭ ፎስፎረስ (white phosphorus) ሰላማዊ ሰው ላይ ተደፋ እየተባለ እኮ ነው ያለው በአሁኑ ወቅት ፤ ውሸት እንዲሆን ምኞቴ ነው። ቴሌግራፍ Telegraph የዘገበው የነጭ ፎስፎረሱ ጉዳይ እውነት ከሆነ ግን በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ከ ኢትዮጵያ መንግስት የባሰ አሸባሪ እንደሌለ ተገንዘቡ ፤ የኤርትራ መንግስት በሁለተኝነት እየተከተለ።

  አብዛኞቹ አሸባሪ የሚባሉት የሶማሊያ አሳ ተመጋቢዎች አሳቸውን እስካልተቀሙ ድረስ እኮ ሰላመኞች ናቸው። የኢትዮጽያ መንግስትም የህዳሴ ግድብን ኤሌክትሪክ ማመንጭያነቱን ሰርዞ ፡ ግድቡን አሳ ቢያረባበት የኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ሰላም እና የተሻለ ብልፅግና ያገኛል ግድቡን ኤሌክትሪክ ከሚያመነጭበት የተሻለ በሰላም በልፅጋ ኢትዮጵያ ።
  ዲና ሙፍቲ አሜሪካ በግዛቴ አትገባትም እንዳለችው ሌሎች ሀገራትም አትገባም ብለውት ፡ በመቀጠልም ዜግነት የሰጠችውም ሀገር የግል ባንክ አካውንቱን ፍሪዝ እንዳታደርግበት ሰግቶ ነው ‘ በቀጠናው ፀጥታ…በቀጠናው አሸባሪ….” እያለ የሚቀባጥረው ።
  .
  ‘ UN demands full inquiry after Telegraph reveals potential white phosphorus burns in Ethiopia’s war. ‘
  .

 4. ቪዛው ገና ጅምር ነው፡፡ ፕ/ሚሩ እና ጀሌውቹ ናቸው ኢትዮጵያን ለ3 ዓመት እያሽበሩ ያሉት። አሜሪካ እንዚህን ዘረኞች ቪዛ ብቻ አይደልም መከልከል ያለባት ጊዚያዊ መንግስትም ማምጣት አለባት፡ አገራችን ላየ ይሄ ጨምላቃ፣ ዘረኛ ፕ/ሚር ኢትዮጵያን እያጠፋ ነው፡፡ አሜሪካን አውጥታ እንደትጥልንን አጥበቀን መያዝ አለብን።

  ወገኖቼ ኢትዮጵያን የምትፈልጉ ከሆነ ይሄንን ነቀርሳ ፕ/ሚር መንግስት ማስወገድ የገድ ይላል። እሱ ካደረስብን እልቂት የባሰ ምንም አይመጣብንም። ወደፊት ኢትዮጵያ መግባት ስትፈልግ ወይ በሱዳን ወይ በኤርትራ እየትደብክ የምትገባበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። የመጨርሻ ደንቆሮ ሃላፊንት የሌለው አዛባ /ሚር ነው።
  እንዴ የሚሰራው ሥራ እኮ ታይቶ የማይታውቅ ነው! የኦሮሞ ፍ/ቤት አዲስ አባባ የሚያቋቁም ሰውዬ የተዝጋጅልህን አላወክም ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያውነትህ እንድትሽማቀቅ የሚያያደርግ ግዜ ነው ያደረስን።

 5. ይህ አስተያየት ” በኢትዮጵያ ከአማራ ንጉሣዊ ቤተሰብ የተወልድኩ የአሜሪካ ዜጋ” ላላው ግለሰብ ነው። በመሆኑም ትውልድህ ከውርንጭላ እናት ሲሆን አጎትህም ፈረስ መሆኑን እንድታረጋግጥ። ዜግነትህ አሜሪካ ከሆነም ከኣለም ህዝብ በላይ ሳትሆን የነጫጭቦች ውርንጭላ የኢቢቲ ተቀላቢ አጋሰስ ጌኛ መሆንህን አርጋግጥ።ስለሆነም ኣብዛኞቹ አሸባሪ የሚባሉት የሶማሊያ አሳ ተመጋቢዎች አሳቸውን ካልተቀሙ ሰላመኞች ናቸው ስለአልከው ደግሞ የሶማሊያ አሳ አስጋሪ እና ተመጋቢ መሆናቸውን አሳ እንዳይበሉ የተከለከሉ መሆናቸውን ዛሬ ከአንተ ተሰማ ።ለመሆኑ ከየትኛው ውሃ ነው አሳ እንዳይመገቡ የተተከለከሉት? ህንድ ውቅያኖስ እንዳትልና ጉድ እንዳይፈላ።
  እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የህዳሴ ግድበ የኤለክትሪክ ማመንጫነቱን ሰርዞ አሳ ቢያረባበት የተሻለ ነው ስለአልከው። በመሠረቱ ይህንን የመሰለ ጥበበ እና እውቀት የሸመትከው በውርጭላ ነጫጭባ ዜጋ ነኝ ባልከው ሀገር አሳማዎችን ስትጠብቅ ከአሳማዎች አዛባ የተማርከው መሆኑን ብታረጋግጥው ተደማጭነት ታገኛለህ። ሆኖም የህዳሴን ግድብ በተመለከተ ያለው መንግሥት ይምራ እንጂ ግድቡ እየተሰራ ያለው በሀገር ውስጥ እና በመላው ኣለም በሚኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን/ዊት ለውድ ሀገረቻው፤ወገናቸው ደከመኝ ታከተኝ ሳይሉ በሚያበረክቱት ትብብር መሆኑን ምንም እንኳን ቡሊት ብትሆንም አይምሮ ካለህ አጥብቀህ እንድትረዳው። ሌላው የውጭ ጉዳይ ቃለአቀባይ ዲና ሙፍቲ ዜግነት የሰጠችው አገር የግል ባንክ አካውንቱን ፍሪዝ እዳታደርግበት በመስጋት ቀባጠረ እያልከን ነው።ሆኖም ግን የአሜሪካ መንግሥት ከመሬት ተነስቶ የግለሰብ አካውንት ፍሪዝ አያደርግም መደረግ ካለበት በተፈጸመው ወንጀል መሰረት የዜግነት መብቱን በመጠቀም በፍርድ ቤት ነው።ምናልባት አንተ በፉድ እስታፕ ያጠራቀምካት ከ$5000 እስከ $100000 ካለችህ ጡርቂ ስለሆንክ ፍሪዝ እንዳይደረግብ ባንክህን ሳትተኛ ጠብቅ የኔ ጡርቂ።

  • አንባው በቀለ
   አሳዳጊ የበደለህ ስለሆንክ አይፈረድብህም! ከአንተ አይነት የበታችኝነት ስሜት ከተጠናወተው ፣ አላዋቂ ፣ የጫት እራራ ፣ ርሀብ ፣ በሽታ ፣ ፍርሀት እና ዱካክ ከሚያስለፈልፈው ልቅ አፍ ጋር ተመሳሳይ ሀገር መወለዳቸው ስላሳፈራቸው ጌቶችን እኔ ውታፍ ነቃያቸውን ይህንን ጥያቄ እንድጠይቅህ አዝዘውኛል ። “ጡርቂ/ የኔ ጡርቂ ምን ማለት ማለት ነው?”

 6. አይ ጉድ አይ ግድ የማይሰማ ነገር የለም።ትናንት ከአማራ ንጉሣዊ ቤተሰብ የተወልድኩ አሜሪካዊ ዜጋ ዛሬ ደግሞ ‘እልፍኝ አስከልካይ” ከነተረቱ ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ይላሉ ።ለመሆኑ የአሜሪካ ዜጋ ሆነህ የየትኛው ንጉስ ቤተ መንግሥት እልፍኝ አስከልካይ ነህ?እንዲያው ያችኑ የፉድ እስታፕ የምታገኝባትን መስሪያ ቤት ይሆን? ከሆነም አዎን የእልፍኝ አስከልካይነቱ ሹመት ይገባሃል። በመሆኑም ትውልድህን በተመለከተ ቀደም ሲል በሰጠሁት አስተያየት አረጋግጠሃል።ይኽውም በበኩሌ ለኔ ” ምንም ድሃ ብሆን ርሃብ ቢርበኝ፤ ምንም ድሃ ብሆን በሺታ ቢያጠቃኝ፤ ለከርሱ ለሆዴ ዜግነት አልቀይር ኢትዮጵያዊ ነኝ። እንዲሁም የጌቶችህ ውታፍ ነቃያቸው መሆንም መልካም ሥራ ሰጥተውሃልና ጽዳታቸውን ጥብቅ እያልኩ የጫት እራራ ያልከው ያው አንተ ራስህ ሺንት ቤት ጨርሰው።የሚባለው ግን የጫት ሃራራ ነው።ታዲያ ጌቶችህ የኢትዮጵያ በአማራ ንጉሣዊ ቤተሰብ ቢሆኑ ኖሮ “ጡርቂ የሚለውን ቃል ሊያስተምሩህ በተገባ ነበር።ስለሆነም ጌቶችህን ጠይቅ ካልሆነም የአማረኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ለይ ታገኘዋለሕ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.