/

በምርጫ መሳተፍ  ወይም ቅስቀሳ ማድረግ ግድያና ውድመት ሲፈጸም ኃላፊነቱን ላልተወጣው አገዛዝ ዕውቅናን እንደመስጠት ይቆጠራል !! – ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር

15

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
ግንቦት 18፣ 2021

መግቢያ

በአለፉት ሶስት ዓመታት በአገራችን ምድር በመንግስትም ሆነ ከመንግስት ጋር በተሳሰሩ ኃይሎች በህዝባችን ላይ ምንም ዐይነት ወንጀል ያልተሰራ ይመስል በሚቀጥለው ወር  በሚደረገው ምርጫ ላይ መሳተፍ አስፈላጊ ነው እየተባለ ቅስቀሳ ይደረጋል። አንዳንድ የውጭ ኃይሎችና በውጭው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህ ዐይነቱ “ታሪካዊ ምርጫ”  እንዳይሳካ አሻጥር በመስራት ላይ ናቸው፤ በተለያዩ የአውሮፓ አገሮችና በአሜሪካን ምድር የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርጫውን ለማሰናከል “ቅስቀሳ ሲያደርጉ” ደርሼበታለሁ በማለት የመንግስቱ የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ   የሃሰት ወሬ በመንዛት አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያውያኖችን በማሳሳት ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ተማርን የሚሉና በጥቅም የተገዙ የፕሮፌሰርነትንና የዶክትሬነትን ካባ ያጠለቁ በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካን ምድር የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የምርጫውን አስፈላጊነት በማስመር ቅስቀሳ ሲያደርጉ ይታያሉ። የከበርቴው ዲሞራሲ በሰፈነበት በምዕራብ አውሮፓና በአሜሪካን  የሚኖሩ ተማርን የሚሉ እንደዚህ ዐይነት ኢትዮጵያውያን ያሉበትን የተደላደለ የኑሮ ሁኔታና የሚያገኙትን ጥቅም በመዘንጋት ባለፉት ሶስት ዓመታት በአገራችን ምድር ሰላም የሰፈነ ይመስል፣ ግለሰብአዊ ነፃነት እንደነገሰና ህዝባችንም በዲሞክራሲ የተንበሸበሸ ይመስል ለምርጫው መካሄድና አስፈላጊነት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ስንሰማና ስናነብ የእነዚህን ምሁራን ዕውቀትና የማመ´ዛዘን ችሎታ እንድንጠይቅ እንገዳደለን። አንዳንዶች በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚያስተምሩ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በትላልቅ ኩባንያዎች ተቀጥረው የሚሰሩና በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ የሰፈነውን የመናገር፣ ሃሳብን የመስጠትና የመተቸት፣ እንዲሁም ደግሞ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የመሳተፍን ነፃነት የሚያውቁ ናቸው። ይሁንና በአገራችን ምድር በግልጽ የሚታየውን ፖለቲካዊ ጭቆና፣ የሰላም እጦትና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ከሚኖሩበት አገር የተንደላቀቀ ኑሮ  ጋር በማወዳደርና በመጸጸት ከህዝባችን ጎን ሲቆሙ አይታዩም። የእነዚህ ምሁራን የዲሞክራሲ መለኪያ አንድ ሰው ብቻ ነው። በእነሱ ዕምነት የኢትዮጵያ ህዝብ ከቁጥር ውስጥ የሚገባና እንደሰው የሚታይ አይደለም። ዲያቆን ዳንኤልና ፈላስፋው ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በተገኙበት ቤተመንግስት ውስጥ በተደረገ የአድርባዮች ስብሰባ ላይ እዚያው የነበረው አንድ ኢኮኖሚስት “ትላንት ያጣነው መሪ ነበር፣ ዛሬ ደግሞ መሪ አግኝተን ህዝብ አጣን”  ያለው አድርባይ አነጋገር በእነዚህ ምሁራንም ዘንድ ሲንፀባረቅ ይታያል።

የለውጥ ኃይል የሚባለው በዶ/ር አቢይ የሚመራው አገዛዝ ስልጣንን ከተቀዳጀ ይኸው ሶስት ዓመቱን አስቆጠረ። በእነዚህ ሶስት ዓመታት ውስጥ ህዝባችን በህይወቱ አይቶ የማያውቃቸውን አሰቃቂ ነገሮች በሙሉ ለማየትና ለመቅመስ ተገዷል። በነፃነት ፈንታ ኢ-ዲሞክራሲያዊና አፋኝ ስርዓት ነግሷል። በተለይም ዘር ተኮርና አንድ ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ግፍ ተፈጽሟል። አሁን በቅርቡ ደግሞ  በመንግስት በተደገፈ በሚመስል በሚገባ በተዳረጀ  ኃይል አልጣዬ፣ ሸዋ ሮቢትና ካራ ቆሬ ላይ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ከፖለቲካ ጋር ምንም ዐይነት ግኑኝነት የሌላቸው ምስኪን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በግፍ ተጨፍጭፈዋል። የብዙ መቶ ዓመታት ዕድሜን ያስቆጠሩ ከተማዎች እንዳሉ ወድመዋል። ቀደም ብሎም  ሻሸመኔ፣ በኋላ ላይ ደግሞ መተክልና የምዕራብ ወለጋ እንደዚሁ በየክልሉ አስተዳዳሪዎች የተሰገሰጉና ያንን ከለላ በማደረግ መጤዎች ብለው በሚጠሯቸው ዜጋዎችና ቀይ  ፊት ያላችሁ ናችሁ እየተባሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎችና የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች በግፍ ተገድለዋል። በብዙ ሺሆችም የሚቆጠሩም በመፈናቀል ለረሃብና ለብርድ እንዲጋለጡ ተደርገዋል። ይህ ሁሉ ወንጀል ተፈጽሞና አሁንም እየተፈጸመ ባለበት ወቅት ከአገዛዝ ተብዬውም ሆነ ከደጋፊዎቹ ከምርጫ በኋላ አዲስ ሁኔታ እንደሚጠፈር ነው የሚነግሩን። ዛሬ ስልጣንን የጨበጡት ኃይሎች ከምርጫ በኋላ በአሸናፊነት ሲወጡ መልካቸው ሁሉ ተቀይሮ፣ በአዲስ አስተሳሰብ ታንጸው፣ ሙሉ በሙሉ ዲሞክራቶችና የነፃነት፣ እንዲሁም የተሟላ ዕድገት አራማጆች ሆነው በመውጣት አገራችንና ህዝባችንን በተለየ መልክ እንዲሚለውጧት ነው ሊነግሩንና ሊያሳምኑን የሚሞክሩት። “ከምርጫ በኋላ ሁሉንም ነገር ታዩታላችሁ፣ አትቸኩሉ፣ ጊዜ ስጡን”  እያሉ ነው ለማዘናጋት የሚሯሯጡት። በተጨማሪም ከምርጫ በኋላና እኛ በአሸናፊነት ስንወጣ እስካሁን ድረስ በግፍ የተገደለው ህዝባችን ከሞተበት በመነሳት ስላማዊ ኑሮ መኖር ይጀምራል፤ አዲሱም  አገዛዝ ሁሉንም ነገር ያደርግላቸዋል፣ ብለን እንድንቀበል ነው የሚያጃጅሉን። ይህ ሊሆን እንደማይችልና በምርጫም ብቻ በአገራችን ምድር ምንም ዐይነት ለውጥ፣ መሻሻልና ዕድገት እንደማይመጣ ለማረጋገጥ እሞክራለሁ። ከዚያ በፊት ግን እንደኛ በመሰለው በብዙ ነገሮችና እጅ ወደ ኋላ በቀረው አገርና በምዕራብ አውሮፓ አገሮች ስለሚካሄደው ምርጫና ስለሚያመጣው ውጤትና በመሀከላችን ስላለው የሰማይና የመሬትን ያህል ዕርቀት ልዩነት ለማሳየት  እወዳለሁ። በተለይም በዚህ ነገር ላይ ግልጽ ግንዛቤና አቋም እስከሌለን ድረስ ስለህግ የበላይነትና ስለ ምዕራቡ የካፒታሊስት አገሮች የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ አሰራር  መሰረተ-ሃሳቡ አልገባንም ማለት ነው።

 

የምዕራብ አውርፓ የዲሞክራሲ ዕድገት፣ የፓርቲዎች አወቃቀርና

የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ አሰራር!!

በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ የዲሞክራሲያዊ ስርዓትንና የብዝሃዊነት ፓርቲ አወቃቀርን ወይም አደረጃጀትን አስመልክቶ በአብዛዎቻችን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የግንዛቤ እጦት አለ። በተለይም እዚህ ምዕራብ አውሮፓና አሜሪካንም ጭምር ከሰላስና ከአርባ ዓመታት በላይ  ብንኖርም የፓርቲዎችን መፈጠርና አደረጃጀትት፣ እንዲሁም የሚከተሉትን ርዕዮተ-ዓለምን አስመልክቶ ፖለቲከኞች ነን በሚሉት ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የግንዛቤ እጦት አለ። በአሁኑ ወቅት በአራችን ምርጫ መካሄድ አለበት ብለው የሚወተውቱትንና ለዚህም ቅስቀሳ የሚያደርጉትን ስንመለከት እነዚህ ሰዎች አውሮፓና አሜሪካ ብዙ ዓመታት ቢኖሩም ፓርሊሜንተሪ ዲሞክራሲ በተግባር ሲመነዘር  ምን ዐይነት ውጤት እንደሚያመጣ ለመገንዘብ የሚችሉ አይደሉም። በሌላ ወገን ግን በአሁኑ  የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ምርጫ ቢካሄድ ፋይዳ የለውም፣ እንዲያውም ይባስ ብሎ ለአገዛዙ ዕውቅና መስጠት ነው ብለው የሚሟገቱትን ጽንፈኞች ናቸሁ በማለት የራሳቸውን ኢ-ሳይንሳዊ፣ ፀረ-ዲሞክራሲያዊና ፀረ-ህዝብ አመለካከት በሌላው ላይ ለመለጠፍ ይሞክራሉ። በተለይም ምሁራን ናችሁ ብለው ከሚጠሩን ህዝባችን የሚጠብቀው መሰረታዊ ነገሮች አሉ። አርቆ አሳቢነትን፣ ማመዛዘንን፣ ማነፃፀርንና ተጨባጭ ሁኔታዎችንም ሆነ ፖለቲካዊና መንግስታዊ አወቃቀርን በትክክለኛው የዕውቀት መነፅር በመመርመር ትክክለኛ ትንተና መስጠት። ለሀቅ መቆምና በምንም ዐይነት በጊዜያዊ ጥቅም አለመገዛትና ለዝና ብሎ ህዝብ የጣለብንን አደራ አለመዘንጋት። አንድ ምሁር ወይም የተማረ ሰው ተማረ የሚያሰኘው በራሱ ህሊና ሲገዛና በነፃም ሲያስብ ብቻ ነው። ሀቀኝነትና አንድ ተጨባጭ ሁኔታን በቅጡ መመልከትና ትንተና መስጠት ደግሞ የምሁራዊነት መመዘኛ ነው።

ለማንኛውም ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የነበሩ የተለያዩ ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች፣ እንዲሁም የህብረተሰብ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለሀቅ ባይቆሙና ትክክለኛው ዕውቀትና መንገድ ይኸኛው ነው ብለው መንገዱን ባያሳዩና አጥብቀው ባይታገሉ ኖሮ በጠቅላላው የሰው ልጅ በጨለማ ዓለም ውስጥ እንደሚኖር የተረጋገጠ ጉዳይ ነበር። ፖለቲካዊ ፍትሃዊነት፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍትሃዊነትና የህግ የበላይነት፣ በተለይም ደግሞ ማንኛውም የሰው ልጅ በአምላክ ምስል የተፈጠረ በመሆኑ በሌላ እሱን በመሰለ መሰቃየት፣ መብቱ መገፈፍና መገደልም የለበትም የሚሉትን መሰረተ-ሃሳቦች ያስተላለፉልንን መሰረታዊ ነገሮች የእነሱን ፈለግ በመከተል ለዕውነተኛ ነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር መታገል ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታችን መሆን አለበት።  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ በመሆኑ ከሌላ ብሄረሰብ መጣ እየተባለ ጭፍጨፋና መፈናቀል እንዳይካሄድበት አጥብቆ መታገል አስፈላጊ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደነፃ ዜጋ ሲታይና መብቱ ሲከበር ብቻ ነው ዕውነተኛ ኢኮኖሚያዊና ህብረተሰብአዊ ዕድገት ሊመጣ የሚችለው። ከዚህ በላይ በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ የመንግስትን መኪና የጨበጠ ሁሉ ከአምላክ ፈቃድ የተሰጠው ይመስል ህዝባችንን የማሰቃየት፣ የመግደልና መጤ ነህ እያለ የማሳደድ መብት እንደሌለው ነው። ሰውን በጅምላም ሆነ በተናጠል መግደል፣ ከቀዬው ማፈናቀልና ማሳደድ፣ እንዲሁም ከአለአግባብ አንድን ሰው እስር ቤት ውስጥ መወርወር የተፈጥሮንና የህብረተሰብን ህግ የሚጥሱ በመሆናቸው ይህ ዐይነቱ ኢ-ሳይንሳዊና ኢ-ፍልስፍናዊ አመለካከትና ድርጊት ከአገራችን ምድር ለአንዴም ለመጨራሻም ጊዜ መወገድ ያለበት ጉዳይ ነው። ለዚህም አትብቆ መታገል ያስፈልጋል።

በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ የዲሞክራሲ ዕድገትና የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ ብቅ ማለት የረጅም ጊዜ የአስተሳሰብ ለውጥና የማቴሪያል ዕድገት ውጤቶች ናቸው። ካፒታሊዝም እንደ ስርዓተ-ማህበር ከመቋቋሙም ሆነ ከመገንባቱ በፊት በከፍተኛ ደረጃ የጭንቅላት ስራ ተሰርቷል። ንቃተ-ህሊና እንዲዳብር መሰረት ተጥሏል። ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ መገንዘብ እንዲቻል ፈላስፋዎች ያልተቋረጠ ጥረት ለማድረግ ሞክረዋል። ምክንያቱም ማንኛውም ነገር በጭንቅላት ስለሚታይ፣ ግንዛቤ ውስጥ ስለሚገባና ስለሚተነተን ነው። ስለሆነም በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ጭንቅላት፣ አዕምሮና መንፈስ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ ማለት ነው። ካፒታሊዝም እያደገና እየተስፋፋ ሲመጣም ከፍተኛ የሆነ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሊዳብርና የኑሮ መሻሻልም እንዲኖር ከፍተኛ ትግል ይደረግ ነበር። በተለይም እንደ ሶስዮሎጂ፣ የተለያዩ የኢኮኖሚክስ ቲዎሪዎች፣ ታሪካዊ ምርምሮችና፣ የሳይኮሎጂ ምርምር፣ በጠቅላላው የህብረተሰብን ዕድገት የሚመለከቲ ነገሮች በሙሉ ካፒታሊዝም እየተስፋፋና እያደገ ሲመጣ ነው እንደ ዕውቀት መዳበር የቻሉት። ከዚህም በላይ የካፒታሊዝም ማደግና መስፋፋት፣ እንዲሁም አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እያቀፈ መምጣት ወይም በላቡ እየጣረ እንዲኖር ማድረግ የግዴታ የተቋምም መስፋፋት እንዲፈጠር አስገደደ። በየቦታው ትምህርት ሲስፋፋ ቀስ በቀስም የህብረተሰቡ የማሰብ ኃይል ከፍ እያለ መምጣት ቻለ። ይሁንና ግን እስከ አስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ወይም ደግሞ እስከ ሃያኛው ክፍለ-ዘመን መግቢያ ድረስ በአብዛዎቹ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች የፍጹም ሞናርኪዎች አገዛዝ የሰፈነበት ሁኔታ ነበር። ከሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ በስተቀር ይህንንም ሆነ ያኛውን ዐይነት ስም የለጠፉ ፓርቲዎች አልነበሩም። ዛሬ የተለያየ ስም ይዘው የሚንቀሳቀሱና ለምርጫም የሚወዳደሩ ፓርቲዎች ዕድሜያቸው ከሰባና ከአርባ ዓመታት በላይ አይበልጥም። እንደ ፖርቹጋልና ስፔይን የመሳስሉት አገሮች ጋ ስንመጣ ደግሞ በእነዚህ አገሮች ፓርቲዎች ብቅ ያሉትና በብዝሃዊነት ላይ የተመሰረተ ፓርላሜንት የተቋቋመው ከ1974 ዓ.ም በኋላ ነው።

ባጭሩ በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ፓርቲዎች የካፒታሊዝም እድገት ውጤቶች እንጂ ካፒታሊዝም ከመመሰረቱና ከመዳበሩ በፊት የተፈጠሩ አልነበሩም። ምክንያቱም ካፒታሊዝም እያደገ ሲመጣና አብዛኛውን ህዝብ ተቀጥሮ እንዲሰራ ሲያደርግ ህብረተሰቡ በመደብና በገቢ መከፋፈል ጀመረ። በዚያው መጠንም በአስተሳሰብና በፍጆታ አጠቃቀም እየተለያየ መጣ። ይህ ሁኔታ ፓርቲዎችን በተለያየ የርዕዮተ-ዓለም ስም እንዲደራጁ አስገደዳቸው። ይህንን ወይም ያንን የርዕዮተ-ዓለም ስም የለጠፈ ለዚኽኛው ወይም ለዚያኛውም መደብ ጥቅም ነው እታገላለሁ በማለት በጎራ ተሰለፉ። ስለሆነም የፓርቲዎችም አደረጃጀት ታሪካዊና ህብረተሰብአዊ ግዴታ ነው ማለት ይቻላል። ፓርቲዎችም በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ የተዋቀሩ በመሆናቸው ጠቅላላውን ህዝብ የሚወክሉ ሳይሆን እንደ ርዕዮተ-ዓለማቸው ለዚኽኛው ወይም ለዚያኛው  መደብ ጠበቃ የቆሙ ናቸው። ይሁንና ፓርቲዎቹ የርዕዮተ-ዓለም ባህርይ ቢኖራቸውም በአወቃቀራቸው ምሁራዊ ባህርይ ስላላቸውና ከውስጥ በስራ-ክፍፍል በመመደብ የተለያዩ ህብረተሰቡን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት አንደኛው ሌላውን ቻሌንጅ የሚያደርጉ ናቸው። በፓርቲዎችም ውስጥ የአምላኪነትና የአድርባይነት ባህርይ በፍጹም አይታይም። አንድ ግለሰብ እንደፈለገው አንድን ፓርቲ ሊበውዘውና እኔ በምለው መንገድ ብቻ ተጓዙ የሚል መብት የለውም። አባላቱም በዕውቀት ተወዳዳሪዎች በመሆናቸው አንደኛው ሌላውን ተከታዩ ሊያደርገው በፍጹም አይችልም። መመዘኛቸውም የቆሙለት ርዕዮተ-ዓለማቸውና አንድ ላይ ሆነው ያረቀቁት ፕሮግራማቸው ነው።

በኢኮኖሚ ስርዓቱ ማደግና ተቋሞችና መንግስትም ጭምር ከሞላ ጎደል ዲሞክራሲያዊ አወቃቀር ስላላቸውና በኃላፊነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በምርጫ አማካይነት አንደኛው ፓርቲ በአሸናፊነት ቢወጣ ተጠያቂነቱ ለጠቅላላው ህዝብ የሚሆንና የተዋቀረውንና በደንብ የሚሰራውን ኢኮኖሚ እንደፈለገው የመለወጥ መብትና ችሎታም  የለውም። በህገ-መንግስቱም ስርዓቱን መለወጥ እንደማይቻል የተደነገገ ሲሆን፣ ይህ ማለት ግን አልፎ አልፎ መሻሻሎች አይደረጉም ማለት አይደለም። እንደየ አስፈላጊነቱም ህገ-መንግስቱንም ሆነ ሌሎች ነገሮች ይሻሻሉ። በተለይም በጣልቃ-ገብ የኢኮኖሚ ፖሊሲ(Interventionist Economic policy) አማካይነትም አንዳንድ የመሻሻያ እርምጃዎች ይወስዳሉ። ካፒታሊዝም በአውቶኖመስ ደረጃ ስለሚሰራም ከምርጫ በኋላ በቂ ድምጽና መቀመጫ ማግኘት ካልተቻለና በአስቸኳይም መንግስት መመስረት የማይቻል እንኳን ቢሆን ስርዓቱ ስራውን አያቋርጥም። ማህበራዊውም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ስራው ይቀጥላል። በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ መስሪያቤቶችም ካለምንም ጉድለት ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። ከብዙ ልምድና የጭንቅላት መዳበር የተነሳም፣ በፓርቲዎች መሀከል ጥምር መንግስት መመስረት የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። እስከ 1980ዎቹ ዓ.ም መግቢያ ድረስ በሶሻል ዲሞክራቲክና በሊበራል ፓርቲዎች መሀከል የጣምራ መንግስት የመመስረት ባህል ሲኖር፣ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በኮንሰርቫቲቭ ፓርቲዎችና በሶሻል ዲሞክራቶች መሀከል ከብዙ ድርድር በኋላ የጣምራ መንግስት መመስረት እንደባህልና እንደልምድ እየተወሰደና ተቀባይነትም እያገኝ መጥቷል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ አረንጓዴው ፓርቲ ከሚባለው ጋርም በፌዴራልም ሆነ በሪጂናል ደረጃ በጣምራ መንግስት መመስረት ተለምዷል። በሁለት ፓርቲዎች መሀከል በሚደረገው ድርድርም እስከ ስድስት መቶ የሚቆጠሩ የፓርቲዎች ተጠሪዎች ወይም ጠቅላላውን አባል የሚወክሉ ወካዮች ድምጻቸውን መሰጠትና መሻሻያም ማቅረብ እንደ ቅድመ-ሁኔታም  የሚሰራበት መሰረተ ሃሳብ ነው። በሌላ አነጋገር፣ የአንዱ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ወይም ጥቂት ሰዎች እንደፈለጋቸው የሚደነግጉበት ሁኔታ የለም። በፓርሊያሜንቱም ውስጥ እያንዳንዱ ተመራጭ ለህሊናው ተገዢ ሲሆን፣ የራሱን አገዛዝ ፖሊሲ የሚቃወምበት ወይም ድምጽ የሚነፍግበት ጊዜ አለ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመድረክ መስቀለኛ መንገድ

ይህ ጉዳይ አንደኛው ሲሆን፣ በጠቅላላው አገር ውስጥ የህግ የበላይነት የሚባለው በሚገባ የሚሰራበት ነው። በሶስቱም የመንግስት አካሎች፣ ማለትም በህግ አውጭው፣ በህግ አስፈጻሚውና በኤክስኩቲቩ መሀከል ግልጽ የሆነ የስራ ክፍፍል አለ። ስልጣንን የጨበጠው ኃይል ወይም ኤክስኩቲቩ ከፓርሊያሜንቱ በስተጀርባ ወይም እሱን በመርገጥ የፈለገውን ነገር ለማድረግ አይችልሞ፤ መብትም የለውም። የፓርሊያሜንታሪ አጣሪ ኮሚቴ የሚባል ነገርም ስላለ አንዳንድ ሚኒስተሮችና አገዛዙ ራሱ ከህገ-መንግስቱና ከፓርቲዎች ስምምነት ውጭ በራሳቸው ፈቃድ አንዳንድ ስምምነቶችን ካደረጉ በቀጥታ ይጠየቃሉ። እንደሁኔታውም ፓርሊያሜንቱ በመሰብሰብ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ላይ ዕምነት እንደሌለውና(Vote of no Confidence) ድምጽም በመሰጠት በድምጽ ብልጫ ከስልጣን የሚነሳበት ጊዜ አለ። ተግባራቸውንም በሚገባ የማይወጡ ሚኒስተሮች ክስልጣናቸው በአስቸኳይ እንዲነሱ ይደረጋሉ። ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ዋናው ጉዳይ የመንግስቱ መኪናና ከምርጫ በኋላ ስልጣንን የሚጨብጠው ፓርቲ አንድ ላይ የሚያያዙና ገዢው ፓርቲ እንደፈለገው የመንግስቱን መኪና የሚጠመዝዘውና ለጥቂት ሰዎች መገልገያ የሚያደረገው ሳይሆን የመንግስቱ መኪና በአውቶኖመስ ደረጃና በህገ-መንግስቱ መሰረት የሚሰራ ነው። ይህም ማለት የመንግስቱ መኪና፣ ማለትም ወታደሩ፣ ፖሊሱ፣ የስለላ ድርጅቱ እንደመጨቆኛ መሳሪያ የሚታዩ ሳይሆን የህዝብን ደህንነት የሚጠብቁ ናቸው። ሰላማዊ ሰልፍ ቢደረግና ሰልፉም ከቁጥጥር ውጭ ቢወጣ በህዝብ ላይ የመተኮስ መብት የላቸውም። ከዚህ አልፈን ስንሄድ ደግሞ በህገ-መንግስት ፍርድ ቤት(Constitutional Court) ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስልጣን የጨበጠውን ፓርቲ ወይም የጣምራ አገዛዝ የመክሰስ መብት አላቸው። ለምሳሌ አገዛዙ የሚወስደው ማንኛውም ፖሊሲ ከህገ-መንግስቱ ጋር የማይጣጣም ከሆነ አገዛዙ ይከሰሳል። ከዚህም በላይ በፓርላሜንት ውስጥ በድምጽ ብልጫ የጸደቀ ህግ በህገ-መንግስት ፍርድ ቤት ሊሻርና በሌላ ሊተካ ይችላል። ስልጣንን የጨበጠውም ፓርቲ የህገ-መንግስቱን ውሳኔ አልቀበልም የማለት መብት በፍጹም የለውም። ከዚህ ውጭ ደግሞ መንግስትንም ሆነ ፓርቲዎችን የሚቆጣጠሩ በደንብ የተደራጁ የሲቪል ማህበረሰብ አሉ። እነዚህ ራሳቸው  በመንግስቱ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ጫናና መሻሻልም እንዲደርግ ጥረት ያደርጋሉ። ከዚህም በላይ በመንግስት በጀት ተመድቦላቸው የአገር ውስጥንና የውጭውን ፓለቲካ፣ የህበረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ጉዳይ፣ የስነ-ምግባርን ጉዳይ በሚመለከት…ወዘተ. ምርምርና ጥናት በማድረግ ለመንግስት የሚያቀርቡና ምክርም የሚስጡ አሉ። በአገር አቀፍ ደረጃ ቢያንስ ከስድስት በላይ የሚሆኑ የኢኮኖሚክስ የምርምር ተቋማት አሉ። እነዚህም በርዕዮተ-ዓለም ወይም በተለያየ ሳይንሳዊ አመለካከት የተደራጁ በመሆናቸው የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ በማጥናትና በሰው የገቢም ሆነ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያለውን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ በመመርመር ማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለመንግስት ምክር ይሰጣሉ፣ በመንግስትም ላይ ግፊት ያደርጋሉ። በልዩ ልዩ ተቋማት የሚደገፈው የካፒታሊስት ኢኮኖሚ በዚህ መልክ የሚሰራና ህብረተሰብአዊ መረጋጋት እንዲኖር የሚያደርግ ነው።

ባጭሩ በሰለጠነው የምዕራቡ ዓለም የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ አሰራሩ እንደዚህ ነው። ፓርቲዎችም የአድርባይነት ባህርይ በፍጹም የላቸውም። ዕምነታቸውም ለቆሙበት ዓላማ ሲሆን አብዛዎችም ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸውና ኃላፊነትም የሚሰማቸው ናቸው።  ይህ ዐይነቱ የዳበረ አስተሳሰብ ለመቻቻል፣ ችግሮችን በውይይትና በክርክር፣ በተለይም በዕውቀት ደረጃ እንዲፈታ አስችሎአቸዋል። ስለሆነም ነው መረጋጋት የሚታየውና፣ አንድ ዐይነት ችግርም ሲከሰት በአስቸኳይ መፍትሄ ለመፈለግ ሩጫ የሚደረገው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከሰላሳና ከአርባ ዓመታት በኋላ ሁኔታዎች በዚህ መልክ መቀጠል እንደማይችሉ በመረዳታቸው የወደፊቱን ሁኔታና ሊከሰት ከሚችለው ሁኔታ ጋር ሊሰራ የሚችል ምርምር እያደረጉ ነው። ብቃትነት ካላቸውና በመንግስት ከሚደጎሙት ተቋማት ባሻገር ከሁለት መቶ በላይ በተለያየ ፊልድ የሰለጠኑ ምሁራንን ያቀፈ ተቋም በማቋቋም ጥናትና ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው። የወደፊቱም ኢኮኖሚ አደረጃጀት የምርትን አመራረት፣ የጥሬ-ሀብትን ሁኔታ፣ የአየር መለዋወጥን ጉዳይ በማጤን ጠቅላላው ስርዓት ተከታታይነት (Sustainability)  እንዲኖረውና ለተከታታዩ ትውልድም እንዳያልቅ ታስቦ በመዘጋጀት ላይ ነው። እንደኛው አገር በአቦ ሰጡኝ የሚሰራ አይደለም ማለት ነው። ከዚህ በመነሳት ነው በአገራችን ምድር በተለይም በአሁኑ ሁኔታ የምርጫን አስፈላጊነትና አላስፈላጊነት፣ እንዲሁም ከምርጫው ውጤት ህዝባችን የሚጠብቀውንና የሚፈልገውን ማግኘት ይችል እንደሆን  መመርመር የምንችለው። ዋናው መሰረተ ሃሳብና በጭንቅላት ውስጥ መቋጠር ያለበት ጉዳይ በአውሮፓ ምድር ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ስልጣን ላይ የያዙትና አገሮቻቸውን በጊዜው ከሰፈነው ከፍተኛ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የባህል ቀውስ ሊያላቅቁ የቻሉ መሬዎች በጀርመን እንደ አደናወር፣ በኋላ ደግሞ ዊሊይ ብራንዳትና ሄልሙት ሽሚድት ሲሆኑ፣ በአውስትርያ ብሩኖ ክራይስኪ፣ በስዊድን ደግሞ ኦላፍ ፓልመ የሚባሉት ታላላቅ መሪዎች ናቸው። እነዚህ በጊዚው የየአገሮቻቸው መሪዎች ብቻም ሳይሆኑ የዓለም መሪዎችም ነበሩ ማለት ይቻላል። በትልቅ ታታሪነት፣ አስተዋይነትና ቻይነት አገሮቻቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከደቀቀ ኢኮኖሚ በማላቀቅ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ በመገንባት እኛም መጥተን እዚህ ለመኖር እንድንችል አድርገዋል። መሪ ማለት እንደዚህ ነው እንጂ በተንኮል መንፈስ በመጠመድ የራሱን ዜጋ በመግደልና በማስገደል አገሩን መቀመቅ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም።

 

የኢትዮጵያ መንግስታዊ አወቃቀር ለዲሞክራሲ እንቅፋት የመሆኑ ጉዳይ!

በአገራችን ምሁራን ዘንድ የመንግስትን መኪና አወቃቀርና ተግባር አስመልክቶ አንዳችም ቦታ ጥናትና ምርምር ተደርጎ አያውቅም። ስለዚህም ጉዳይ ማንሳት እንደወንጀልና እንደ አናርኪስነት ነው የሚያስቆጥረው። በአብዛኛዎቻችን ዕምነት መንግስት የሚባለው ነገር ከእግዚአብሄር የተሰጠ፣ በሂደት ውስጥ መሻሻል የሌለበት፣ የማይነካና የማይዳሰስ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው። ስለሆነም መንግስት ዲሞራሲያዊ ባህርይ ሊኖረው አይገባም፣ ስልጣንንም የሚጨብጡ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የሞራልና የዕውቀት ብቃት ሊኖራቸው አይገባም። ማንም ሰው እየተነሳ የመንግስትን መኪና በመጨበጥ የፈለገውን ነገር የማድረግ መብት አለው የሚል ግንዛቤ በአብዛኛዎቻችን መንፈስ ውስጥ ተቀርጿል። መንግስት አገለጋይና ህዝቡን ከማንኛውም አደጋ ጠባቂ ሳይሆን ከላይ ሆኖ የሚያዝና በፈላጭ ቆራጭነት የሚገዛ ነው። ይህ ዐይነቱ ፊዩዳላዊ አስተሳሰብ ነው እስከዛሬ ድረስ አገራችንን መቀመቅ ውስጥ የከተታትና ህዝባችንም ፍዳውን እንዲያይ የተደረገው።፡

በሌላ ወገን ግን በአውሮፓ የካፒታሊስት ህብረተሰብ ውስጥ ከመንግስት መኪና አንስቶ እስከሌሎች ጉዳዮች ድረስ ምርምርና ክርክር ሳይደረግ አንዳችም ነገር በፍጹም ተግባር ላይ አይውልም። መንግስት ማለት ምን ማለት ነው? ተግባሩስ ምንድነው? ምን ዐይነት ሰዎችስ የመንግስትን መኪና መቆጣጠር አለባቸው? ስለሆነም በአውሮፓ ምድር ውስጥ የሰውን ልጅ ህይወት የሚመለከቱ ማንኛውም ነገሮች፣ ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፍትሃዊነትን አስመልክቶ ሰፋ ያሉ ምርምር ተካሂዷል። ከተማዎች እንዴት እንደሚገነቡ፣ የቤቶች አሰራር ምን ዐይነት ይዘት እንደሚኖራቸው፣ በተፈጥሮና በሰው ልጅ መሀከል ሊኖረው የሚገባው ግኑኝነት… ወዘተ. ደረጃ በደረጃና በጥልቀት ተመርምረዋል። በዚህም መሰረት ተግባራዊ ሊሆኑ በቅተዋል።  ይህም ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ በጣም አስከፊ ሁኔታና ጨቋኝ አገዛዞች ስለነበሩ ይህንን በጥብቅ የተመለከቱ ምሁራን አንድ ህዝብ እንደ እንስሳ መታየት የለበትም፣ አንድ አገርም በዚህ መልክ ሊያድግ አይችልም፣ ማህበራዊ ሰላምም ሊኖር አይችልም ብለው በመረዳታቸውና የህግ የበላይነት መከበርንና የመንግስት ተግባርንና ኃላፊነትን በሚመለከት በግልጽ እንዲታወቅ አጥብቀው በመታገላቸው ነው። ይህ ያልታከተ ትግላቸውና ምርምራቸው ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ቀስ በቀስ ተግባራዊ መሆን በመቻሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት አግኝቷል። በዚህም ምክንያት የተነሳ መንግስት የካፒታሊዝምን ዕድገት አራማጅ እንዲሆን ሆኖ በመዘጋጀት ቀስ በቀስ በእርግጥም ደግሞ ጠቅላላው ኢኮኖሚ በሳይንስና በቴኮኖሎጂ ላይ ተመስርቶ እንዲቀሳቀስ አስችሎታል። ይህ ማለት ግን ከሶስት መቶና አራት መቶ ዓመታት በፊት የነበሩ ፈላስፋዎችና የተፈጥሮ ሳይንቲስቶች ምኞት ካፒታሊዝምን እንደ ስርዓተ ማህበር ተግባራዊ ማድረግ ሳይሆን ጥበባዊና ስርዓት ያለው፣ እንዲሁም በሁሉም አቅጣጫ ፍትሃዊነት የተሞላበት ስርዓት መመስረት ነበር። የኋላ ኋላ እነሱ የተመኙት ሳይሆን በአሸናፊነት የወጣው ዛሬ ካፒታሊዝም ብለን የምንጠራው ስርዓት ነው። ይሁንና ከብዙ ልምድና ትግል በኋላ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ መሻሻሎች በመደረጋቸው በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ልዩ ልዩ ድጎማችዎችን እንዲያገኝ ተደርጓል።

ወደ አገራችን ስንመጣ የአገራችን ዘመናዊ የመንግስት መኪና አወቃቀር የምሁራዊ እንቅስቃሴና የኢኮኖሚው ማደግ፣ የከተማዎች መገንባትና በተለያዩ መገናኛና መመላለሻ መንገዶች መያያዝ ነፀብራቅ ወይም ውጤት አይደለም። የአገራችን ዘመናዊ የመንግስት መኪና አወቃቀር ከውጭ የመጣና ወደ ኋላ በቀረ ስርዓትና አስተሳሰብ ላይ የተጫነ ነው ማለት ይቻላል። ስለሆነም እንደዚህ ዐይነቱ መንግስታዊ አወቃቀር እንደ ካፒታሊስቱ የመንግስት መኪና አወቃቀር ኢኮኖሚው ሰፋ ባለ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ላይ ተመስርቶ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ ሳይሆን እንዲያውም ካፒታሊዝም እንዳያድግ የሚያፍንና፣ ሰፊው ህዝብ ባልባሌ ቦታዎች ላይ እንዲሰማራ የሚያደርግ ነው። ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ለሃይማኖትና ለጎሳ ግጭት ምክንያት ሊሆን ችሏል። ኢኮኖሚያዊ መዛባት፣ ኢኮኖሚው በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ተደግፎ ለመንቀሳቀስ አለመቻል፣ ሰፋና ግልጽነት ያለው የገበያ ኢኮኖሚ አለመኖር፣ ሰፊው ህዝብ ተከታታይነት ያለው ገቢ እንዲኖረው አለመደረጉ፣ የወጣቱ በስራ መስክ መሰማራት አለመቻልና የሙያ ማስልጠኛ ቦታዎች ባለመኖራቸው ጊዜውን ባልባሌ ነገሮች ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉ…ወዘተ. …ወዘተ.  እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮች ለማህበረሰባዊ ግጭቶች፣ በጎሳዎችና በሃይማኖቶች መሀከል ላሉ መሻከሮች ምክንያት በመሆን ግጭት እንዲፈጠሩ የማድረግ ኃይላቸው ከፍ ያለ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ አደገኛ አጀንዳ ላላቸው ለውስጥና ለውጭ ኃይሎች በጣም አመቺ ነው። ህብረተሰብአዊ ግጭት እንዲፈጠር አመቺ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል። ስለሆነም አገዛዝ የሚባለውና የመንግስቱ መኪና በጣም ጠባብ ዕውቀት ባላቸው ሰዎች በመያዛቸው በህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ሁሉ የመመልከት ኃይል የላቸውም። ግጭት ሲፈጠር ሁኔታውን ለማረጋጋት የሚሞኩሩት በጠብመንጃ ወይም በመተኮስና ሰውን በመግደል ነው። በመሆኑም ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች እንደ ባለስልጣን የሚታዩ ወይም የመንግስት መኪና የግል-ሀብታቸው አድርገው የሚቆጥሩ እንጂ እንደ ህዝብ አገልጋይና አገርን አሳዳጊና ብሄራዊ ነፃነትን አስከባሪ ሆነው የሚታዩ አልነበሩሞ፤ አይደሉምም። ባላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስታተስ በመዝናናት በመደሰት ህዝብን የሚንቁና አገርን ለውጭ የስለላ ኃይሎች አሳልፈው የሚሰጡና፣ አሁንም የሚሰጡ ናቸው  ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ሰፋ ያለና የተገለጸት ምሁራዊ ኃይልም ባለመኖሩ ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች ህዝባችንን እንዲገዙ ከአምላክ የተላኩ መስለው ስለሚታዩ የጥሬ-ሀብት በተትረፈረፈበት አገር ውስጥ ህዝባችን በድህነትና በረሃብ ዓለም ውስጥ እንዲኖር ተደርጓል። የመጨረሻም መጨረሻም ዛሬ እንደምናየው የጦርነት ሰለባ በመሆን ፍዳውን እያየ እንዲኖር ተገዷል።

ስለሆነም በየጊዜው ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች ቀድሞ የተዋቀረውን የመንግስት መኪና ዲሞክራሲያዊ ከማድረግ ይልቅ የባሰውኑ የጭቆናውን መሳሪያ በማጠናከር ህዝባችንን ረግጠው እንዲገዙ አስችሎአቸዋል። ከየካቲቱ የስድሳ ስድስት ዓ.ም አብዮት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት የመንግስቱ መኪና ትናንሽ ጭንቅላቶች ባላቸው ወይም መንፈሰ-አልባ በሆኑ ሰዎች የተያዘና የመንግስትን ሚና ባልተረዱ የሚበወዝና ንጹህ በንጹህ የካፒታሊዝምን ዕድገትንና፣ ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ እንዳይዳብር እንቅፋት የሆነ ነው። ስልጣንን የጨበጡ ሰዎች፣ ስለጥበብ አስፈላጊነትና ማህበራዊ ሚና፣ ስለ ሙዚቃ የሰውን መንፈስ አዳሽነትና አረጋጊነት፣ ስለሙዚየሞች መሰራት፣ ጥበባዊ የሆኑ ህንፃዎች ስለመሰራታቸው፣ ባጭሩ አንድ ማህበረሰብ እንደማህበረሰብ ተከታታይነት እንዲኖረው ምን ምን ነገሮች ከታች ወደላይ መሰራት እንዳለባቸው የሚያውቁት ነገር ስለሌለ አገራችንን በመጨቆኛ መሳሪያ ኃይል ብቻ ነው የሚገዙት። ይህ ዐይነቱ መንግስታዊ አውቃቀር ያለውን ኋላ-ቀርነት የባሰውኑ የሚያጠናክርና ህዝቡን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ ነው። ድንቁርናን የሚያስፋፋና ያለውንም የሚያጠነክር ነው። ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች በሙሉ በጭንቅላታቸው የሚያስቡ ባለመሆናቸው የመንግስትን መኪና የሚጠቀሙበት ህዝብን ለማገልገልና አገርን ታላቅ ለማድረግ ሳይሆን የራሳቸውን ዘመዶች ለመጥቀም ብቻ ነው። በአብዛዎች የሶስተኛው ዓለም አገሮች የሰፈኑትን ወይም የተዋቀሩ መንግስታትን አስመልክቶ በተገለጸላቸው የአውሮፓ ምሁራን በሰፊው የተጠናና የተተነተነ ነው። ይሁንና ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚቅበጠበጠው የአገራችን ምሁር ጠጋ ብሎ ከመመርመርና ከማጥናት ይልቅ በአጉል የኩራትና የጉራ ስሜት ወደፊት በመገስገስና ከአንዳንድ መልካም አስተሳሰብ ካላቸው ኢትዮጵያውያኖች የሚመጣውን አስተያየት ላለመስማት በመፈልግ በዚህና በሌሎች አያሌ ነገሮች ላይ ጥናትና ክርክር እንዳይደረግ በማድረግ ለዕድገት እንቅፋት ለመሆን በቅቷል። አሁንም በየቦታው የሚደረገውን የዙም ውይይት ሳዳምጥ በአብዛዎች ዘንድ የቱን ያህል ኋላ-ቀርነት እንደነገሰ ለመገንዘብ ችያለሁ። አብዮቱ ከፈነዳ ከአርባ ዓመት በኋላም በአተሳሰባችን አልተሻሻልንም። ሁሉም በየፊናው ስልጣንን በመጨበጥ እንዴት አድርጌ ያንን ምስኪን ህዝብ ማሽትና የውጭ ኃይሎችን ማገልገል እችላለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ እንጂ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግስታዊ መኪና በማዋቀር አንድ ታላቅ አገር ለመገንባት አይደለም የሚታገል የሚያስመስለው። ከዚህ ሁኔታ ስንነሳ በህወሃት ዘመንም ሆነ በዛሬው ዘመን በህዝባችን ላይ የሚወርደው ሰቆቃና ግድያ ይህን ያህልም የሚያስገርም አይደለም። ተራ የአካዳሚ ዕውቀትም ጭንቅላታችንን በማለስለስ ለስልጣኔ እንድንቆም አላደረገንም። አንዳንዶች መልካቸው የሚያማምሩ ቢመስሉም ጭንቅላታቸው ውስጥ ሰይጣን ያለ ይመስል የባሰውን አረመኔ መሆናቸውን እያረጋገጡልን ነው። ሲግሙንድ ፍሮይድ አንድ ቦታ ላይ እንዳለው በፊዚካል ውበትና በአስተሳሰብ ወይም ደግሞ በንቃተ-ህሊና መሀከል መጣጣም ሊኖር አይችልም፣ ወይም ደግሞ አንድ ሰው ቆንጆ በመሆኑ የግዴታ በባህርይውም ቆንጆ  ይሆናል ብሎ መገመት አይቻልም ያለው በአገራችን ምድር በግልጽ የሚታይና የሚረጋገጥ ሀቅ ነው። እንዲያውም አንዳንድ ባለስልጣናት ጭንቅላታቸው ወይም አስተሳሰባቸው በመልካቸው ስለሚሸፈን የማሰብ ኃይላቸው ይቀጭጫል።  ለጭንቅላታቸው መዳበርም ይህን ያህል ትኩረት ስለማይሰጡ የበለጠውን ወደ አረመኔነት በመለወጥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠርን ህዝብ ህይወት ያበላሻሉ። ታሪክንና ባህልን እንዳለ ያወድማሉ። የመጨረሻ መጨረሻም አንድ አገር በውጭ ኃይሎች እንድትወረር ሁኔታውን አመቻችተው ይሄዳሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትውልድን ተኮሮና ለማትረፍ ሸሽተው ይሩጡና ይደበቁ! - በላይነህ አባተ

ስለሆነም በዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ውስጥና የመንግስት አወቃቀር ምርጫ ማካሄድ ያለውን ኋላ-ቀርነትና የተዝረከረከ አኗኗር ዘዴ የባሰውኑ የሚያጠነክር እንጂ ተዓምር ሊፈጥር አይችልም። በአገራችን ምድር መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ የምንፈልግ ከሆነ መንግስት በሚባለው መሰረተ-ሃሳብ ላይና ዲሞክራሲያዊ ባህርይ እንዲኖረው ስለመደረጉ ጉዳይ በጥልቅና በስፋት መወያየት ያስፈልጋል። በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ክርክር ማድረግ አለብን። አሰልቺ ከሆኑ ታሪካዊ ሀተታዎችና፣ አገራችን እንደዚህ ነበረች ከሚለው አባባል መላቀቅና ለዕድገትና ለስልጣኔ በሚያመቹ ነገሮች ላይ ብቻ መወያየትና ማጥናት አለብን። አይ ይህ አያስፈልግም፣ የሚያስፈልገው የሰዎችና የህገ-መንግስት መለወጥ ብቻ ነው የምንል ከሆነ ከአሁኑ ባይ ባይ ኢትዮጵያ ብለን እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ አለብን።

 

       የፓርቲዎች አደረጃጀት ድክመትና እንዲሁም ለኢኮኖሚ  ዕድገት እንቅፋት የመሆን ጉዳይ!!

ትላንትም ሆነ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ፓርቲ አለን፣ ተደራጅተናልም ብለው ለስልጣን የሚታገሉትን፣ ወይም ለምርጫ እንወዳደራለን የሚሉትን ፓርቲ መሰል ነገሮች ስንመለከት የደቀቀ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ምሁራዊ መሰረት የሌላቸውና አንድ አገር እንዴት ከታች ወደላይ (Organically) እንደሚገነባና ህዝቡም እንደማህበረሰብ እንዴት መተሳሰር እንዳለበት የሚያውቁት አንዳችም ነገር የለም። ስለሆነም ስልጣን ቢጨብጡም በመጀመሪያ ደረጃ ምን ምን ነገሮች ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው የተረዱና ለመረዳትም የሚፈልጉ አይደሉም። ባለው የተጨማለቀ ነገር ላይ ኢ-ሳይንሳዊ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የስራ መስክ ከመክፈትና ድህነትን ከመቅረፍ ይልቅ ያለውን ሁኔታ የሚያባብሱ ይሆናሉ። በተለያዩ የኢኮኖሚ ቲዎሪዎችና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች መሀከል ያሉትን ልዩነቶች ስለማይረዱ በቀላሉ በዓለም አቀፍ ተቋማት በመመከር የባሰውኑ ድህነትን የሚያመጡና ሀብት እንዲባክን የሚያደርጉ ይሆናሉ። በአገራችን ያለው የፓርቲዎች ድክመት የምሁሩም ድክመት ነፀብራቅ ነው ማለት ይቻላል። ምሁሩ ከራሱ ወጣ ብሎ ሰፋ ያለ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነና ፍላጎትም ያለው አይደለም። ሰነፍና ባለው ዕውቀት ስለሚዝናና ምሁራዊ ብስለት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው። አስተሳሰቡና አካሄዱ በሙሉ ለዕድገት እንቅፋት ነው። ለማዳመጥ፣ ለመከራከርና ለማስተማር ዝግጁ አይደለም። አብዛኛውም ምንም ዐይነት አቋም የለውም።  በሌላ ወገን ደግሞ ዛሬ ለስልጣን እንወዳደራለን ብለው ከተመዘገቡት ውስጥ አንዳንዶችም ሆነ ውጭ አገር ሆነው የሚጮሁት በአንድ ወቅት ወንጀል የሰሩና ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ያሰቃዩ የነበሩ ናቸው። በአውሮፓ ፓርቲዎችም ሆነ በምሁራን ታሪክ ውስጥ አቋመ-ቢስ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የለም። ሁሉም ለቆመበትና ላመነበት ዓላማ የሚታገል ነው። በደም ፍላትና ሌላውን በመወንጀል የሚራወጥ ሳይሆን በሳይንሳዊ ግንዛቤ የራሱን ትንተና ለመስጠት የሚሞክር ነው። የአገራችንን የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምሁሩን አስተሳሰብ በምንመረምርበት ጊዜ አብዛኛው በመጯጯህ ጊዜውን የሚያባክን እንጂ አቋሙን በጽሁፍ ለማስረዳት የሚሞክርና በክርክር ለማሳመን የሚጥር አይደለም። ይህንንም ሆነ ያኛውን ፓርቲ ወይም ግለሰብ እንደግፋለን የምንልም በራሳችን ዕምነትና አስተሳሰብ የምንመራ ሳንሆን የምንነዳና በቀላሉ የምንኮራረፍ ነን። ስራችን ሁሉ እንድንፋጠጥና እንድንጨራረስ የሚያድርግ ነው። መንፈሳችን የተረበሸና ወደ ቂም በቀል የሚያደላ ነው። ስለሆነም ስልጣንን የሚጨብጥ ኃይል ሁሉ ከምሁራዊ አስተሳሰብና ብስለት በመነሳት ሳይሆን ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ወይም ሌሎች እርምጃዎችን ተግባራዊ የሚያደርገው ተበድዬ፣ ተጨቁኜና ተዋርጄ ነበር በማለትና ተገርፎ እንዳደገ ሰው የተራዬን ቁጭቴን መወጣት አለብኝ በማለት ነው። በመሆኑም ፖለቲካ የቂም በቀል መውጫ፣ የተንኮል መስሪያ፣ አገርንና ባህልን ማከረባበቻና የመጨረሻ መጨረሻም የሚቀናቀነውን ሁሉ ማጥፍያ መሳሪያ ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በእነዚህ ዐይነት ሰዎች ዕምነት ፖለቲካ ከሞራል ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፣ ወይም ደግሞ ስለሞራል የሚያውቁት ነገር የለም።  ይህ ዐይነቱ ደመ-ፍላት በከፍተኛ ምሁራዊ እንቅስቃሴ መገታትና መድረኩ የግዴታ ሰፋ ላለ ለፍልስፍና፣ ለቲዎሪና ለሳይንስ ክርክር ክፍት መሆን አለበት። የአንድ አገር ችግር በአጉል ትረካ የሚፈታ ሳይሆን በሳይንሳዊና በፍልስፍናዊ የአነባበብና በቲዎሪ የአተናተን ዘዴ ብቻ ነው። ትክክለኛ ፍልስፍናና ሳይንስ መመሪያችን ሲሆኑ ብቻ ነው ተጨባጭ ሁኔታዎችንም ማንበብ የምንችለውና በተጨባጭ ለሚታየው ችግርም ተቀራራቢ መፍትሄ ማቅረብ የምንችለው። ይህ ዐይነት ሁኔታ በሌለበት አገር ውስጥ የአገራችን የተወሳሰበ ችግር በተራ ምርጫ ብቻ ሊፈታ ይችላል ብሎ መገመት የዋህነት ነው።

ለምርጫ እንወዳደራለን ብለው በምርጫ ቦርዱ የተመዘገቡትን የፓርቲዎች የሞራል ብቃት ሁኔታ ስንመለከት አብዛኛዎቹ ምንም ዐይነት የሞራል ብቃት ያላቸው አይደሉም። በመጀመሪያ ደረጃ በአገራችን ምድር እየኖሩ በምድር ላይ የሚታየውን ተጨባጭ ሁኔታዎች ማንበብና መተንተን የሚችሉ አይደሉም። ህዝባችን በምን ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖር በየቦታው እየተንቀሳቀሱ የሚጎበኙ አይደሉም። በእግራቸው ስር ያለውንና የሚታየውን ነገር እንኳ ማየት የማይችሉና ጥያቄም ለማቀረብ መንፈሳቸው የተዘጋጀ አይደለም።  በተለይም በአዲስ አበባ ውስጥ አብዛኛው ህዝብ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መኖሩ እየታወቀ እየተዘዋውሩ በማየት ኗሪው ህዝብ ከዚህ ዐይነት አስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለወጥ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ ሲወያዩና በመንግስትም ላይ ግፊት ሲያደርጉ አይታይም። ከዚህም ባሻገር በዶ/ር አቢይ የተዋቀረው አገዛዝ ስልጣንን ከተረከበ ጀምሮ በህዝባችን ላይ፣ በተለይም በአማራው ወገናችን ላይ የግድያና የማፈናቀል እርምጃ ሲወሰድ ይህንን ዘግናኝ ድርጊት በመኮነን ማንነታቸውን አላስወቁም። ለዲሞክራሲና ለሰብአዊ መብት መከበር ጠበቃ መሆናቸውን አላረጋገጡም። እንዲያውም ምንም ዐይነት ወንጀል እንዳልተፈጸመና እንደማይፈጸም ከአገዛዙ ጋር አብረው ሲቀመጡና ተጋብዘው ሲበሉ ይታያሉ። በህዝባችን ላይ የሚፈጸመውን ወንጀልና ዘግናኝ ድርጊት ለሰፊው ህዝብ በማሳወቅ ህዝቡ ወጣ ብሎ ድምጹን እንዲያሰማና ድርጊቱ እንዲቆም የሚወስዱት እርምጃ የለም። አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ነን ባዮች የድርጊቱ ተባባሪዎች ይመስል ዝም ብለው የሚመለከቱ ናቸው። ከአገዛዙ ጋር ውስጣዊ ስምምነት(Tacit Agreement) ያላቸው ይመስላል። ታዲህ በዚህ ዐይነት ቀውጢ ጊዜ ጩኸቱን ያላሰማ ፓርቲ በምን ተዓምር ነው በምርጫ ተወዳድሮ  ቢያሸንፍ እንኳ ዐይነተኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው? ባጭሩ ፓርቲዎች ለምሁራዊና ለሰብአዊ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ለሚመሰረት ሰፋ ላለ ኢኮኖሚ እንቅፋት የሆኑ ናቸው ማለት ይቻላል። በአገራችን ምድር ኢ-ሳይንሳዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲደረግ ይህ ነገር መስተካከል አለበት፣ ወይንም እንደዚህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሰፋ ላለ ሰፊውን ህዝብ ሊጠቅም የሚችል ለሀብት ፈጠራ የሚስማማ አይደለም ብለው መንግስትን ሲያፋጥጡ አይታይም።

ቀደም ብዬ ለማሳየት እንደሞከርኩት በአውሮፓ ምድር ፓርቲዎች ከመቋቋመቸው በፊት ከተማዎችና መንደሮች በደንብ ተገንብተዋል። ከተማዎችና መንደሮች በልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተሳስረዋል። ሰፋ ያሉ ተቋማትና የባህልም ማዕከሎች ተገንብተዋል። ከረጅም ጊዜ የካፒታሊዝም ዕድገት በኋላ ፓርቲዎች ሲመሰረቱና ለምርጫም ሲወዳደሩ አዳዲስ ከተማዎችን የሚመሰርቱና ተቋማትን የሚገነቡ ሳይሆን ያለውን የሚያሻሽሉ ናቸው። በኢኮኖሚ ፖሊሲም እንደየ ኃይል አሰላለፋቸው የተለያየ ዐይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የውስጥ ገበያው እንዳይረበሽ የሚያደርጉ ናቸው። ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ሁሉም ነገር ከዜሮ በመነሳት ነው መሰራትና መገንባት ያለበት። መንደሮችንና ከተማዎችን በአዲስ መልክና ሰው እንዲኖርባቸው አድርገን መገንባት አለብን። ግልጽነት ያለው የኢኮኖሚ አደራጃጀት ማዋቀር አለብን።  የጥሬ-ሀብትንና የሰውን ጉልበት ለማንቀሳቀስና ተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ብቃቅትነት ያላቸው ተቋማት በየቦታው መገንባት አለብን። ለዚህ ደግሞ አዲስና ታግቶ የሚሰራ፣ ሞራላዊ ብቃትነት ያለው የተማረ የሰው ኃይል ማሰልጠን ያስፈልጋል። በአጭሩ ተከታታይነት የሚኖረው ከአንድ ትውልድ ወደሚቀጥለው ሳይረበሽ የሚተላለፍ ስርዓት መመስረትና በየጊዜው ማሻሻል ያስፈልፍጋል። ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንነሳ ስልጣንን የጨበጠው ብልጽግና የሚባለውና ሌሎችም ብቃትም ሆነ ችሎታ ያላቸው አይመስሉም። ከዚህ ሁኔታ በመነሳት ነው በብልጽግና ዘመን ያለውን፣ ያየነውንና ህዝባችንም የቀመሰውን የመረረ ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን መመርመር የምንችለው።

 

ዘመነ-ብልጽግና ወይም ዘመነ ሰቆቃ!

በዶ/ር አቢይ የሚመራው አገዛዝ ስልጣንን ከጨበጠ ከሶስት ዓመት በላይ  አስቆጠረ። ዶ/ር አቢይ በመጀመሪያው አንድ ዓመት ህዝባችን በብዛት የሰጣቸውን ድጋፍ መሰረት በማድረግ ስርዓት ያለውና ህዝባችንን ለዕድገት በአንድነት የሚያነሳሳው የተቋም ማሻሻያና ሌሎች ስር-ነቀል እርምጃዎችን ሲወስዱ አልታዩም። ፓርኮችን ከመስራትና በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ እንደ ቴሌና አየር መንገድ የመሳሰሉትን በመንግስት ስር ያሉ የአገልግሎት ተቋማትን ለውጭ ኩባንያዎች በድርሻ ለመሸጥ ጉድ ጉድ ከማለት በሰተቀር ከህውሃት የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመላቀቅ ሰፋ ያለ የስራ መስክ ሊከፍትና አገሪቱንም በጸና መሰረት ላይ እንድትገነባ የሚያደርግ የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርጉ አይታይም። ይባስ ብለው አገራችንን በመዕለ-ነዋይ ስም ለአረቦችና ለተቀሩት የውጭ ባለሀብቶች ለመሸብሸብና የጨለማውን ዘመን ለማራዘም ደፋ ቀና ብለው ሲሰሩ ነው የምናየው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ... " እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም " 

ወደ መንግስት መኪናው ጋ ስንመጣም እስካሁን ድረስ ሳይታክቱ የሰሩት የአንድ ሰው አምባገነንነት እንዲነግስ ነው። በመሆኑም የህውሃት አገዛዝ በሌላ ዐይነት አገር አፍራሽና አፋኝ ስርዓት የተተካበትን ሁኔታ በግልጽ እንመለከታለን። መንግስታዊ አወቃቀሩ ወደ ፋሺሽታዊነት እየተለወጠና ህዝባችንም በፍርሃት የሚኖርበትን ሁኔታ እንያለን። በብልጽግና ስም የተደራጀው ፓርቲ ነኝ ባይና የመንግስቱ መኪና አንድ ላይ የተያያዙ እንጂ መንግስት የሚባለው የህዝብ አገልጋይ መኪና በአውቶኖመስ ደረጃ የሚንቀሳቀስና ኃላፊነቱን የሚወጣ አየደለም። የአገዛዙንም አወቃቀር ስንመለከት በኤክስኩቲቩ፣ በህግ አርቃቂውና በህግ አስፈጻሚው መሀከል ግልጽ የሆነ የስራ ክፍፍል የለም። ፓርላሜንት የሚባለውም ምንም ሚና ስለሌለው ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሌክቸር የሚሰጡበት መድረክ ወደመሆን ደርሷል። በትክክል ለመናገር በአገራችን ምድር ዲስፖታዊ አገዛዝ ተመስርቷል ማለት ይቻላል። በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን “ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ” የሚለው አነጋገር ዛሬም የሚሰራበት ለመሆን በቅቷል። ለምሳሌ በአንድ የኢኮኖሚ ስብሰባ ላይ ተገኝተው አንዱ የዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ምሁር ስለቴሌ በድርሻ መልክ መሸጥ ጠቃሚ አይደለም፣ እንዲያውም  ጎጂ ነው ብሎ ለማስረዳት ሲሞክር ለምንድነው እስቲ ዘርዘር አድርገህ አስረዳን ከማለት ይልቅ “ወስነናል” በማለት ነው በማስፈራራት መልስ የመለሱለት። ጠቅላይ ሚኒስተሩና የካቢኔት ሚኒስተሮች ሁሉንም ነገር በራሳቸው የሚወስኑና የኒዎ-ሊበራልን ፖሊሲ በሚያራምዱ በእርንስት ኤንድ ያንግ (Ernst and Young) በመሳሰሉት አገር አፍራሽ ድርጅቶች የሚመከሩ ናቸው። በኢኮኖሚክስና በፋይናንስ ሚኒስተር ውስጥ በሚኒስተር ዴኤታነት ተቀጥረው የሚሰሩት ተጠሪነታቸውና አገልጋይነታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለዓለም ባንክ ነው።፡ ደሞዛቸውም በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ነው። ይህም ማለት እነዚህ ሰዎች በተጨባጭ ለውጭ ኃይሎች የሚሰሩ እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅምና የአገራችንን ኢኮኖሚ ሰፋ ባለ መሰረት ለማዋቀር አይደለም።  ጠቅላይ ሚኒስተሩና የካቤኔ ሚኒስተሮችም በህገ-መንግስቱ መሰረት በፓርሊያሜንቱ ፊት የማይጠየቁና በፓርሊሜንታሪ አጣሪ ኮሚቴም ስራቸው የሚመረመርና የሚጣራ አይደለም። ከዚህ ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስተሩ እጅግ  ወደ ኋላ የቀረ አስተሳሰብ ባላቸው እንደነ አባዱላ፣ ሌንጮ ባቲና ሌሎች ፀረ-ዲሞክራቲክ ኃይሎች የሚመከሩ ናቸው። በዚህ መልክ በተዋቀረና በአድሃሪ ሰዎች ከተከበበ አገዛዝ ዲሞክራሲንና ፍትሃዊነት ያለውን አስተዳደር መጠበቅ በፍጹም አይቻልም። ወደሌሎች ጉዳዮችም ስንመጣ ፖሊሶች ለፍርድ ቤት የሚታዘዙ አይደሉም። ፍርድቤት አንድ እስረኛ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ሲሰጥ ፖሊስ አልለቅም እያለ ግብግብ የሚፈጥርበትን ሁኔታ እንመለከታለን፤ እንሰማለንም። አንዳንድ አካባቢም፣ በተለይ በኦሮምያ ክልል ዳኞች በፖሊሶች እንደሚደበደቡ ይነገራል። ሰሞኑን እንደሰማነውና በቪዲዮም እንደተመለከትነው አንድ የአስራስምንት ዓመት ወጣት ወንጀል ሲሰራ ተገኝቷል በማለት በፖሊሶች ተደብድቦ በጥይት እንዲገደል ተደርጓል። ፖሊሶች በግልጽ ሰውን እንደዚህ በጠራራ ፀሃይ ላይ ሲደበድቡና ሲገድሉ የክልሉ መንግስት ዝም ብሎ ይመለከታል። የኦሮሞ ኮንግረስ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ሙላቱ ገመቻ ኢትዮ ኒውስ ለሚባለው ሚዲያ ላይ ቀርበው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ በኦሮምያና በሌሎች ክልሎች ከፍርድቤቶችና ከአቃቤ ህጎች ይልቅ ፖሊሶች የበለጠ ስልጣን ያላቸውና በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ለምን ፍርድ ቤቶች እንደሚያስፈልጉ ነው በዝርዝር ያስረዱት። በእሳቸውም አባባል በደርግ የአገዛዝ ዘመን በቀይ ሽብር ወጣቱ በጠራራ ፀሀይ እንደሚገደል ሁሉ ዛሬም በተለይም በኦሮምያ ክፍል ተመሳሳይ ድርጊት እንደሚፈጸም ተናግረዋል። ይህ ሁሉ ምንድነው የሚያረጋግጥልን?  በዚህ ዐይነት ፈሺሽት መሰል አገዛዝ ሁኔታ ውስጥ  የምርጫ ማድርገ ትርጉሙ ምን ላይ ነው?

ከዚህ ወጣ ብለን ስንሄድ የዶ/ር አቢይ አገዛዝ በቤናሽጉልና በምዕራብ ወለጋና ቀደም ብሎ በሻሸመኔ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲካሄድና ሀብትም ሲወድም ዝም ብሎ የተመለከተ ነው። ሰሞኑን ደግሞ በካራቆሬ፣ በሸዋ ሮቢትና በአልጣዬ በተደራጀ መልክና በዘመናዊ መሳሪያ በመታጠቅ የብዙ መቶ ዓመታት ከተማዎች ሲወድሙና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ መንግስት ዝም ብሎ የተመለከተ ነው። አንዳንድ ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ራሱ በዶ/ር አቢይ የሚመራው አገዛዝ እጁ እንዳለበት ነው።  ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልክ አንዳንድ ጄኔራሎች ለማስተባበል ሞክረዋል። እነዚህ ጄኔራሎች ከአማራ ልዩ ኃይልና ከፋኖዎች ጋር በመሆን በጦር ሜዳ ላይ ጥሩ ውጤት  ቢያስመዘግቡም፣ በወለጋ፣ በመተክል፣ በሸዋ ሮቢት፣ በካራቆሬና በአጣዬ ላይ የደረሰውን ግፍ የመመልከት ኃይል አልነበራቸውም። ወይም ራሳቸው ተባባሪ ይመስል የተጠረጠረውን ጄኔራል ይህንን ሊያደርግ አይችልም ብለው ጠበቃ ሲቆሙ ታይቷል። ይሁ ሁሉ ነገር የሚያረጋግጠው እነዚህ ጄኔራሎችም ሆነ የመንግስትን መኪናን የሚቆጣጠረው አገዛዝ  ሞራላዊና ምሁራዊ ብቃትነት እንደሌላቸው ነው። የተወሳሰበውን የህብረተሰባችንን አገነባብና ዛሬም አገራችን ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ በመረዳት በምሁራዊ መነጽር በመመልከት ጥበብ የተሞላበት ፖለቲካ ማካሄድ የማይችሉና አገራችንና ህዝባችንን ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጡ ናቸው። በተለይም ሱዳን የፈጸመችውን ወረራና መሬት መያዝ አስመልክቶ የሚሰጡትን ገለጻና ዝም ብሎ መመልከት ስንከታተል የዶ/ር አቢይ አገዛዝና አንዳንድ ጄኔራሎች ለኢትዮጵያችን ሳይሆን ለሱዳን ጠበቃ የቆሙ ነው የሚያስመስለው። ነገሩን በጥብቅ ለተከታተለ ሱዳን ጦር ስትከፍትና መሬት ስትቆጣጠር ዝም ብሎ መመልከት የዶ/ር አቢይ አንደኛው ስትራቴጂ የአማራን ልዩ ኃይልና ህዝቡን ማዳከም ይመስላል። በአገዛዙ ዘንድ፣ በተለይም ደግሞ ኦሮሞ የበላይነትን መጎናጸፍ አለበት ብለው በሚያምኑት ዘንደ አማራ በሁሉም አኳያ መወጠርና መዳከም አለበት የሚል አስተሳሰብ የነገሰ ይመስላል።

ወደ ክልል አገዛዞች ስንመጣ አሮምያን አስተዳድራለሁ የሚለው አምባገነናዊ አገዛዝ እራሱን እንደ ነፃ መንግስት የሚመለከትና በሌሎች ክልሎች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሰውን እስከመግደል ድረስ የሚደርስ ነው። በኦሮምያ ክልል ብቻ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚቆጠር እዚያው ተወልዶ ያደገ ከአማራው ብሄረሰብ የተውጣጣ የህብረተሰብ ክፍል አለ። ሌሎች ብሄረሰቦችም ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ በሚኖሩበት አካባቢ እንደሁለተኛ ዜጋ የሚታዩና መጤ እየተባሉ የሚንገላቱና የሚፍናቀሉና በፍርሃትም የሚኖሩ ናቸው።  በመሰረቱ ዛሬ ኦሮምያ ተብሎ የተካለለው ቦታ ኦሮሞዎች የሚኖሩበት አልነበረም። በ16ኛው ክፍለ-ዘመን ኦሮሞዎች በተስፋፊነት የያዟቸው ቦታዎች ናቸው። ኦሮሞዎች ከመስፋፋታቸው በፊት በ14ኛውና በ15ኛው ክፍለ-ዘመን በተለይም ከአማራው ክፍል ሃይማኖትን ለማስፋፋት ተብሎ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች እየተሰማሩ ያስተምሩና አካባቢውን ያለሙ እንደነበር የታወቀ ጉዳይ ነበር። እዚያም ተዋልደው ለብዙ መቶ ዓመታት ከትውልድ ትውልድ እየተራቡ የመጡ ናቸው። አብዛኛዎቹ በደቡቡ ክፍል የነበሩ አገዛዞችም ለክርስቲያኑ አገዛዝ ግብር የሚከፍሉ ነበሩ። ይህ ሁሉ ነገር በግልጽ በማስረጃ መልክ ተጽፎ እያለና አፄ ምኒልክም ግዛታቸውን ዘመናዊ ለማድረግ የጥገና ለውጦች ያደረጉትን እንደወንጀል ተቆጥሮ በትረካ ላይ በመመስርት በተለይም በአማራው ወገናችን ላይ እንደዚህ ዐይነት አሰቃቂ እርምጃ መውሰድ አሁን ባለንበት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘመን መደረግ የነበረበት ተግባር አልነበረም።  የሚያሳዝነው ነገር ግን በኢትዮጵያ ምድር ተወልደውና አድገው፣ ትምህርትቤት ሄደውና በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ተምረውና ተመርቀው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱት የድሮዎችን አገዛዝና ህዝባችንን ከማመስገን ይልቅ ያስተማራቸውን ህዝብ ሲገድሉና ሲያባርሩ ስናይ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ አላቸው ወይ? ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን። መማረርና መቆጨት የነበረበት ደሃው ገበሬ ነበር። ይሁንና እነዚህ ተንደላቀው ያደጉ በአጉል ትረካ ጭንቅላታቸው ስለተቀረጸ ኢትዮጵያን እንዳለች መበወዙን ተያይዘውታል። ማንኛውም ነገር ከእኛ ፈቃድ ውጭ መደረግ አይችልም በማለት ሁሉንም ነገር ወደ መቆጣጠር አምርተዋል።

ያም ሆነ ይህ በብልጽግና የአገዛዝ ዘመን አገራችንና ህዝባችን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቀዋል። ህዝባቸን በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ወድቋል። ጠዋት ወጥቶ ማታ ተመልሶ ቤቱ ለመግባቱ እርግጠኛ አይደለም። በተለይም ዲሞግራፊውን መለወጥ ያስፈልጋል በሚል ስም በአላዋቂዎች አዲስ አበባ ውስጥ በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከባላገር አምጥቶ ማስፈር  ከተማይቱን የኪስ አውላቂዎች፣ የማጅራት መቺዎችና የገዳዮች መናኸሪያ አድርጓቷል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ እነ ሺመልስ አብዲሳ የዛቱት ነገር ተግባራዊ ይሆናል ማለት ነው። ይኸውም አዲስ አበባን ትርጉም እንዳይኖራት ማድረግ። የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውና ከጄኔባ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ የምትቆጠረው አዲስ አበባ ትርጉሟን የምታጣበት ጊዜና፣ እነዚህ ተቋማትና የአፍሪካ አንድነት መቀመጫቸውን ወደሌላ የአፍሪካ አገር የሚያዛውሩበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ማለት ነው። ዶ/ር አቢይና የኦሮምያ ክልል አስተዳዳሪዎች ይህንን ዕውን ለማድረግ ሌት ተቀን የሚሰሩ ነው የሚመስለው።

ከዚህ አጠር መጠን ያለ ሀተታ ስንነሳ በዛሬው ወቅት ምርጫ ማካሄድና በምርጫ መሳተፍ፣ እንዲሁም ለምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ላለው አሰቃቂና አገርን አፍራሽ አካሄድ ዕውቅናን እንደመስጠት ይቆጠራል። ምርጫው ቢካሄድ በእርግጥ “በአሸናፊነት” ሊወጣ የሚችለው ብልጽግና የሚባለው ሞራላዊና ምሁራዊ ብቃት የሌለው ፓርቲ ነኝ ባይ ነው። እደምናየው አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ቢሮዎች የሏቸውም፤ በየቦታው እየሄዱም ቅስቀሳ ለማድረግ አይችሉም። ይህም ማለት ምርጫው በሰላምና በግልጽነት የሚካሄድ አይሆንም ማለት ነው። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ አሸናፊ ነኝ ብሎ የሚወጣው ብልጽግና የሚባለው የጨለማውንና የሰቆቃውን ዘመን የሚያራዝመው የዶ/ር አቢይ ፓርቲ ይሆናል ማለት ነው። ስለሆነም በዚህ ዐይነት ግልጽነት በሌለበት፣ ሰላም ባልሰፈነበት፣ ግድያና መፈናቀል በተስፋፋበት አገር ውስጥ ምርጫ ማካሄድ በታሪክና በህዝብ ላይ እንደ መቀለድ ይቆጠራል። በሌላ ወገን ደግሞ ራሱ የብልጽግና ፓርቲ ነኝ የሚለው ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ስምንት ፖሊሲ ነክ በሆኑ ነገሮች፣ ማለትም በስራ-አጥነት፣ በኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ በመንግስት ሚና፣ በብሄራዊ ደህንነትና በሰላም ጉዳይ ላይ፣ በትምህርት ፖሊሲ ላይ፣ በማህበራዊ ፖሊሲና በህገ-መንግስቱ…ወዘተ. … ወዘተ. ላይ ጊዜ የለኝም በማለት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመከራከር ፈቃደኛ እንዳይደለ አስታውቋል። በተለይም አቶ ዛዴግ አብርሃ የብልጽግና አመራር አካል የሆኑት ግልጽ በሆኑ ፖሊሲ ነክ ጉዳዮች ላይ በሰው ፊት ቀርቤ ለመከራከር ፈቃደኛ አይደለሁም በማለት በግልጽ ተናግረዋል። በሌላ ወገን ግን የብልጽግና ፓርቲ በየቦታው እየተዘዋወረ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ ይታያል። ይሁንና ግን አብዛኛው ህዝብ ማንበብና መጻፍ በማይችልበት አገርና የየፓርቲዎችን ፕሮግራምና ፖሊሲዎችን  አንብቦና ተረድቶ የራሱን አስተያየትና ፍርድ ለመስጠት በማይችልበት አገር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ከፍተኛ የታሪክ ወንጀል እንደመስራት የሚቆጠር ነው።

ከዚህ ሁኔታ ስንነሳ በተለይም እዚህ አውሮፓና አሜሪካ እየኖሩ ምርጫ መካሄድ የለበትም ብለው የሚጽፉትን የሚሳደቡ አንዳንድ ምሁራን ነን ባዮች ያሉበትን ቦታ የማያውቁና በ21ኛው ክፍለ-ዘመንም እንደሚኖሩ ያልተገነዘቡ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች በዶ/ር አቢይ ፍቅር ያበዱ ይመስላሉ። የሰውየው ስም ሲነሳ ያንቀጠቅጣቸዋል። ፍቅራቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከአንድ ሰው ጋር ነው። ዋና አለማቸውም አዲስና ያደገች፣ እንዲሁም ዲሞክራሲያዊት አገርን ማየት ሳይሆን ለማኝንና የምትበታተንን አገር ነው። ይህንን ጉዳይ አውጥተው ባይናገሩም ተጨባጩን የአገራችንን ሁኔታ ለማየት አለመቻላቸውና በአንድ ግለሰብ ፍቅር መታወራቸው  እንደዚህ ብሎ ከመደምደም በስተቀር ሌላ ነገር ማለት አይቻልም። ስለሆነም በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምርጫ ማካሄድ በአገራችን ምድር ዲሞክራሲ እንዳያብብ፣ ዘመናዊ ተቋማት እንዳይገነቡ፣ ሰፊውን ህዝብ ከድህነትና ከለማኝነት የሚያላቅቀው ወደ ውስጥ ያተኮረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዳይሆን፣ የኢኮኖሚው መሰረት ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዳይሆን ማድረግ፣ ቆንጆ ቆንጆ ከተማዎችና ለሰፊው ህዝብ የሚሆን ከአገራችን የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማሙ ቤቶች እንዳይሰሩ፣ ባጭሩ በአገራችን ምድር ሰፊው ህዝብ ማንነቱን እንዲገነዘብና በአዲስ መንፈስ በመነሳሳት አገሩን በአዲስና በጸና መሰረት ላይ እንዳይገነባ መሰናክል እንደመፍጠር ይቆጠራል። መልካም ግንዛቤ!!

 

          [email protected]

www.fekadubekele.com

                                          https://anchor.fm/fekadu-bekele-negussie

                                  https://www.youtube.com/watch?v=zK-GT5twTHQ

Bekele, Fekadu;    African Predicaments and the Method of Solving them

effectively, Berlin, 2016

 

15 Comments

 1. ዶክተር
  ከዚህ በፊት ብዙ ብዙ ነገር ሲጽፉ አስተውያለሁ። በጣም ረጃጅም ጽሁፎች። ከታዘብኩት ግን አንድም ሰው በርስዎ ጽሁፎች ላይ ኮሜንት ሲያደርግ አላየሁም። – እኔ እንኳ ጽሁፎቹ ከአቅሜ በላይ ስለሚሆኑብኝ እንክዋን ኮመንት ማድረግ ማንበቤ ራሱ ድፍረት ይሆንብኛል ብየ ነው። አሁን ከማስተማሩ ወጡና ግልጽ ወገንተኛ ሆነው መጡ፣ ያውም “more catholic than the pope” ሆነው፣ መብትዎን አከብራለሁ። ግን ግን…….
  ምርጫ እኮ የሚካሄደው የግድ ያለውን መንግስት ለመጣል አይደለም። እነ አብን፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች “ዉጡና ካርድ ውሰዱ፣ በምርጫው ተሳተፉ” እያሉ በሚቀሰቅሱበት ሰአት እርስዎን “ምርጫ አትሳተፉ” ብሎ ለመቀስቀስ [ከይቅርታ ጋር] ውክልናውን ከየት አመጡት? በአሁኗ ደቂቃ “ምርጫ አያስፈልግም” የሚሉት እኮ ባልደራስ [እየተሳተፈም ቢሆን] እና የሻለቃው ተከታዮች ብቻ ናቸው። ይተዉ፣ እርስዎ የተማሩ፣ የተመራመሩ አይደሉም እንዴ? ከፕ/ር ጌታቸው በጋሻው ትምሀርት ዉሰዱ እንጂ። በስሜት ወጡና የኔ አይነት ተራ ሰው የሚያቦካውን ሁሉ እንደማስረጃ እየቆጠሩ “አሳምነውን ያስገደለው አቢይ ነው”፣ “አቢይ የኦሮሙማ አራማጅ ነው” እያሉ ሙልጭ አድርገው ጥንብ እርኩሱን ካወጡ በኋላ በዚያው ጠፉ። በዚህ ከቀጠሉ እርስዎም እንደዚያው መሆንዎ አይቀርም።
  ይቺ አረፍተ ነገር ትኩረቴን ሳበች፣
  “ይሁንና ግን አብዛኛው ህዝብ ማንበብና መጻፍ በማይችልበት አገርና የየፓርቲዎችን ፕሮግራምና ፖሊሲዎችን አንብቦና ተረድቶ የራሱን አስተያየትና ፍርድ ለመስጠት በማይችልበት አገር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ከፍተኛ የታሪክ ወንጀል እንደመስራት የሚቆጠር ነው።”
  ትንሽ የተምታታ ነገር አለው፤ “…የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ…” ነው የታሪክ ወንጀል የሚሆነው ወይስ “…..ምርጫ ማድረግ በራሱ ነው ታሪካዊ ወንጀል የሚሆነው?’ እያሉን ያሉት “ያልተማረ ህዝብ ስለሚበዛ ምርጫ አያስፈልግም” ነው። ምርጫን ነው ማስቀረት የሚቻለው እንጂ የምርጫ ቅስቀሳን ሊሆን አይችልማ! ሌላው የአውሮፓና የአሜሪካ ምሳሌዎን ይተውን። እዚሁ አፍሪካ ዉስጥ ካሉን እነ ጋና፤ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ቦትስዋና ወዘተ እንማራለን
  “ጽድቁ ቀርቶብኝ በአግባቡ በኮነነኝ” አሉ እማማ አረጋሽ።
  በምርጫ ብቻ!

  • ከድር ሰተቴ ይህን ጥልቅ የሆነ ጽሁፍ ለማንበብ ከመጀመሬ በፊት የዚህን ወገን ሀሳብ ለማጣጣል ስናይፐርህን አቀባብለህ እንደምትጠብቅ አልተጠራጠርኩም ነበር። በበኩሌ ምርጫን አልጠላም ይህም ጥግ የደረሰ ምሁርና ለሀገሩ ዘወትር ጥብቅና የቆመ አንተ በምትልከው ፈገግ ይል እንደሆን እንጅ ከግምት አይወስደውም ለማንኛውም የእውቀት አስተዋጽኦ ያደረገውን ሁሉ ኦሮሙማን ነኩብኝ ብለህ አትጨርግደው ይህን ወንድማችንን እዛ ብታገኘው ምን ልታደርጉት እንደምትችሉ መገመት አይከብድም።
   እንዲህ ምርጫ ምርጫ ብለህ ልብህ የደከምከው ፓርላማ ገብተህ መተዳደሪያህን ልታደርገው ይሆናል ይቅናህ ወዳጄ ሰውን ግን ጨርግደህ ጨረስከው ክብር ለሚገባቸው ክብር ብትሰጥ ጥሩ ነው።

   • አያ ሰመረ ዋናው ምርጫዉን አለመጥላትህ ነው። አብን ዉጡና ምረጡ እያለ አንተ ለምንስ ትቃወማለህ? ምርጫዋ እስክታልፍ ታገስ። ከዚያ በኋላ የግለሰብ ሃሳብ በሙሉ “የቁራ ጩኅት” ስለሚሆን፣ መሰላቸቱም ይመጣና ዘሃበሻም ይዘጋል። እስከዚያው ግን
    በምርጫ ብቻ!

 2. ለአቶ ከድር ሰተቴ፡
  የውክልና ጉዳይ ከተነሳማ እርስዎም ከላይ የለጠፉትን አግቦኛ መጣጥፍ ማን ውክልና ሰጥተዎት ነው?ያስብላል።ይህን ይተውት እና ኢትዮጵያዊ መሆን በራሱ በቂ ነው።ብቃት የሌላቸው ሰዎች ቡቁ ለሆኑ አገር ወዳዶች የመንግሥቱን መኪና መልቀቅ ግድ ይላል።እስከዛሬ ድረስ የታየው ግንዛቤ ግን ምሁሮችን ያገለለ አካሄድ ነው።ዶክተር ፍቃዱ የአውሮፓን ሥልጣኔ አንዳለ ይወሰድ ያሉበትን አጋጣሚ አንድም ቦታ አላጋጠመኝም። የሚወጠን ነገር ሁሉ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተመርኩዞ የአገርን ዕሴት እያለሙ ዘለቄታ ባለው ሁኔታ መሥራት ማስፈለጉን ነው የመከሩት፝። “አውቆ የተኛን መቀሰቀስ” እንዳይሆን ቅንነት ልናዳብር ይገባል ባይ ነኝ።

  • “ምርጫ ይተላላፍ” የሚል የቀረው ፓርቲ ባልደራስ ብቻ ነው። ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች፤ አብንን ጨምሮ “ዉጡና ተምዝገቡ፤ ምረጡ” እያሉ ባሉበት ምን ውክልና ያስፈልገኛል?
   ይችን ልጨምር፤
   “ብቃት የሌላቸው ሰዎች ብቁ ለሆኑ አገር ወዳዶች የመንግሥቱን መኪና መልቀቅ ግድ ይላል።”
   ዶክተር ሥልጣን ፈልገው አልመሰለኝም። “ብቁ የሆኑት ሃገር ወዳዶች”ም [መለኪያው ምን እንደሆነ ባይታወቅም!] ቢሆኑ እኮ በፓርቲ ካልታቀፉ “የመንግስትን መኪና መዘወር” አይችሉም። ከምርጫው በኋላ “ከፓርቲ ፖለቲካ” ዉጭ አባን ከና የሚል የለም። ግለሰብ [ኢትዮጵያዊ ዜግነት ካለው] ወይ ካሉት ፓርቲዎች አንዱን መቀላቀል፤ ወይ አዲስ ፓርቲ ማቋቋም፤ ወይ የፖለቲካ ተንታኝ መሆን [እውቀት ይጠይቃል]፣ ወይ ከፖለቲካ ዉጭ ሆኖ በየአራት አመቱ አንዲት የምርጫ ካርድን መብትን መጠቀም። ካላስ!
   በምርጫ ብቻ!

 3. ውድ ወንድሜ በመጀመሪያ ለትችትህ በጣም አመሰግናለሁ። ጽሁፉን በጠቅላላው ስታነበውና የእኔን ሎጂክ ስትረዳ ብቻ ነው የምንግባባው። ለማስረዳት እንደሞከርኩትና በአብዛዎች የሶስተኛው ዓለም ያለው ህኔታ ከምርጫ በኋላ እንደሚያረጋግጠው በምርጫ አሸንፎ የሚወጣው ፓርቲ ለህዝቡ የሚጠቅም ነገር ስለማይሰራ ነው። አንድ ህዝብ ምርጫ የሚያስፈልገው በእርግጥም መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ሊሟሉለት የሚችሉ ከሆነና ከረዠም ጊዜ አንፃር ደግሞ መሰረታዊ ለውጥ ሲመጣለት የሚችል ከሆነ ብቻ ነው። እስካሁን ድረስ በአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ውስጥ ከተካሄዱት ምርጫዎች የምንማራው መንግስታት የባሰውኑ ጨቋኝና ድህነትን ፈልፋይ መሆናቸውን ነው። የኢትዮጵያን ሁኔታ ከተመለከትክ የመጨረሻ መጨረሻ ብልጽግና የሚባለው ፓርቲ ነው በአሽናፊነት የሚወጣው። ሌሎች ፓርቲዎች ቢያሽንፉ እንኳ ዶ/ር አቢይ ስልጣኑን ይለቃል ብዬ አላምንም። ለማንኛውም ጠቅላላውን ጽሁፌን ስትረዳውና ሎጂኩን ስትገነዘብ ለምን በአሁኑ ጊዜ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ አላስፈላጊ መሆኑን ልትረዳልኝ ትችላለህ።

  በተረፈ በጣም አመሰግናለሁ

  ፈቃዱ

  • አመስግናለሁ ዶክተር። ይረዱኝ ዶ/ር፣ እንደሃገር በጣም ብዙ እና ትልልቅ ችግሮች አሉብን፣ ምርጫ ሁሉንም ይፈታልም አይባልም። ምርጫውን ያለማድረግ ግን ከማድረግ የበለጠ መዘዝ አለው። ብልጽግናን ማሽነፍ ቢቀር እንኳ እስከ 30 እና 40 ፐርሰንት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቢወከሉ እንደ ሃገር ትልቅ ድል ነው። እንዳለፈው 100 ፐርሰንት ከተባለ ብልጽግናም አብዷል ማለት ነው፣ አደጋውም የከፋ ይሆናል፣ እርስዎ ልክ ይሆናሉ።
   ሌላው፤ አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ላይ ምንም ሰበብ አያስፈልግም። ምርጫ ማጭበርበር አይቻልም። እንዲያውም በጣም የሚያስፈራው ብልጽግና ያለምንም ተፎካካሪ “የሚያሸንፍበት” የኦሮሚያ ክልል ነው ፟ – The silence is deafening there!
   ካልተግባባንም ምንም አይደለም። ለጊዜው በሃሳብ ልዩነት እንለፈው። ከዚያ ጊዜ ፈራጅ ይሆናል፣ ሩቅም አይደል በጣም ቅርብ ነው። ወይ ያስታውሱኛል፣ ወይ አስታውስዎታለሁ። በግሌ ይቅርታ ከመጠየቅም ወደኋላ አልልም።
   በምርጫ ብቻ!

 4. According to the genocide watch the ten stages of Genocide are
  Step 1. Classification
  Step 2. Symbolization
  Step 3. Discrimination
  Step 4. Dehumanization
  Step 5 Organization
  Step 6. Polarization
  Step 7. Preparation
  Step 8. PERSECUTION
  Step 9. Extermination
  Step 10. Denial

  Those who are going forward with the upcoming election as if there is no genocide in Ethiopia are those who reached the tenth step ‘Denial’, those of us who are not in denial recognize holding free and fair elections in Ethiopia in these chaotic times is not possible and should not even be contemplated let alone actually have an election.

 5. ክቡር ዶ/ር ፈቃዱ
  ከድር ሰተቴ በየወብ ሳይቱ እየዞረ አስተያየት እንዲያስታውቅ የተቀጠረ ልክስክስ ውታፍ ነቃይ ነው፡፡ ለሱ ጪራሽ መልስ እንዳይሰጡ፡፡
  ሆዳም ለሰው ነፍስ ደንታ የለውም፡፡ በምርጫ ቅስቀሳ ለተገደሉ ሰዎች ደንታ የማይሰጥ አገዛዝ ያሉትን አጣሞ ምርጫ አያስፈልግም እንዳሉ አስመስሎ የሚያቀርብ ህሊናም ይሉኝታውም የሌለው ከርሳም ካዲሬ ነው፡፡

  • ዶክተሩ ያልከፋቸውን አንተ ምን ቤት ነህ? ሲጀመር በሃሳብ የመለየትና የመጠየቅ መብቴን አክብር። ሲቀጥል ከቻልክ ሃሳቡን ሞግት። For the record, ከድር ሰተቴ ከ”ዘሃበሻ” ዉጭ የትም የለም። ሃባ ሸራፋ የሚያገኘውም ጥቅም የለውም።
   መሳደብ የሚመነጨው ክሃሳብ ድርቀት ነው።
   በምርጫ ብቻ!

 6. “መልካም ግንዛቤ” አለ ዶ/ር ፈቃዱ? ለግንዛቤ የሚሆነዉ ነገር የትኛዉ ነዉ? “ምርጫ አይደረግ” የሚለዉ ሃሳብ የፖለቲካ አቋም እንጂ የግንዛቤ ነጥብ አይደለም። እሱንም ቢሆን የእሱን ያህል በሰፋ ሃተታ አያጅቡት እንጂ ሌሎች ብለዉታል። መግለጫም አዉጥተዉበታል።

  ግን የፖለቲካ አቋሙን ራሱን እንመርምረዉ። እሺ ምርጫ አይደረግ ይባል፤ ከዚያ ምን ይደረግ? ምርጫ አይደረግ የሚሉ ወገኖች እነ ሻለቃ ዳዊትን ጨምሮ፣ መንግስት ፈርሶ ነገርን እንዳዲስ እንጀምር ነዉ የሚሉት። ይህ ፈረንጆች a no starter የሚሉት ነዉ። በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ይህን እንደማይቀበል ተናግሯል። ታዲያ እነሻለቃ ዳዊት ጦር ሊመለምሉ ወይም ህዝባዊ አመጽ ሊያደራጁ ነዉ? ይህ ቧልትም ድንቁርናም ነዉ። እንዲህ አይነቱን ጅላጅል አስተሳሰብ የሚያስተናግድ አካል የላትም። ደቃለች።

  እኔ የዶ/ር አብይ ጭፍን ቀርቶ የአዘቦት ደጋፊ አይደለሁም። በእሱና በመንግስቱ ላይ የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ያሳዩትን ድክመት የምተች ነኝ። የመምረጥ እድል ቢኖረኝ ኖሮ ለእሱ ወይም ለፓርቲዉ ድምጼን አልሰጥም ነበር። ይህ ማለት ግን ዶ/ር አብይ ምንም ጥሩ ስራ አልሰራም የምልም አይደለሁም። ወይም በአገሪቱ ዉስጥ የተበላሸ ነገር ሁሉ ተጣያቂ ነዉ ብዬ አላምንም። በተለይ ግን በዶ/ር አብይ ስልጣን ዘመን ዲሞክራሲ የለም የሚለዉ ግርድፍ አስተሳሰብ ጭፍን ጥላቻን እንጂ በምድር ላይ ያለን እዉነታ አያመለክትም። በምርጫዉ ሂደት ዉስጥ ችግሮች እንዳሉ እረዳለሁ። ኦሮሚያ ዉስጥ በቂ ፉክክር አይኖርም። ይህ ግን የአብይ ጥፋት አይደለም። በቀን ወጣቱን ለአመጽ እያዘጋጁ ሌሊቱን ከታጣቂዎች ጋር የሚመክሩ የተለያዩ ጽንፈኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ከጨዋታ ዉጭ የመሆን ዉጤት ነዉ። አንዳንዶቹ በፈጸሙት ወንጀል እስር ቤት ሲገቡ ሌሎቹ አኩርፈዉ ራሳቸዉን ከዉድድር አግልለዋል። ሌሎች ቦታዎች ላይ ግን የተሻለ ፉክክር ሊኖር እንደሚችል እጠብቃለሁ። ይህ ግን የሂደት ጉዳይ ነዉ። አዉሮፓም አሜሪካም ዛሬ ድረስ ፍጹም የሆነ ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት አልገነቡም። አሜሪካ ዉስጥ ጥቁሮችን ለማግለል በመራጮች ምዝገባ ላይ የሚደረገዉ አሻጥር የታወቀ ነዉ። አዉሮፓ የባሰ የጥቁር አግላይ የፖለቲካ ስርአት ያለበት አሁጉር ነዉ።

  በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ታይቶ የማይታወቅ የመናገር፣ የመጻፍና የመደራጀት መብት አለ። ችግሩ አንዳንዶች ይህን መብት ተጠቅመዉ የሰከነ፣ አገር አሻጋሪ የሆነ ሃሳብ ከማፍለቅና ከማስተላለፍ ይልቅ የእየለቷን ክስተት በግራ በቀኝ እየበለቱ (የገቢ ምንጭ ስለሆነም) ህዝቡን ግራ ሲያጋቡ መዋላቸዉ ነዉ። ምርጫዉ መደረጉ አይቀሬም አስፈላጊም ነዉ። ከዉጤቱ ባሻገር፣ እንደ አገር አንድን መሰናክል እንደምንወጣ ማረጋገጫ ነዉ የሚሆነዉ። ይህን አብይን ለማንገስ እንደመፈለግ አድርጎ ማሰብ ከራስ ኦርቢት ወጣ ብሎ የአገርን ጉዳይ ሰፋ አድርጎ ለማየት ካለመቻል የሚመነጭ አስተሳሰብ ነዉ።

  አሜሪካኖችና አዉሮፓዉያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን አደገኛ ተጽእኖ ለማዬት የማይችል ሰዉ፣ parallel reality ዉስጥ የሚኖር መሆን አለበት።

  የአገር ጉዳይ የአንድ ጠ/ሚ ወይም ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ዛሬ ለአገራችን እንቁም የምንል ሁሉ፣ የዛሬ 23 አመት አገራችን ከኤርትራ ጋር ጦርነት ስትገባ ከሰዉ በላዉ ህወሃት ጎን ቆመናል። ምክንያቱም የአገር ጉዳይ ስለሆነ። አያቶቻችን፣ ቅድም አያቶቻችን ያደረጉት ይህንን ነዉ። ነጻ አገር ያስረከቡንም በዚህ አይነት አስተሳሰብ ነዉ።

  ለዶ/ር ፈቃዱና እሱን ለመሰሉ ስለአገራቸዉ የሚያስቡ ኢትዮጵያዉያን የምመክረዉ፣ ከወቅታዊ ሁኔታዎች ያለፈ ራእይ ላይ እንዲያተኩሩ ነዉ። ያ እራይ ደግሞ ድንገት ነገ እንደማይፈጠር፣ ይልቁንም ትእግስት ማስተዋልና hard lifting እንደሚያስፈልገዉ እንዲረዱ ነዉ። ምርጫዉ የዚያ ሂደት ክፍል እንጂ የራዕያችን ማሳኪያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። let’s take it easy.

 7. ውድ ወንድሜ አቶ ማቴዎስ፣
  በመጀመሪያ ደረጃ ለትችትህ በጣም አመሰግናለሁ። መልካም ግንዛቤ ስል በአጠቃላይ ሲታይ የህግ የበላይነትና ተጠያቂነት፣ እንዲሁም ኃላፊነት ከላይ ባስቀመጥኩት መሰረት ነው የሚሰራው ለማለት ነው። በመጀመሪይ ደረጃ በምዕራቡ የካፒታሊስት ዓለም የፓርሊሜንታሪ ዲሞኮራሲና ፓርቲዎች እንዴት እንደተመሰረቱ ካሳየሁ በኋላ በአጠቃላይ ሲታይ አገዛዞች እንዴት እንደሚሰሩም ነው። ለማሳየት እንደሞከርኩት ካፒታሊዝም ሙሉ በሙሉ ከመዳበሩ በፊት ብዙ ምፓርቲዎች እንዳልነበሩ ነው። ፓርቲዎች የካፒታሊዝምና ሰፋ ያለ የምሁራዊ እንቅስቃሴ ውጤቶች ናቸው። በአውሮፓ ምድር ምሁራዊ እንቅስቃሴ የተጀመረው በ14ኛው ክፍለ-ዘመን ነው። ይህ ዐይነቱ ቀስ በቀስ እያደገና እየዳበረ የመጠ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ከአመራረት ስልት መለወጥ፣ ከቴክኖሎጂ መዳበር፣ ከከተማዎች ግንባታና ከጥበብ ማበብ ጋር ተደምሮ ለፓርሊሜታሪ ዲሞክራሲ አመቺ ሁኔታ ሊፈጥር ችሏል በማለት ለማብራራት ሞክሬአለሁ። ይህንን ጉዳይ በአናሎጊ ማነፃፀር ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ፍሬ የሚሰጥ አትክልት ወይም ዛፍ ነገር ፍሬ ከማብቀሉና ፊሬውም ከመብሰሉ በፊት ከታች ወደ ላይ በብዙ ነገሮች በመታገዝ ማደግና መብሰል አለበት። ለምሳሌ ፓፓዬ በልተህ ታውቅ እንደሆነ ፓፓዬ ይህንን ዐይነቱን ክንዋኔና ካለፈ በኋላና ፀሀይ የምትለግሰውን ኃይል ካገኘ በኋላ ነው ወደ ጣፋጭነት ሊለወጥ የሚችለውና ተለቅሞም መበላት የሚቻለው። ሳይበስል የሚበላ ከሆን ግን በጣም ይጎመዝዛል፣ በፍጹም አይቀመስም። ተምርም እንደዚሁ ነው። ከመብሰሉ በፊት ልብላህ ብትለው በጣም ነው የሚመረውና የሚጎመዝዘው። ይህንን ጉዳይ ወደ አገራችንም መንግስት መክና ስትለውጠው የመንግስቱ መኪና ላይ የተቀመጡ ሰዎች ጭንቅላታቸው ያልበሰለ ወይም ምሁራዊ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው። ስለሆነም የመንግስትን መኪናን በመጠቅመ ወደፋሺዝምነት ያመራሉ። ይህንን ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የላቲን አሜሪካ አገሮችና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የሚታይ ሀቅና ሰፋ ላለ ዲሞክራሲያዊ ግንባታና ለካፒታሊዝም እንቅፋት የሆነ ነው።
  ለማንኛውም አነተ እንደምታየው ሳይሆን ነገሩ በጣም የተወሳሰበና ከረጅም ጊዜ ጥናት በኋላ ግንዛቤ ለማግኘት የሚቻል ነው። ዶ/ር አቢይ ዲሞክራሲን አምጥቷል ወይም የሰራው ስራ በሙሉ ስህተት አይደለም የሚለው የቀልድ አነጋገር ነው። በህዝብ ላይ እንደማሾፍ ይቆጠራል። በሻሸመኔ፣ በአልጣዬ፣ በሸዋሮቢት፣ በካራቆሬ፣ በመተክልና በምዕራብ ወለጋ በአማራዎች ላይ እልቂት ሲደርስ የሚያሾፍ መንግስት ዲሞክራሲን አምትጧል ብትለኝ በህዝብ ላይ እንደምትቀልድ ነው የምመለከተው። በተረፈ ግን እኔ እንደ ሻለቃ ዳዊት ለመንግስት ግልበጣ የምዘጋጅ አይደለሁም። በዚህም አላማንም። በሌላ ወገን ግን አሁን ባለው የአኦሮሞማ ፕሮጀክት አገራችን ወደ ፋሺዝም ስርዓት እንደምታመራ ነው የማረጋግጥልህ። አገራችንም ከማደግ ይልቅ እየቆእረቆዘች ነው የምትሄደው። እጅግ አደገኛ ሁኔታ በአገራችን ምድር ሰፍኗል። ለማንኛውም ድረ-ገጼን ብትመለከት ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ማግኘት ትችላለህ። http://www.fekadubekele.com አድራሻው።

  በተረፈ ለትችትህ በጣም አመሰግንሃለሁ
  ፈቃዱ በቀለ

 8. ወንድሜ ዶ/ር ፈቃዱ፦
  በእርጋታ ስለሰጠኸዉ መልስ አመሰግናለሁ። በአገራችንን የፖለቲካ ዲስኮርስ ውስጥ አንዱ ትልቅ ችግር ይህ አይነቱ እርጋታ መጥፋቱ ነዉ። ሁሉም የራሱን ሃዲድ ይዞ እየጋለበ፣ በሌላ ሃዲድ ላይ በሚሄደዉ ላይ ጩኸትና ስድብ ሲያወርድ ነዉ የሚዉለዉ።

  መጨረሻ ላይ ካነሳኸዉ የዲሞክራሲ ጉዳይ ብጀምር፦ ያዉ ሁሉም እንደሚያዉቀዉ፣ ሃሳብን በነጻነት በጽሁፍ ወይም በንግግር ለመግለጽ ከተቻለ፣ ካስፈለገም በዚያ ሃሳብ ዙሪያ ከሌሎች ጋር በመሆን ተደራጅቶ ሃሳቡ ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው በሰላም መታገል ከተቻለ፣ ካስፈለገም ለህዝብ ዉክልና ያለ ምንም እገዳ ወይም ተጽእኖ ለመወዳደር ወይም ለመምረጥ ከተቻለ፣ መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲ ገጽታዎች ተፈጥረዋል ማለት ይቻላል። እነዚህ መብቶች ጸንተዉ እንዲቆዩ ደግሞ፣ ተቋማዊ ድጋፍና ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። ይሁንና ዲሞክራሲ ስለተፈለገ ብቻ የሚፈጠር ሳይሆን በጊዜ ሂደት ዉስጥ የሚዳብር የፖለቲካ ባህል ነዉ። ያም ሆኖ በሰዎች ተፈጥሮ የተነሳ ፍጹማዊ የሆነ ዲሞክራሲን ማምጣት ከቶዉንም አይቻልም።

  ኢትዮጵያ ዉስጥ የዲሞክራሲ አስተሳሰብ የፖለቲካ ዲስኮርስ አካል መሆን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ትልቁ የዲሞክራሲ ባላንጣ መንግስት ሆኖ ዘልቋል፣ በ27 አመታት አገዛዙ፣ ህወሃት/ኢህአድግ ለዲሞክራሲ መብት አለመኖር ዋናዉ ተጠያቂ የህዝቡ ባህል አለመዳበር ነዉ ይል እንደነበር እናስታዉሳለን። ይህ አባባል፣ ዛሬ ላይ እንደምናየዉ፣ የተወሰነ እዉነትነት ቢኖረዉም፣ ትልቁ የዲሞክራሲ ጸር ግን መንግስት ራሱ ነበር። የመንግስት ስልጣን ላይ የሚቀመጡ ሰዎች የማህበረሰቡ አካል ስለሆኑ የተለዬ ባህል እንዲኖራቸዉ ባንጠብቅም፣ ከዲሞክራሲ ጋር የሚኖራቸዉን ጠብ የተለየ የሚያደርገዉ ከኢኮኖሚና ከስልጣን ጥም ጋር የተያያዘ ፍላጎት የሚኖራቸዉ መሆኑ ነዉ።

  የሆነዉ ሆኖ፣ ባለፉት 3 አመታት የፌዴራል መንግስት ባህርይ በከፍተኛ ደረጃ ተቀይሯል። ማንም እንደፈለገዉ መናገር፣ መጻፍ፣ መደራጀት ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ለሰላም ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ቅስቀሳዎችን ማድረግ እስከሚችሉ ድረስ መብታቸዉ ሲጠበቅላቸዉ እያየን ነዉ። አልፎ አልፎ እከሌ ይህን በመናገሩ ታሰረ፣ ከአገር መዉጣት ተከለከለ፣ እከሌ ሰልፍ ጠርቶ ተከለከለ ወዘተ የሚሉ ስሞታዎች አልፎ አልፎ ቢሰሙም exception ናቸዉ። ከዚህም ባለፈ፤ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጠባቂ ተቋሞች ገለልተኛ ሆነዉ እንዲሰሩ የሚያስችል ለዉጥ ተደርጓል። Perfect ላይሆኑ ይችላሉ፣ ለዉጡን ግን መካድ አይቻልም። አሁን ያለዉ ትልቅ ችግር የመንግስት የዲሞክራሲ መብት ለማክበር አለመፈለግ ወይም አለመቻል ሳይሆን፣ ያን መብት abuse የሚያደርጉ የፖለቲካ ሃይሎች፣ አክቲቪስቶችና ወፍዘራሽ ማህበራዊ ሚዲያዎች መብዛት ነዉ (አንዳንድ የክልል አስተዳደሮችም የችግሩ አካል ሆነዉ ቆይተዋል)። በእኔ አስተያየት በዋናነት የዚህ ችግር ተጠያቂዎቹ የኦሮሞ ብሄረተኞች ናቸዉ (ህወሃት ወያኔን ወደጎን በመተዉ)። በሻሸመኔና በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች የዛሬ አመት ገደማ የደረሰዉ ትልቅ እልቂትና ዉድመት ገደብ ያጣ የኦሮሞ ብሄረተኝነት ዉጤት ነዉ። (የሚገርመዉ፣ ከዚያ አይነት ጥፋትና ዉድመት በኋላ፣ መንግስት እነጀዋርና በቀለ ገርባን በቁጥጥር ስር ሲያዉል፣ የዲሞክራሲ መብትን የማፈን እርምጃ ነዉ እያሉ ዛሬ ድረስ የሚጮሁ መኖራቸዉ ነዉ)።

  ዲሞክራሲ ለአንድ አገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ህይወትና እድገት አስፈላጊ የሆነዉን ያህል፣ አንዲት አገር ለተጋረጡባት ችግሮች ሁሉ ብቸኛ መፍትሄ አይደለም። የሰላምና የህግና የፍትህ መከበር፣ የኢኮኖሚ እድገትና ፍትሃዊ ክፍፍል፣ የባህሎችና የኪነጥበብ እድገትና ወዘተ ጎን በጎን ያስፈልጋሉ። ሲንጋፖር ዉስጥ የዲሞክራሲ መብት አከባበር እምብዛም ነዉ። ሌሎቹ ተፈላጊ ነገሮች ግን በቦታዉ ስላሉ፣ በአገራቸዉ የሰፋ ዲሞክራሲ ያላቸዉ ብዙ ህንዶች ሲንጋፖር ሄደዉ መኖርን ይመርጣሉ። የአረብ አገሮች ምሳሌ extreme ስለሆነ እሱን አላነሳዉም። ሌላ አገር ሳንሄድ እራሳችን አገር፣ ሰዉ ከዲሞክራሲ ይልቅ ቅድሚያ ሰላምና ደህንነት ይከበር እያለ ነዉ።

  In the end, democracy does not have a blue print or a manual to follow. You simply work at it, learn from your missteps, balance it with other societal needs, and keep working at it. In Ethiopia’s case this is a complicated process because, besides the common questions of democracy, we have an ideology held by many that posits ethnic self-government as a democratic right. That belief is strongly contested by those who believe politics by its nature is citizenship based, not ethnic based. No one can expect this fight to go down smoothly. It would therefore be foolhardy for the government to pick a side and bulldoze over the other. For a time period, one needs to find a way to strike some kind of balance between these two positions to keep the country together during this transition period while advancing democracy to the limits of the current political system and seek an enduring solution for the political system itself.

  Abiy and his colleagues believe the ‘medemer’ philosophy does that balancing act in the meantime while incrementally taking us to the long term solution. I am not sure if they have a clear idea what that ultimate solution will look like. Time will tell if they are right but it is a compelling and worthwhile perspective.

  We now have three school of thoughts on how to bring democracy and a stable political system in Ethiopia: one that maintains ethnic groups have self-governing political rights and the current ethnic federal system should not be reformed fundamentally, if at all, to ensure those ethnic rights are in place; another school of thought that maintains the current system must be reformed fundamentally on the basis of citizenship based politics in order to yield true democracy, peace and a stable political system while guarantying the respect of and equality of all ethnic cultures, languages and other values; and a third school of thought that, it seems to me, believes in merging the best of the two sides and move incrementally to some long-term equilibrium.

  The way forward is to give these three perspectives a chance to be tested through rational dialogue and ultimate referendum on a revised constitution by the Ethiopian people. This election has created some opportunity for citizens to hear about the different perspectives but not enough. I believe and hope whoever wins the election will convene a national dialogue and a process for revising the constitution. I believe, if we handle it well, that process will take us further in the direction of building a durable democracy and one that keeps the country in unity. I don’t see a short cut or a better alternative.

  Meanwhile, we need to bring the unhelpful rhetoric a notch down. Languages like the federal government makes a mockery (ሹፈት) of the killing of innocent lives is not just wrong, it feeds into a dangerous narrative. There are folks whose daily incantation starts with smearing the federal government as the enemy of certain groups, particularly the Amhara. The subtext of this narrative is “the federal government (that is led by an Oromo) doesn’t care about the killing of innocent lives because the victims are Amhara.” This is insane, but many people believe it as an absolute truth. In fact, it has become a high value currency with which certain media outlets and Amhara nationalists exchange favors. We must resist the temptation to jump on this bandwagon because, in the end, it is a losing proposition for everyone.

  To your main theme – how parliamentary democracy got where it is now in Europe – I agree with you that we would have an easier task of building democracy if we had a developed capitalism, for several reasons. But we cannot postpone democracy until we build capitalism because, as eminent thinkers like Amartya Sen argued, for poor countries the road to economic development is through good governance and democracy.

  We cannot replicate Europe’s or America’s experience, either, because we don’t have the same conditions they had when they started the road to multiparty democracy. Even America didn’t replicate Europe. We can learn some from the experiences of others but we will have to go through our own experience using own devices. If we have the will and the goodwill, we can build a durable democracy. Some African, Asian and Latin American countries have done it. Why not us?

  Our current challenge is not the will. But we terribly lack the goodwill and we are so consumed with plenty of anger, cynicism, opportunism and most of all tribalism. It is beyond me how people who condemned ethnicism yesterday became virulent tribalists overnight; how they think the best way to fight Oromo nationalism is Amhara nationalism; how they think the best tool to right a wrong is doing the same wrong thing. That is where we are at today.

  The question is how do we get out of the current mess and build democracy? No ready-made answer for this. But if by some miracle we start to show some goodwill toward each other, perhaps cumulatively, we can come up with one brilliant idea that would take us to a destination that is acceptable or at least work for most. However, whatever route we take we must ensure the unity and integrity of the country. Under current circumstances, the best defense for Ethiopian unity is the federal government! Not because of Abiy or Demeke or anyone else, but because we need the institution intact to keep Ethiopia intact. If we undermine the federal government, instead of appropriately criticizing it and helping it with good ideas, not only will we fail to build democracy, I am afraid, we could lose our country.

  I give you the last word. It was a pleasure having this dialogue.

 9. ውድ ወንድሜ አቶ ማቴዎስ፣

  አስተያየትህ በኢሜይሌም በኩል ደርሶኛል በጣም አመሰግናለሁ። በሃሳብህ እስማማለሁ። እያንዳንዱ አገር የየራሱ ህብረተሰብአዊ ታሪክና ልምድ፣ እንዲሁም ባህል ስላለው የሰውም አስተሳሰብ በዚያው በአገር ውስጥ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ በአጠቃላይ አነጋገር ባህል ብለን በመንጠራው የሚቀረጽ ነው። ይሁንና ማንኛውም ህብረተሰብ እዚያው ረግቶ የማይቀር ስለሚሆንና በድሮው አስተሳሰብ ብቻ በጉልህ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ስለማይችል የግዴታ ከጊዜው ጋር ሊጓዝ የሚችል የአሰራር ስልትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ መቻል አለበት። ወደድንም ጠላንም ይህ ተፈጥሮአዊ ህግ ነው። እንደዚህ ማድረግ የማንችል ከሆነ ከእንስሳ የምንለይብት ነገርት የለም ማለት ነው። በተለይም በለጠፍኩት የዩቱብ ቻናሌ ለማስረዳት እንደሞከርኩት በግሪክ ምድር አንዳንድ የተገለጸላቸው ሰዎች ጥያቄ ባያነሱና ባይመራመሩ ኖሮ የአስተሳሰብ ለውጥ ባልመጣ ነበር። ይህ ዐይነቱ በግለሰቦች ጥረት የተደረገ ምርምርና የአስተሳሰብ ለውጥ ወደ ህብረተሰብአዊ ኃይል በመለወጥ ከግሪክ አልፎ ለአውሮፓው ማህበረሰብ ለዲሞክራሲ መሰረት መጣል ችሏል። በተለያዩ ጽሁፎቼ ውስጥ ለማሳየት እንደሞከርኩት የአውሮፓው ማህበረሰብ ወደ ፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ ሊመጣ የቻለው ሰፋ ያለ የጭንቅላት ተሃድሶ እንቅስቃሴ ካደረገ በኋላ ነው። በዚህ ውስጥ ለዲሞክራሲ ማበብና መዳበር በተፈጥሮ ሳይንስ ላይ፣ በፍልስፍና ላይ፣ በሶስዮሎጂና በሌሎች ነገሮች ላይ የተደረገው ምርምር ለዲሞክራሲና ለነፃነት ማበብ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል ማለት ይቻላል። ባጭሩ የዲሞክራሲን ጉዳይ ከብዙ ነገሮች ጋር በማያያዝ ነው የማየው። በአገራችን ምድር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ ከተፈለገ በተለይም ተግባራዊ የምናደርገው የኢኮኖሚ ፖሊሲና የትምህርት ፖሊሲው ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። በተለይም ሰለኢኮኖሚ ዕድገት ያለን አመለካከት እስካለተለወጠና ጠቅላላውን ህዝብ የሚያካትት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ ያለን ችግር እየተወሳሰበና እየተባባሰ ነው የሚሄደው። ይህ ዐይነቱ ችግር በእኛ አገር ብቻ የሚታይ ሳይሆን በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችም ያለ ችግር ነው። እንደ አርጀንቲናና ብራዚል፣ ቺሌና ሌሎችም ከሰላሳ ዓመታት በፊት በምርጫ ስም አገዛዞች ቢለዋወጡም ተመሳሳይ የሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በማካሄዳቸው በእነዚህ አገሮች ውስጥ የባህል፣ የፓለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የአካባቢ ቀውሶች በስፋትም ሆነ በጥልቀት ይታያሉ። አገዛዞችም አፍጠው አግጠው የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ስለማይችሉና፣ በደሀና በህብታም መሀከል ያለው ልዩነት በጣም የሰፋ በመሆኑ ያላቸው አማራጭ የመንግስቱን መኪና የበለጠ ጨቋኝ ማድረገ ነው። ለምሳሌ ብራዚል ስልጣን ላይ ያለው ፕሬዚደንት የሚሰራውን ስንመለከት እንደገና አምባገነናዊ አገዛዝ ስልጣን ላይ ያለ ነው የሚመስለው።
  ለማንኛውም ካለንበት ችግር ለመላቀቅ ነገሩን በሰከነ መልክ ማየት ያስፈልጋል። በተለየም የሚያሳስበኝ አርቲፊሻል የሆነ በአንዳንድ የጎሳ ኤሊቶች መሀከል ያለው ፍጥጫ ነው። በእኔ እምነት ከ90% በላይ የሚሆነው ህዝባችን ስላምን ይፈልጋል። በጣም አስቸጋሪ የሆነው አጉል ትረካ የሚያወራውና የግዴታ ጊዜው የእኔ ነው እያለ የሚፎክረው ነው። ከዚህ ዐይነቱ ትረካ መውጣትና ማንኛውም ነገር በሳይንስ መነጽር መታየትና መመርመር አለበት ንዬ አምናለሁ። ሁሉም እንደፈለገው እየተነሳ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚተረጎም ከሆነና በዚህ ዐይነቱ ትረካ ላይ የምንጨቃጨቅ ከሆነ ጠቅላላውን ህዝብ የሚመለከት ዕድገት ለማምጣት አንችልም። በእኔ ዕምነት ክርክርና ምርምር ማድረግ ያለበን በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ በፊሎሶፊና በጠቅላላው የህዝባችንን ችግሮች ሊፈቱ በሚችሉ ነገሮች ላይ ብቻ ነው። ማንኛችንም መኖር እንፈልጋለን። ለመኖር ስንል መስራት አለብን። ለመስራት ደርግሞ የስራ ቦታ ማግኘት አለብን። ለዚህ ደግሞ የግዴታ ኢንቬስትሜንት መካሄድ አለበት። ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመጣ ደግሞ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር አለብን። በቴክኖሎጂዎች አማካይነት ነው ምርታማነትን በማሳደግ የህዝባችንን ችግር መፍታት የምንችለው። ለዚህ ደግሞ መንግስት የሚባለው አካል ከፍተኛ ኃላፊነትና ግንዛቤ እንዲኖረው ያስፈልጋል። ከደቡብ ኮሪያ፣ ከጃፓንና ከቻይናዎች የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ከምዕራብ አውሮፓም እንደዚሁ ብዙ ነገሮችን መማር እንችለለን። በአጭሩ በዕውቀትና በኢኮኖሚ ዕድገት አማካይነት ነው የአገራችንን ችግሮች ልንፈታ የምንችለው። ኢኮኖሚው ሁለገብ ከሆነና የሰፊውን ህዝብ ፍላጎት ማሟላት የሚችል ከሆነ ሌሎች ነገሮችን ቀስበቀስ መፍታት እንችላለን። ተጨባጩን የአገራችንን ሁኔታ ስመለከት ግን ሁላችንም የምናደላው ምርምር በማድረግ ላይ ሳይሆን በንትርክ ላይ ነው። ይህ ዐነቱ ሂደት ለጤናማ ዕድገት አመቺ አይሆንም።

  በተረፈ ሰፋ ላለ አስተያየትህ በጣም አመሰግንሃለሁ!

  ፈቃዱ በቀለ

 10. ዶ/ር ጽሁፎ አስተማሪ ሁኖ ብዙ ጊዜ ብከታተለዉም በማቴዎስ ሀሳብ እስማማለሁ መለትዎ እርሶ መስማማት ቢችሉም እኔን ግን አልተስማማኝም ማቴዎስ ከጽሁፉ እንዳየነዉ ወይ ፈረንጂ ቤት ያደገ ወይ ኢትዮጵያ እንግሊዝኛ እንዲማር ፈረንጂ አገር የላከቸዉ ገለ ሰብ ነዉ የሚኖርበት አገር የእንስሳ መብት ተከብሮ ጥበቃ የሚደረግለት ነዉ። በፈረንጅ አገር የኖረበት ዘመን በሰዉ ልጂ ላይ ያለዉን አስተሳሰብ ስላልለወጠዉ እንዲህ ያለ አስነዋሪ ጽሁፍ ይጽፋል። አማራዉ እንደ አዉሬ እየታደነ የሚገደለዉ የሱን ሰብአዊነት በር አላንኳኳም ስለ አማራዉ ግድያ የአማራ ሚዲያዎች ናቸዉ እያለ ሊነግሮት ይፈልጋል ልክ ነዉ ማን ይናገርለት እነ ማቴዎስ አስገድለዉ ገደልን እንዲሉ ነዉ የተፈለገዉ? የፈረንጂ ፕሮግራምን ሳይቀነስ ሳይጨመር እያሳለጠ ያም አልበቃዉ ብሎ አማራዉ አልተገደለም ሊለን ይፈልጋል። የጥላቻ ስሜቱ በፈረጂ አገር የሚመለከተዉ ሰብአዊነት ለቡ አልደርስ ብሎ በሪሞት የሚቆጣጠራቸዉን ጀሌዎቹን በሰይጣናዊ ሀሳብ ያስታጥቃል። አማራዉ ላይ የሚደረሰዉ እንግልት ጭፍጨፋ ሳይረዳዉ ቀርቶ አይደለም። ትምህርት የማይለወጥ አእምሮን ሊለወጥ እንደማይችል ማቴዎስ ጥሩ ማሳያ ነዉ። ለማንኛዉም አምላኪዎችህ የጻፉትን ብዙ ነገር ብታነብም ኢትዮጵያን ለመበታተን Ethiopia under Italian occupation by professor Saacchi ፈልገህ አንብብ አማራዉ ጠፍቶ ትግሬ ተመችቶት ይኖራል ብለህ አትጠርጠር ማንነትንም አዉቄዋለሁ።
  ዶ/ር አስተምሮቶ መልካም ነዉ ለእንደዚህ አይነት ለተወላገዱ ፍጡራን መልስ ባይሰጡ መልካም ነዉ ጎትተዉ ወዳልተፈለገ መንገድ ይከቶታል እነሱ ተልእኮ ላይ ስለሆኑ በአመንክዮና በሃሳብ ጥራት ሊያምኑ የማይችሉ ሮቦታይዝድ የሆኑ ክፉ ፍጥረቶች ናቸዉ።
  አመሰግናለሁ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.