“ ከዕዉነት የማይነሳ የሠላም እና ዕርቅ ምኞት ዘላቂነት ከዕምቧይ ካብ አይለይም ! – ማላጂ

1

ኢትዮጵያን እና አገሪቷን ለዘመናት ሲያመሰቃቅሉ የነበሩት የብሄርተኝነት እና አግላይ ስርዓት ፈረሰኞች እና አገልጋዮች ግፍ አንገሽግሾት ከረጅም ዓመታት ብሶት ከወለደዉ ህዝባዊ ትግል ለፍሬ ለማብቃት የከፈለዉን መስዋዕትነት ዛሬም ትግሉን እና የትግሉን ዉጤት የራሳቸዉ ባለቤት የሚያደርጉት የነበሩት  የህዝብ እና የአገር ተገልጋዮች እና ህዝብ አግላዮች መሆናቸዉን ራሳቸዉ ከጅምር አሳይተዋል ፡፡

ከለዉጥ ማግስት መጋቢት ሀያ አራት ሁለት ሽ  አስር ዓ.ም. በፊት የነበሩትን አግላይ፣ ገዳይ እና በዳይ  ብሄራዊ  በደል ከነበረበት ለታሪክ ይደር እና ከዚህ የለዉጥ ዕለት ማግስት  ስለሆነ እና ስለቀጠለዉ የህዝብ እና የአገር ዉድቀት እና ሞት ከድጡ ወደ ምጡ ሆኗል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የነበረዉን ህዝባዊ ድጋፍ ሳንረሳ እና የቀደመዉን ሳናወሳ ህዝቤ ሞት እና ስቃይ በቃ ብሎ አፉን ቃል ሳይጨርስ  ከሀምሌ 2010ዓ.ም. ጀምሮ የተቀናጀ እና የተደራጀ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን በግላጭ በሚጎዳ የጥላቻ እና የጥፋት ድርጊቶች መልካቸዉን ቀይረዉ ሀ ሁ….ብለዉ መጀመራቸዉ ግልፅ ነዉ ፡፡

ይህ የቀደመ እና ለያይ  ህዝባዊ አስተዳደር እና አንዱን ህዝብ ከአንዱ በመለየት እና በማጥላላት የነበረዉ ከፋፋይ መንግስታዊ አስተዳደር በቀናት ዉስጥ የማይጠበቁ እና የዚህች አገር እና ህዝብ መቆርቆዝ መንስዔ እና ለዚህም ተጠያቂ መሆን የነበረባቸዉ ስብስቦች በክብር እንግድነት በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ  እና 2011 ዓ.ም. መጀመሪያ በሚኒሊክ ቤተ መንግስት የተጋበዙት እና የከደሙት እነማን እንደነበሩ እና በአንጻሩ ለኢትዮጵ የኖሩ እና የሞቱት በዚህ ግብዣ ወቅት አለመኖር ወይም መገለል በጊዜዉ ከፍተኛ ግርምታ እና ግርታ መፍጠሩን አስመልክቶ ከሶስት ዓመት በፊት ከአንድ ወዳጄ ጋር አንሰተን ስንወያይ ወዳጀ የሰጠኝ ምክነያት አልተዋጠልኝም ነበር ፡፡

ወዳጄ ያለኝ እነኝህ ሠዎች/ ስብስቦች በ1980ዎች አጋማሽ የሽግግር መንግስት ምስረታ፣ ህገ መንግስት ዝግጅት  እና የፌደራል ስርዓት አደረጃጀት ዋና ተዋናይ ስለነበሩ በቂ ግብዓት ይዞ ለመጪ ዘመን ማስተካከያ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ ነገሩኝ ወዳኜ …..ደጉ፡፡

ወዳጀ ያኔ የለም ለአገር በአገር የሞቱት ተርሰተዉ አገር የገደሉ እና ከአገር ወጥተዉ ባህር ማዶ ሆነዉ የጥፋት ዕሳት ሲያቀጣጥሉ የነበሩት ያሉበት ስብስብ ለዚያዉም ስለ ኢትዮጵያ እና ምኒሊክ  ወተት ሲባሉ ሬት የሚሉትን ማሰባሰብ እንደሚያሳስብ ደጋግሜ አልኩ ፡፡

የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይደርሳል….ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ፍጥነቱን እና መጠኑን በመጨመር ለሞት እና ስደት ( መፈናቀል) የሚዳርጉ ክስተቶች ቀጥለዋል  ፡፡

ይህ ነዉ እንግዲህ “ዕዉነት የሌለበት ዕርቅ እና ሠላም”  “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ” ብሎ እንደመንከራተት የሚቆጠረዉ ፡፡

ለግማሽ ክ/ ዘመን የመለያየት እና የጥላቻ ሀሰተኛ እና ረብ የለሽ የታሪክ ቱማታ ባልታረሙበት እና ባልተስተካከሉበት የነበሩት ህፀፆችን ማስቀጠል ከጅምሩ ህዝባዊ የለዉጥ እንቅስቃሴዉን  ጥገናዊ ማድረጉን አመላካቾች ነበሩ ፡፡

የብሄር ጭቆና ፣ የመደብ ልዩነት ፣ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ፣ ባለቤት እና ቤት አልባነት ( ባይተዋርነት፣ መጤ) የመሳሰሉትን በአንድ ህዝብ እና አገር ላይ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የመሆን እና ለዚህም በዋነኛነት መሳሪያ የመበሩት ህገ መንግስት ይዘቶች፣ የክልል አደረጃት እንዲሁም ታዳጊ እና አዳጊ ክልል ብሎ መለያየት ትክከክለኛነቱ ፣ ተገቢነቱ እና ወቅታዊነቱ እንኳን ለአፍታ ሊጤን ወይም የህዝብ አስተያየት ባልተሰጠበት ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ በሚል እንጅ ብዙም እንደማይጠበቅ ሳይታለም የተፈታ ነበር ፡፡

ከዚህም በላይ በነበሩት የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅሮች ለዓመታት በነበረ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የዜጎች ሞት እና መፈናቀል ፣ ለምዝበራ እና የመሳሰሉት በደሎች ጥፋተኞች በጥፋታቸዉ ልክ እንዲጠየቁ ህዝብ ቢያሳስብም ….ከእናሻግራለን…ዉጭ ጭጭ መባሉ የነበሩትን ሠባዊ ፣ቁሳዊ እና ሁለንተናዊ ጥፋቶች ተጠናክረዉ እና ተስፋፍተዉ እንዲቀጥሉ ዋነኛ ምክነያት ሆኗል፡፡

ክልከላ በተደረገባቸዉ መሰረታዊ የአገር እና ህዝብ ደህንነት ጉዳይ ላይ ማንኛዉም ግለሰብ ሆነ ስብስብ ከአገር እና ከህዝብ በታች እንደሆነ ተቆጥሮ ለጥፋት ድርጊቱም ሆነ ለፈፀመዉ ወንጀል በጥፋትነት እና በጥፋተኛነት አስካልተለየ በቀር ትክክለኛ እና ቅቡል እንደሆነ ድጋፍ መስጠት እንደሆነ ሊቆጠር የሚችል ነዉ ፡፡

ለዚህም ብዙ መስሌዎችን መጥቀስ ቢቻልም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም ከ1983 ዓ.ም አስካሁን በዜጎች ሞት ፣ስደት እና በአገር ክህደት ተግባር የተሳተፉት እና እየተሳተፉ ያሉት አንዳቸዉም በሰሩት ጥፋት እና ወንጀል አልተጤቁም ፤ሊጠየቁም አልተፈለገም ፡፡

ከዚህም ሌላ ለዘመናት የበደሉትን እና የገደሉትን ህዝብ ይቅርታ ለመጠየቅ ሲሞክሩም ሆነ ሲያስተባብሉ አይታይም ፡፡

ርግጥ አበዉ ባለቤት የናቀዉን…… ባለዕዳ አይቀበለዉም እንዲሉ  የኢትዮጵያ አሻጋሪ መንግስትም በዉስጡ ለዓመታት በህዝብ ላይ ከፍተኛ  በደል የፈፀሙትን  እና ህዝቡም ወደ ብሶት አደባባይ እንዲወጣ ያደረጉትን ምንም እንዳልነበሩበት አድርጎ ባላቸዉ ያለአቅም እና ስራ እየጨመረ ለሚያይ አካል ከእኔ እና ከናንተ በብዙ አገር እና ህዝብ ጉዳት ላይ የጣለ በገለልተኛ አካል ይጣራ እያለ ለሌላ ጥፋት ጊዜ ቢገዛ እንጅ ትዉልድ ከእኛ ይማር የሚል እና ኃላፊነት የሚሰማዉ ማግኘት ቀቢፀ ተስፋነት መሆኑን ከተረዳን ቆየን ፡፡

ዛሬም ቢሆን ትናንት በአገር ክህደት ፣ በሽብርተኝነት እና በዘር ፍጅት (Genocide ) የተሳተፉት የትናንቱ ጥፋት  ከተጠያቂነት ይልቅ የመብት እና የነጻነት ምልክት እና ሀዋርያ ሆነዉ እንዲቀጥሉ መፍቀድ  በድፍንፍን ዕርቅ እና ሠላም ማቀንቀን ለጥፋተኞችም ሆነ ለክፉ ድርጊቶቻቸዉ ባለቤት እና ተጠያቂ እንዳይሆኑ የመከለል እና የመከላከል አካሄድ ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ወቅታዊ ዕርቅ እና ሠላም አያስገኝም ፡፡

ለሁሉም የሚበጀዉ ዕዉነት እንጅ ሠላም እና ዕርቅ በማስተጋባት እንዳልሆነ ከአገራችን ወቅታዊ እና ዓለማቀፋዊ ነባራዊ ሁነት መረዳት ይቻላል ፡፡

ስለዚህም ለዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ መግባባት እና ዕርቅ  ዕዉነት መሆን  ፡-

 • የጥላቻ እና የሀሰት ግድግዳዎች ይፍረሱ፣ መጋረጃዎች ይቀደዱ ፣
 • በአገራችን የዓመታት ማንነትን ተመርኩዞ ሲካሄድ የነበረዉ አንድን ማህበረሰብ የማግለል እና የመግደል ሴራ በግልፅ መሠየም ፣
 • በለይቶ መግደል፣ ማግለል እና በመሳሰሉት ወንጀሎች ያቀነባበሩ ፣የመሩ ፣የተሳተፉ ፣ያሳተፉ እና አይተዉ እንዳላዩ ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ ሁሉ በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ፊት ይወገዙ ፤ይጠየቁ፣
 • በአገራችን በግል እና በቡድን የተፈፀመ ጥፋት ዘር ፍጅት፣ አድሏዊ አስተዳደር፣ የአገር ክህደት ፣የህዝብን እና ዜጎችን ሠላም የመንሳት (ሽብርተኝነት) ሊያስከትል የሚችለዉን ክፉ መዘዝ ባለበት ለማቆም ደርጊት በድርጊቱ ልክ ይጠራ፣
 • ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ዜጎች ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ ክብራቸዉን ፣መብታቸዉን ተነጥቀዉ በማንነታቸዉ ለደረሰባቸዉ ሞት፣ስደት እና ዕልቆ መሳፍርት የሌለዉ ግፍ እና መከራ ይቅርታ ሊጠየቁ ፣ ከሳ ሊከፈላቸዉ እና የሰማዕትነት መታሰቢያ ለኖራቸዉ ይገባል፡፡

ይህን በመጨረሻ የተጠቀሰዉን የሰማዕታት መታሰቢያ መኖር ከቀይሽብር እና ነጭ ሽብር ሰማዕታት ጋር ሲነጻፀር  ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ፅልመት ዘመን የተከፈለዉ የብዙ ወድ እና የዋህ ኢትዮጵያዉያን ህይዎት ዋጋ / ሞት፣ አካል መጉደል፣ ስደት እና ዉርደት ሲለካ በዓይነት እና ብዛት በዕጥፍ ከቀይ ሽብር ሠለባ የሚልቅ መሆኑን፡፡

ለዚህም እንደ አብነት ከሁለት በላይ ተጠቃሽ  መሰረታዊ ዕዉነታወችን ማሳየት የሚቻል ሲሆን ይኸዉም ፡-

 • ኢህአፓም ሆነ የነበረዉ የወቅቱ መንግስት የፖለቲካ እና የርዕዮተዓለም ልዩነት ብቻ መሆኑ እና የነበር ሲሆን ፣
 • አንደኛዉ ጊዜያዊ መንግስት ሲሆን ሌላኛዉ (ኢህአፓ) ከእኔ ፍላጎት እና ይሁንታ ዉጭ መንግስት አትሆንም ፤አትችልም ማለቱ፣
 • ሁለቱም ዋና መዲና ላይ ሆነዉ ኢህአፓ በኃይል  የህዝብ ስልጣን  ይገባኛል ብሎ የከተማ ዉጊያ ማሰብ /መጀመር ሲሆን ፣
 • በሂደቱ የህዝብ ልጆች ቢኖሩበትም በይገባኛል/ ኢህአፓ እና ወቅታዊ ያገባኛል ባይ ( መንግስት) መካከል ስለነበር ትግሉን ከተማ ዉስጥ እና የኃይል ከማድረግ ዉጭ በባለቤትነት ልዩነት አስካለ ትግል መኖሩን ትክክለኛ ሊያደርገዉ ይችላል

ከ 1983 ዓ.ም አስካሁን የሆነዉ ግን ፡

 • በከፋፋይነት የሚታወቀዉ የዓመታት የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር እና ይህ የሚነሳበት እና ምንጭ የሆነዉ ህገ መንግስት ለዜጎች መፈናቀል ፣ስደት እና ሞት  በምክነያትነት ሲጠቀስ ይህም ከትግል መጀመሪያ ምዕራፍ የታሰበበት ሆኖ በተሌም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በድምቀት የሚታዩበትን ማህበረሰብ/ ዜጋ ሁሉ ዓማራ በሚል የማጥላላት  ትርክት የጥላቻ ግድግዳ መገንባት ፣
 • በከተማ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ በሰበብ አስባብሰ እጅግ ሚስጣራዊ እና ስልታዊ ደባ ማሳደድ ሲሆን በገጠሪቷ የአገሪቷ ክፍሎች የሚኖሩትን ኢትዮጵያዉያንን ደግሞ በክልል አስተዳደር በተዋቀረ አደረጃጀት እና ህገ መንግስት በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ መኖር አለማኖር የክልል እና የግለሰቦች ስልጣን በመሆኑ በግልፅ የዜግነት እና በህይዎት የመኖር መብት የተደመሰሰበት ነበር ፤ነዉ ፣ነ
 • ማንነትን እና ዘርን መሰረት ያደረገ የመንግስት አስተዳደር የአንድን አገር ህዝብ አማኝ እና መናኝ በማድረግ ጠላት እና ወዳጅ በማድረግ ግልፅ አስተዳደራዊ አድሎ እና መድሎ መከናወኑ ፣
 • ማንነትን መነሻ እና መዳረሻ የሚያደርግ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች መጠነ ሰፊ የዜጎች ሞት ፣ስደት /መፈናቀል ወንጀል (atrocity) መፈፀሙ/ መኖሩ ፣
 • በቀደሙት ዓመታትም ሆነ አሁን በትጥቅ ትግል ሆነ በሠላማዊ ትግል ለዉጥ እና ነጻነት ለማምጣት እንታገላለን የሚሉት በትግል ሂደቱም ሆነ በፖለቲካ ተሳትፎ የሌለዉን ሰርቶ አዳሪ እና አገሪቷን የሚቀልበዉን አርሶ አደር መግደል ፣ ማፈናቀል እና ማግለል በሰፊዉ የሚታይበት መሆኑ፣
 • በቁጥር ደረጃም ቢሆን በቀይ ሽብር የሚገመተዉ ሰማዕትነት ከ 75000 አስከ ….የሚገምቱ ቢኖሩም በዚህ በዘመናችን በሆነዉ ማንነት ተኮር ጥቃት እና ሞት ግን ከግማሽ ሚሊዮን አስከ 5000000 እንደሚደርስ በተለያየ ጊዜ እና ቦታ የደረሱ እና እየደረሱ ያሉት ምስቅልቅል አገራዊ ሁነቶች ያሳያሉ፡፡

በመጨረሻም ይህ ዓይነት በአንድ አገር ህዝብ  ላይ የነበር ግፍ እና መከራ ሊቆም እና ለትዉልድ ማስተማሪ የሚሆነዉ ዕዉነተኛ ታሪክ እና ማስረጃ ቀጣይነት ባለዉ መልክ ሲዘከሩ እና ሲከበሩ ብቻ ይሆናል፡፡

ለዚህም ነዉ ከዕዉነት የማይነሳ  ዕርቅ እና ሠላም ምኞት ዘላቂነት ከዕምቧይ ካብ አይለይም እና ድካም እንዳይሆን ሁላችንንም የሚያሰጋን ነዉ የምንለዉ   ፡፡

                                                                                                              ማላጂ

                                                                                                   አንድነት ኃይል ነዉ

 

 

 

1 Comment

 1. Ethiopians need to appreciate and admire the correct leadership taken by the mayor and other civilian government administration authorities who made quick decision to pick up arms and defend the town of Majete, Amara Regional State within Ethiopia by taking the initiative to gather the civilian residents of the town of Majete in the Amara region arming them by encouraging the civilians to pick up arms and fight by bravely safe guarding their city for the whole three days and nights until.the genociders retreated saving Majete from being destroyed by those who tried to burn down Majete and commit genocide same as it was recently done in areas between Ataye and Kemisse in the Amara Regional State, within Ethiopia. The ongoing criminal investigations against the to people of Majete need to be dropped with the file permanently closed so no one opens the case ever again in the future on the Mayor and other residents of Majete , Amara Regional State for illegally engaging in gunfire battle by illegally possessing military weapons without the permission from the Amara Regional Government. In the case of an emergency the Mayor had the constitutional.madate to deputize anyone so the action of the Mayor of Majete took need to be considered as the Mayor exercising the Constitutional right by armi g the civilian residents of Majete to defend Majete.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.