አቶ ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

1

178771973 5406654259376025 8733381978472897238 n

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን እንዲመሩ መሾማቸው ታወቀ።

አቶ ተኮላ ከትናንት ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መመደባቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከሁለት ዓመታት በላይ በኃላፊነቱ ሲሰሩ ቆይተዋል።

አዲሱ ኮሚሽነር አቶ ተኮላ ከሦስት ዓመት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል።

ከዚያ በፊትም በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣ የአምባሰል ወረዳ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሠርተዋል።

በተጨማሪም አቶ ተኮላ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ዋና ኮሚሽነር የነበሩ ሲሆን በሠላም ማስከበር ሥራ ላይም ተሰማርተው የበኩላቸውን ተወጥተዋል።

የፌደራል ፖሊስ መሥሪያ ቤትን ከተቀላቀሉ በኋላም በምርመራ ቢሮ፤ የፋይናንስ እና ሎጂስቲክስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው አገልግለዋል።አቶ ተኮላ በሠላም እና ደኅንነት የማስተርስ ዲግሪ አላቸው።

ቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው አቶ ተኮላ ወደ ኃላፊነት የመጡት።

በተለይ በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለው ጥቃት ቁጥሩ በውል የማይታወቅ የሰው ሕይወት አልፏል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩም ከቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል።

ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ‘በግጭቱ’ 200 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ዘግቧል።

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል የሚያወግዙና እንዲቆም የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ባለፈው ሳምንት ለተከታታይ ቀናት ተካሂደዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር መግለጫ ሰጥተው ነበር።

አቶ አገኘሁ በመግለጫቸው ፤ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም ገልጸው፤ “ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ እንዲህ ሆነ እያልን ባለንበት ሁኔታ፤ በራሳችን ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞን ጥቃት ተፈፅሟል” ብለዋል።

በጥቃቱ በርካቶች መገደላቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ጥቃቱን የፈፀመው ኃይል የሰለጠነ፣ የታጠቀ ኃይል እንደሆነና ኃይሉ ከተለያየ አካባቢ ሰልጥኖ የመጣ፤ ወይም በአካባቢው ያለ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም “ጥቃት ለምን ደረሰብን ሳይሆን ጥቃቱ ሲደርስብን የት ነበርን? ምን እያደረግን ነበር? የክልሉ የጸጥታ መዋቅርምን ይሰራ ነበር?፣ የክልሉ የመረጃ መዋቅርስ ምን ነበር?” ሲሉ የጸጥታ መዋቅሩን እንደሚገመግሙና ያጋጠሙ ችግር ለመፍታት እያጣራን ነው ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ ተኮላን ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርነት ያመጣቸው ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳሉት በጸጥታው መዋቅር ላይ የተደረገ ግምገማን ተከትሎ ሊሆን ይችላል ሲል

ቢቢሲ

1 Comment

 1. ታዋቂ የሰልፍ እና የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎችን እንስራ ፤ የወጋን መልሶ በአማራ ክልል መሾም በአሁኑ ጊዜ ለምን ይሆን?

  የፌደራል ፖሊስ እራሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማጉላላቱን እና በአዲስ አበባ የብልፅግና ቢልቦርድችን በመጠበቅ ከሚያጠፋ ጊዜውን ትንሽ አስተርፎ ጊዜውን ለምን የዘር ጭፍጨፋውን አትኩሮት ነፈገው የሚለውን ሪፎርሙን የተዋሀዱት ኮሚሽነር ተኮላ ቢመልሱልን ጥሩ ነው?

  ሪፎርሙን የተዋሀዱት ኮሚሽነር ተኮላስ በአማራ ክልል ዛሬ ስለሚታስሩት እና ስለሚደበደቡት የአማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ምን ያህል ያውቃሉ?

  የሾፌሮች ደህንነትንስ ለማስጠበቅ ለሪፎርም አጋሮቻቸው የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ምን ይመክሩ ይሆን ?

  ” በአማራ ክልል ብቻ ከ66 ሺ በላይ ዜጎች በማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ ”

  https://amharic.ethsat.com/በአማራ-ክልል-ብቻ-ከ66-ሺ-በላይ-ዜጎች-በማረሚ/

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.