ዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን ያገኘው የጠቅላይ ሚኒስተሩ የትላንት የሶሪያ ስደተኞች ጉብኝታቸው

2

ዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን ያገኘው የጠቅላይ ሚኒስተሩ የትላንት የሶሪያ ስደተኞች ጉብኝታቸውና የፍጥር ፕሮግራማቸው ህጻኑዋን ጭምር ሲያወሩ የሚያሳየውን እነ አልጀዚራ ትኩረት ሰጥተው ዘግበዋል። ትኩረት ያልሰጡት የአማራ ብሔር ላይ ያለጣጠረው ግድያ እና ሞት በቃ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነው። የሚያስገርመው በኢትዮጵያዊነት ስም የሚነግዱ ሞት በቃ የሚለው ሰልፍ ለአገር ስጋት ነው ይላሉ። ግብጽ ትዝ ትላቸዋለች። አገሪቱን ወደ ሲሪያ ለመቀየር እየተጋ ካለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊት እና የተጠናከረው ጭፍጨፋን እንደ እንጀዚራ ያን ያህል አያሳስባቸውም።

ሰብዓዊነት በጠቅላዩ ሚዛን ግልጽ ነው። የሲሪያን ስደተኞች ያህል ትኩረት ያላገኙት ከአጣዬና አካባቢው ።
፣ወለጋ እና መተከል የተፈናቀሉ አማራ ሙስሊሞች ግን ጾማቸውም ሀይማኖታቸውም ሌላው ቀርቶ ለሙስሊሙ መብት እንከራከራለን የሚሉ ትዝ አይላቸውም።ጉራ ፈርዳ ላይ የተገደሉት የእስልምና ዕመነት ተከታዮች ናቸው። ማን ጮኸላቸው? የአማራ ሞት በቃ የሚለው ብቻ።አማራ ከሆነ ሙስሊም ሆን ክርስቲያን ሲገደል አይተናል። ሙስሊምነትን ነጥለው አጀንዳ የሚያደርጉ እነዚያ ወገኖቻቸው ተገለው የተረፉት ሜዳ ላይ ሲወድቁ አይደለም። ለፖለቲካ ትርፍ ግጭት ለመፍጠር እና አማራውን እርስ በእርሱ ለመከፋፈል የተወጠነው የሞጣ መስጊድ ቃጠሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ብዙዎችን አሳስቦዋል።የሁሉም የዕምነት ስፍራ መጠበቅ አለበት። መቃጠል መውደም የለበትም። ቤተ ክርስቲያንም መስጊድም፣ጸሎት ቤትም ሆነ ምኩራብ ሁሉም ተቻችሎ የኖረበት አገር ሁሉም ተጠብቆ እንዲኖር የማይሰራ ሥርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ አይፈለግም። አጣዬ ላይ ስለተገደሉ ሙስሊሞች ትንፍሽ ሳይል ስለ ጎንደር ሙስሊሞች ልጩህ የሚል ራሳቸው የጎንደር ሙስሊሞች ችግራችንን እኛው እንፈታለን ብለው ያሳፈሩዋቸው ለዚህ ነው።
178528776 4249729915048604 5066925271159340007 n
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አካሄድም አስመሳይነት ብቻ ሳይሆን ከአቅማቸውም ሥልጣናቸውም በላይ ውሰጣቸው ያለውን የሕዝብ ንቀት ያጋለጠ አጋጣሚ ነው።
ህብር

2 Comments

  1. የላይኛውን ፎቶግራፉን ምስል ” የበሻሻው የሳምቡሳ ሌባ”

    የመሀከለኛውን ፎተግራፉን ምስል “የበሻሻው የህፃናት ማስፈራሪያ ”

    የመጨረሻው የታችኛውን ምስል “የአብይ ራዕይ ስለ ኢትዮጵያዊነት” ብለን ሰይመናቸዋል።

  2. ይሄ አቢይ አህመድ የሚባል የኦነግ ዱርየ በሻሺመኔ በአሪሲ ከ300 በላይ አማራወችንና ኦሮቷዶክሰን አሸጨፍጭፎ ችግኝ ተከላ ላይ ነበር የሚውለው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.