/

‹‹ የብሄርተኞች ቡቲክ!!! አርበኞች ግንቦት ሰባት የህወሓት ጥላ ወጊ!!! ›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

1

የብሄርተኞች ቡፌ/ቡቲክ (“Boutique Nationalism”)1 ፕሮፌስር ኡቫል ኖኦም ሃራሪ

የሄግልን ዴሊክቲካልና ሂስቶሪካል ማቴሪያሊዝም (ቁስአካል) ማርክስ በአፍጢሙ የቆመውን በእግሩ እንዲቆም አደረኩት ባለ መቶ አመቱ ፕሮፌስር ኡቫል ኖኦም ሃራሪ፤ በዓለም ብቸኛ የሰው ልጆችን የልብ ወለድ ታሪክ ፈጠሪ መሆናቸውና የመደራጀት ችሎታቸው መሆኑን አዲስ ግኝቱ አረጋግጦ፣ አበርክቷል፡፡ በዚህም መሠረት የሰው ልጅን ከሌሎች ዝርያዎች የሚለየው በብዛት ሆኖ በመደራጀት መሪ ሊኖረው በመቻሉ ሲሆን ሌሎች ፍጥረታት እንደ ንብና ገብረ ጉንዳን በህብረት ቢሠሩም እንደ ሰው ንቃተ ህሊና ስለሎላቸው ህብረታቸውን ሊጠቀሙበት አልቻሉም ይላል፡፡ ፕሮፌሰሩ የሰው ልጆች የራሳቸው ታሪክ አላቸው በዓለማችን ያሉ ኃይማኖቶች ከአንዱ በስተቀር ልብወለድ (Fiction) ናቸው፡፡ እያንዳንዱ አገር የራሱ የሆነ ልብወለድ ታሪክ ፈጥሮል፡፡ በዓለማችን ታላላቅ ብሄርተኛነት (Nationalism) ከአንድ ምእተአመት በፊት ከነበረው እየቀነሰና እየወረደ ሄዶል፡፡ የሃገራት ብሄርተኛነት ስሜት የተነሳ የሚቀጣጠል ጦርነት፣ አመፅና መገዳደል ቀንሶል፡፡ በታላቌ እንግሊዝ ጸሐይ አትጠልቅም፣ የጀርመን ናዚዝም፣ የጦልያን ፋሽዝም፣ የጃፓን ዲክታተርሽፕ፣ የእኔ አገር ይበልጣል፣ የኔ ዘር ይበልጣል ታሪክ አክትሞል፡፡ በዓለማችን ቅርብ የሰው ልጆች ታሪክ የአንደኛውና የሁለተኛው ዓለም ጦርነት፣ የፀረ- ቅኝ ግዛት ጦርነቶች፣ የቬትናም፣ የኩባ፣ ቀዝቃዛው ጦርነት፣ ይፈራ የነበረው የኒዩክለር ጦርነት ስጋት፣ (Nuclear War) ቀንሶ በጣም አሳሳቢ የሆነው የዓየር ንብረት ለውጥ (Climate Change) እንዲሁም የቴክኖሎጅ መቌረጥ (Technological Disruptions ) ስጋቶች ናቸው ይላል ፕሮፌስር ኡቫል ኖኦም ሃራሪ፡፡ የአውሮፓ ህብረት አገራቶች የብሄርተኞች ቡቲክ “Boutique Nationalism” ዘርግተው በጋራ የንግድ ግብይይት በጋራ እየበለፀጉ ናቸው፡፡

በአሜሪካ የጆርጅ ፈሎይድ በፖሊስ አሰቃቂ ግድያ የዓለምን ህዝብ ታሪክ ቀይሮል፣ የቀለም ልዩነት፣ የዘር ፣ የብሄር፣ የኃይማኖት ልዩነት የሚደረጉ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ከእንግዲህ በአለማችን ቦታ የላቸውም፡፡ በሃገራችን ሰው ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ፣ በድንጋይ ወግረው የሚገሉ፣ በቶርቸር ገርፈው የሚገሉ ጋንግስተሮች ሁሉ ቦታ የላቸውም፡፡ የሃገራችን የፖለቲካ ካድሬዎች የጥላቻ ንግግር በቃችሁ ሊባሉ ይገባል፡፡ ‹‹ዲቃላ›› ጁሃር መሃመድ፣ ‹‹መሬት እንጂ ሰው የለም››መረራ ጉዲና፣ ‹‹አትግዙ አትሽጡ አትለውጡ››በቀለ ገርባ፣‹‹እንደሰባበሩን ሰባበርናቸው›› ሽመልስ አብዲሳ፣ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ከንቲባ መሆን ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው” ብርሃነመስቀል አበበ የኦሮሞ የፖለቲካ ካድሬዎች የማንነት መታወቂያ ንግድ ቤቶች የሚያሰራጩት የጥላቻ ንግግርና በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋና በሃረር እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ራሳቸውን እንደ ባለአገር ሌላውን ህዝብ እንደመጤ የሚፈርጁ በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን ፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ፍትህና ርትህ ማስከበር አልቻለም፡፡

‹‹ኦነግ በዶክትር አብይ መንግሥት የሁለት አመት በትረ ሥልጣን ዘመን የኦሮሚያ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ መሠረት በኦነግ ሸኔ ‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣ 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው ፣72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን፣ እንዲሁም 23 (ሃያ ሥስት) ባንኮች መዘረፋቸውን የተደበቀ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል፡፡›› የህግ ሉዓላዊነት እስካልተከበረ፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እስኪሆን ድረስ ትግላችን ሊቀጥል ይገባል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከነእንከኑ አሰተካክሎና እርማቱን በጋራ ፈትቶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ መንግሥት ካለን ዋነኛው ስራው ይሄ መሆን ይኖርበታል እንላለን፡፡ ሰው የሚገደልበት፣ ችግኝ የሚፀድቅበት!!! ሀገር ሰው ሰው ያልሸተተ ዘረኛ የተረኛ ስሜት መጨረሻው አያምርም እንላለን፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይሄ ሁሉ የስብኣዊ መብቶች ጥሰት ሲከናወን ተከታትለው አለማጋለጣቸው ያሳፍራል፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሠራተኞችን እናመሠግናለን፡፡ በተረፈ ፕሮፌስር ኡቫል ኖኦም ሃራሪ የዓለማችን እውቁ የታሪክ ሰው፣ ፋላስፋና ፀሐፊ እስራኤላዊው ፕሮፊሰር ኡቫል ኖአህ ሃራሪ የሶስት መፅሃፍት ደራሲ ሲሆን መፅሐፉ ከሃያ አምስት ሚሊዮን በላይ ቅጂ የተሠራጨና በሀምሳ ቌንቌ በላይ የተተረጎመ አዲስ ፈር ቀዳጅ የዓለም ሥርዓት አዋላጅ ፀሐፊ በመሆኑ ዝናው በዓለማችን ላይ ናኘ፡፡ ሃራሪ በብዙ መገናኛ ብዙሃን ቴሌቨዝን፣ ራዲዩ፣ ጋዜጣ እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ፣ ጉግል ሰርች፣ ጉግል ማፕ፣ ኔትፍሌክስ እና አማዞን በተጨማሪም በተለያዩ ዩቲዩቦች ጋር ያደረገው ቃለምልልስ አድምጠው ይፍረዱ፡፡ 2
የሻብያ፣ የወያኔና ኦነግ ህብረት ፈርሶ ፣የሻብያ፣ የኦነግና አርበኞች ግንቦት ሰባት(ኢዜማ) ህብረት ምሥረታ

በድሮ ጊዜ ጥላ ወጊ እንደ ምትህተኛ፣ ጠንቆይ፣ አሊያም ሞርተኛ ይቆጠራል፡፡ በደገመበት ሹል ነገር የሰውዬውን ጥላ በመውጋት ሰውዬውን ህመምተና ያደርጋል የሚል እምነት ነበር፡፡ በዛን ዘመን ሁሉም ሰው ጥላው እንዳይወጋበት ጥላውን ይጠብቅ ነበር፡፡ የጥላ ወጊዎች ችሎታ ታዲያ እንኳን ሰው የዛፍ ጥላ ወግተው ያደርቁ ነበር ይባላል፡፡ ዛሬ ጥላው የተወጋ ሊያውም አከርካሬቸው ላይ የተወጉ እልፍ የዓለማችን ሰዎች ኢንተርኔት፣ ሞባይል በፌስቡክ ሲጎረጉሩ ጥላቸው እንደተወጋ አያውቁትም !!! እንዲያ ነው ‹‹ አርበኞች ግንቦት ሰባት የህወሓት ጥላ ወጊ!!! ›› የሆነው፡፡ ‹‹አንተ ስትተወው እኔ አልተውም ወይ፣የዛፍ እንኳን ጥላ ይዞዞር የለም ወይ›› አስቴር አወቀ ::

አርበኞች ግንቦት ሰባት ባህር ማዶና ኤርትራ በርሃ እያለም ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር የነበረው መርህ አልባ ግንኙነቶች ውስጥ በጥቂት ግለሰቦች በተቆቆመ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መሪ ሌንጮ ለታ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ጋር በጥምረት ይሠራ የነበረ ድርጅት ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ኢዜማን በመመሥረት ከዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ/አዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በጣምራ በመስራት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ጥላ የወጋ ድርጅት ነው፡፡ ኢዜማ በእነዚህ የኦሮሞ ድርጅቶች የሃገሪቱ የፖለቲካ በትረ ስልጣን በምርጫ ወይም በሜንጫ እንዲያዝ አብሮ የሰራ ድርጅት ነው፡፡ የሃያ ሰባት አመት ‹‹የሻብያ፣ የወያኔና ኦነግ›› ህብረት ፈርሶ፣ ሁለተኛ አመቱን የያዘው ‹‹የሻብያ፣ የኦነግና አርበኞች ግንቦት ሰባት (ኢዜማ)›› ህብረት ምሥረታ የተተካው፡፡ የነአምን ዘለቀ ምስክርነት፡-

“እኔ፦ ነአምን ዘለቀ ጃዋር መሃመድን ሳውቀው 10 (አስር) አመት ሞልቶታል። በ2010 ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ በሚል መሪ ርእስ በተዘጋጀ የ3 ቀናት ጉባኤ(Ethiopia and Horn of Africa Conference) የጉባኤው ዋና አስተባባሪ ነበርኩ። በርካታ ምሁራንን፣ የፓለቲካ መሪዎችን፣ እክቲቪስቶች ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ኤርትራውያን ምሁራንን፣ እንዲሁም ከፈረንጆችም ምሁራን እና ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት የቀድሞው የአሜሪካ አምባስደር ዴቪድ ሺኒን ያካተተ ፣ በልዩ ልዩ ሚዲያዎች ፣ በVOA ጭምር ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ስኬታማ ጉባኤ ነበር። እኔና አብረውኝ የነበሩ የመድረኩ አዘጋጅ ጓዶቼ ልዩ ልዩ ተናጋሪዎችን መጋበዝ ስንጀምር በትግሉ የምቀርባቸው ሰዎች ጃዋርን ወጣትና ንቁ ምሁር ብለው አስተዋወቁኝ ። በአካል ተገናኝተንም ተወያየን። በጉባኤው ላይ ተገኘቶ ጥናታዊ ጽሁፍ እንዲያቀርብም ግብዣ አቀረብኩለት። ከህዝብም ጋር ለመጀመሪያ ግዜ በሰፊው የተዋወቀበት መድረክ ያ መድረክ ነበር ለማለት ይቻላል። (ጃዋር በወቅቱ ኢትዮ ትዩብ የተቀረጸውን ቪዲዮ ላይ ስሜን በማንሳት ያቀረበውን ምስጋና ፈልጎ ማየት ይቻላል’’)

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጽያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች” መጽሐፍ ላይ ያለኝ ዳሰሳ

2.ግንኙነታችን እኔ ለመጀመሪያዎችይ 5 አመኣታ በ ስራ አሰፈጻሚነት ያገለገልኩበት (2010-2015) በኢሳት ቴሌቪዥንና ሬዴዮ (ኢሳት) ላይ በተደጋጋሚ ጃዋር የቀረበባቸው ፕሮግራሞች ጋር በተያያዘም ይቀጥልና፣ OMN የተባለውን ሚዲያ ጃዋር ከመሰረተም በኋላ የጸረ ወያኔ ትግሉን ዋና ኢላማውን እንዳይስት፣ አብሮ ፣ ተባብሮ ለመታገል፣ በሚዲያም ሆነ በሌላም ዘርፎች በልዩ ልዩ ጊዜዎች የተደረጉ ጥረቶችና ውይይቶችን ያካትታል።” 1

• ግንቦት ሰባት፣ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኦብሳ፣ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መሪ ሌንጮ ለታ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ጋር በጥምረት ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ ነበር፡፡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር (ፕሮፌሰር)፣መረራ ጉዲና ጋር ግንቦት ሰባት ለኦሮሞ ክልላዊ ድርጅቶች የክርስትና አባት (God Father) በመሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ተቀባይነት እንዲያገኙ የማስተዋወቂያ አገልግሎት ሰጥቶል፡፡

• ግንቦት ሰባት ሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች በፖለቲካ ፕሮግራማቸው ኦነግ ጋር አንድ መሆናቸውን ያውቃል፡፡ በዚህም መሠረት ‹‹ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ!!!›› በማለት ለማ መገርሳ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ከማል ገልቹ ይገኙበታል፡፡ ‹‹ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም›› የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)፣ ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኦብሳ፣ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ጋር በጥምረት ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ጁዋር መሃመድ ቀጥሎ በነደፈው ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› አጀንዳ በቀረፀው መሠረት የኢትዮጵያን ህዝብ በዕለት ከዕለት የብሄርና የዘር ፍጅት እንዲሁም የኃይማኖት ግጭት ውስጥ በመዶል ህዝቡ በፍርሃት ውስጥ ተዘፍቆ እንዲኖር በማድረግ፣ የህዝቡን አትኩሮት ወደ ሌላ በማዞር የፖለቲካ ሴራ የኦሮሞ መንግሥት ማስቀደምና የኦሮሞን የኢኮኖሚ ዘረፋ መገንባት ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

• ‹‹ኦሮሞ ይቅደም›› (Oromo First)፡- የኦሮሙማ ፕሮጀክት ኮርዲነተር ጁዋር መሃመድ ባስነሳው የተከብቤለሁ የ86 ሰዎች በድሬዳዋ፣ ሀረርጌና ዶዶላ ከተሞች የተደረገ የግፍ ግድያ ያልተቃወመ፣ ቡራዩ ጭፍጨፋ፣ ኩዩ ፌጮ የኮንዶሚንየም ዘረፋ ያልተቃወመ የጁሃርን የፖለቲካ ሴራና ኢኮኖሚ ዘረፋ ያላጋለጡ የሥልጣን ሱሰኞች ናቸው እንላለን፡፡ ባለፈው 28 አመታት ጀምሮ ኦነግ በመላ ሀገሪቱ ኢንቁፍቱ፣ በደኖ፣ ጉራፈርዳ፣ ጋምቤላ ቢኒሻንጉል ጉሙዝ ያከናወነው የዘር ጭፍጨፋ ግንቦት ሰባት አያውቅም ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡ ጀዋር መሃመድ፣ ሌንጮ ለታ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ጃል መሮ፣ ወዘተርፈወች በዘር ማጥፋት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መቅረብ አይቀርም አንላለን፡፡
• ኦነግ በ1984ዓ/ም ኦነግ ከ300 በላይ የአማራ ተወላጆች ላይ ሐረር ውስጥ በደኖ፣ጋራ ሙለታ፣ጨለንቆ፣ በኢንቁፉቱ ገደል፣ የፈጸመው የዘር ፍጅትና ጭፍጨፋ በተበዳዬቹ አልተረሳም ወንጀለኞቹ ለፍርድ አልቀረቡም ተዋናዬቹ ኦነግ፣ አህዴድና ህወሓት ናቸው፡፡ ይህን ቪዲዬ፣3 ከመቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ አስራአምስት ሽህ ህዝብ ብቻ ተመለክቶታል፡፡ የቅንጅት፣ የግንቦት ሰባት አመራሮች ግን ይህን ወንጀል በእርግጠኝነት ያውቃሉ እንላለን፡፡ ኦነግ ምን ዓይነት ዘረኛ ወንጀለኛ ድርጅት እንደሆነ እያወቁ ኦነግን ማስተዋወቅ ለዛሬ በደላችን የእናንተ አስተዋፅኦ አለው እንላለን!!!

በተለያየ ጊዜ በኦነግ ደራሼ ና ጉራፈርደ፣ የዘር ፍጅት ተከናውኖል፡፡ ከሃያ ስምንት አመታት በኃላ፣ በ2012ዓ/ም ኦነግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰውን የጌዲኦ፣ሐረር፣ድሬዳዋ፣ ሱማሌ፣ ከሚሴ፣ አጣዬ፣ ደራ ያደረሰውን የሽፍትነት ስራ አርበኞች ግንቦት ሰባት አውግዘው ተቃውሞ አስምተው አያውቁም፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ/ ብልፅግና ቀጣዩን ምርጫ በምርጫ ወይም በሜንጫ እንዲያሸንፍ በማማከር በተወዳዳሪነት ግን በመናጆነት ( pacesmaker ) በማገልገል ላይ ኢዜማ በባርነት ያገለግላሉ፡፡ በስብአዊ መብት ጥሰት የቀይ ሽብር ወንጀለኞች አሁን ድረስ እየታደኑ ይያዛሉ፡፡ የኦነግም ወንጀል ለፍርድ መቅረቢያው ከሁለትና ሦስት አመታት በሆላ ለዓለም ፍርድ ቤት መቅረባቸው አይቀርም እንላለን፡፡

• አርበኞች ግንቦት ሰባት ፍኖተ ካርታ ነድፎ ከዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ጋር ተደራርሮ ወደ አገር ቤት ይገባል ብለን ነበር የጠየቅነውና የጠበቅነው፡፡ ነገር ግን ከኤርትራ በርሃ የኢሣያስ አፈወርቂን መልዕክት ወደ ዶክተር አብይ አህመድ ሲያመላልሱ እንደሰነበቱ ሃቁ አንድ ቀን ይወጣ ይሆናል፡፡ ቄሮ፣ ፋኖና ዘርማበህዝባዊ እንቢተኛነትና ትግል ወያኔ በስብዓዊ መብት ጥሰት በአለም ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ፈርቶና በኤች አር 128 ክስ ታድነው እንዳይያዙ ፈርተው ወያኔ እንደአበደ ውሻ ጭራዋን ወሽቃ ፈርጥጣ መቐለ እንደገባች ቀረች፡፡ የአዲስ አበባ ልጆች ሲጫወቱ ወያኔ መቐሌ፣ መንግስቱ ሃራሬ!!!

• ግንቦት ሰባት፣የኤርትራውን የሻብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያ ኦዴፓ ብልፅግና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አገናኝ መኮንን በመሆን የድለላ ስራ በመስራት ሀገር ሳይወክላቸው ያለ አንዳች መርህና የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማሲያዊ ሳይመሠረት በማፍያ ግንኙነት ያገናኘ ድርጅት ነው፡፡

• ግንቦት ሰባት በጸረ ዴሞክራሲያዊነት መርህ ፖለቲካ ሴራ የኢሳትንና ኢትዮ 360 ወጣት ጋዜጠኞችን ያጣሉ የማፍያ ድርጅት ነው፡፡ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ይዞቸው የመጣውን ሠራዊቱን የከዳ ብቸኛ ሆድ አደር ድርጅት በመሆኑን የበርሃ ጎዶቹን በአሞሌ ጨው የለወጠ ሰው ሰው ያልሸጠተ አድርባይ ድርጅት ነው፡ የአምሃ ዳኘው በመጽሃፋቸውና በቃለ መጠይቅ የኢዜማን የፖለቲካ እድርባይነትና የፖለቲካ ሴራ አስረግጠው ለህዝብ አስረድተዋል ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡ አቶ ንአምን ዘለቀ፣ የወጡበትን ምክንያት ህፃን ልጅ አያሳምንም፡፡ ግንቦት ሰባት፣ ከህዝብና ዲያስፖራ የሰበሰቡትን ገንዘብ በህቡዕ ቢዝነስ በመመስረትና ንብረትና ኃብት በማፍራት በደም ገንዘብ ከበርቴ የሆነ ድርጅት ነው፡፡ አርበኞች ግንቦት ሰባት ቅንጅት ሳለ ስለ ወያኔ ኢንዶውመንት ፈንድ፣ ፓርቲ ቢዝነስ፣ ቴሌቪዝንና ሬዲዬ ክፍፍል፣ በመንግስታዊ መኪኖች አጠቃቀም ወዘተ ይከራከር ነበር፡፡ ዛሬ ድምፁን አጥፍቶ የራሱን ቢዝነስ ይሰራል የራሱ ቴሌቪዝን፣ሬዲዬ፣ ቢሮ ወዘተ ስላለው አይሞገትም፡፡

  1. ‹‹ እነ አባይ ጸሃይና የወያኔው ስርአት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሚል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለመጫን በተደረገው ሙከራ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከአምቦ ጀምሮ በልዩ ልዩ አካባቢዎች በተቀጣጠለበት ወቅት በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ (VOA) በጋራ ሆነን ቃለ ምልልስ የሰጠንበት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የአመጽም የእምቢተኝነትም ትግሎች ለጋራ ለማሰባሰብና ለማናበብ የተደረጉ በርካታ ጥረቶችና ግኙነቶች ቀጥለው ፣ እንዳንዴም ልዩ ልዩ ግጭቶች ተከስተው እሰከ 2018 ለውጡ እስኪመጣ ድረስ የቀጠሉ ነበሩ።››

  2. ‹‹ ጃዋር ኦኤሜንን(OMN) ይዞ ኢትዮጵያ ከገባም ከመንግስት ለውጥ በኋላም ጥሩ ሲናገር ይህን እንዲቀጥልበት መልክት በቴክስት በመላክ፣ በማበረታት፣ከሀገር መረጋጋት፣ ለብሄሮች አብሮነትና ሰላም የማይበጁ ፣ ጽንፈኛ አመለካከቶች ያንጸባረቀ ሲመስለኝ ደግሞ ይህ ሀገራችንና የልዩ ልዩ ማህበረስቦች አብሮነት የማይረዳ መሆኑን እየነገርኩት ፣ ጥያቄዎችን ሳነሳለት፣ ማስታወሻም በየጊዜው ስጽፍለት ቆይቻለሁ። ሰፊ የፓለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፣ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ስርአተ መንግስት (state) እንዲፈርስ እንደማይፈልግ ፣ ሁሉም ተሸናፊና አውዳሚ ሊሆን ወደሚችል ሁኔታ መገባት እንደሌለበት፣ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ የተነጋገርንባቸው ርእሰ ጉዳዮች በመሇንቸው፣ ከጃዋር ጋር ለመግባባት ፣ ከሌሎችም ጋር መነጋገር መሞከር እንዳለበት በማመን፣ ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች ወደ ብሄራዊ መግባባት ኣንዲመጡ ካለኝ ጽኑ ፍላጎት አኳያ የተደረጉ ነበሩ። አስከ ዛሬም ድረስ ከጃዋር ጋር ግንኙነት እንዳለኝ ምንም ከህዝብ ደብቄ የማፍርበት ጉዳይ እንዳልሆነ በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ። ከህወአቶች በስተቀር ከጃዋር ጋር ብቻ ሳሆን ከአብዛኞቹ በሀገር ውስጥም በውጭም ከሚገኙ ልዩ ልዩ የፓለቲካ ሃይሎችና ቡድኖች፣ እንዲሁም ግለሰቦች ጋር ከትግሉ ጋር በተያያዘና ለአለፉት በርካታ አምታት ትውውቅ፣ ቅርርብና፣ ግንኙነቶች እንደነበሩኝም ለማንም መገመት አስቸጋሪ አይሆንም።››

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎንደሩን ሰልፍ በጨረፍታ

የኢትዮጵያ ህዝብ እርሶ ከኦነጎች ጋር ያደረጉት ትውውቅ፣ ቅርርብና፣ ግንኙነቶች መታረጃው ሆነ እንጂ ምን ፈየደና እናመስግንዎት!!! እርሶም፣ አቶ አንዳርጋቸውና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኦነጎች ጋር ያደረጋችሁት መርህ አልባ ግንኙነት በአቶ አምኃ ዳኘው ፍንትው ብሎ ተገልፆልናል፡፡ ስለስምዎ አይጨነቁ፣ ስም ድሮ ቀረ!!! በዚህ ደሃ ህዝብ ላይ ሁሉም ስሙን ለመትከል ይሯሯጣል፣ እንደ አብይ ችግኝ ብትተክሉ ይቀላል፡፡ ለዓመታት ግንቦት ሰባትን ደግፈን ገንዘባችን፣ እውቀታችንን፣ ጊዜችንን ያቃጠልነው ሃገራችን ከገባችበት መቀመቅ እንድትወጣ ‹‹ የህገ-መንግስት እንዲቀየር፣ ዘረኛ የቌንቌ የፌዴራል ሥርዓተ መንግሥት እንዲወገድ፣ የቡድን/ የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች መብት ተከብሮ ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ የመገንጠል መብት (አንቀፅ 39) እንዲሰረዝ፣ የዜግነትና ቡድን መብትና ነፃነት እንዲከበር፣ መሬት የግል ኃብት ሆኖ መሸጥና መለወጥ መብት እንዲከበር ነበር እናንተን ያነገስናችሁ፡፡ ቃላችንን እንደ ትላ ወጊ ወግታችሁ በላችሁት!!! በኢትዮጵያ ህዝብ የተጠላችሁት በዚህ የፖለቲካ ሴራችሁና የተላላኪ የፖለቲካ ቡችላ ሆናችሁ ራሳችሁን ችላችሁ በሁለት እግራችሁ መቆም ስለተሳናችሁ ህዝብ ጠላችሁ!!!

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት መርህ አልባ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የመከላከያ ኃይል ግንኙነት በጊዜው መልክ ሊይዝ ይገባል እንላለን፡፡ የሻቢያ፣ ኦነግና ግንቦት ሰባት ኢዜማ የጦር አበጋዞች መርህ አልባ የፖለቲካ ግንኙነትና የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ቀጣይ ፍንጮች ይስተዋላሉ፡፡ የሻቢያ የኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ ሴራ በቃህ ሊባል ይገባዋል እንላለን፡፡ ኢሳያስ እንኮን ለኢትዮጵያ ለኤርትራ ልጆችን ለፈጀ ፋሽስት ጥብቅና መቆም በታሪክ ያስጠይቃል፣ መስዋት የሆኑ የኢትዮጵያዊያን ደምና አፅም በሰላም እንዳይተኛ እረፍት ይነሳል በምንም መመዘኛ ለዚህ ፋሽስት አገራችን ዳግም አትንበረከክም እንላለን፡፡ መንግሥት ይሄዳል ይመጣል የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ አንድነት ሁሌ እየለመለመ ይቀጥላል፡፡
• የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ኦዴድ ብልፅግና የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር መካለል እንዳለበት ሻብያና ወያኔ ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ኢዜማ ገፀ በረከት አቅርቦል፡

• ግንቦት ሰባት ኢዜማና ብአዴን/ አዴፓ በአማራ ህዝብ ላይ ከኦዴፓ/ብልፅግና ጋር በመሆን በአማራ ድርጅቶች ላይ አብንና ፋኖን ወዘተ ለማዳከም የሚያደርጉት የፖለቲካ ሴራ ይቁም፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአማራ ቴሌቪዝን ማርች 19 ቀን 2020 ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ‹‹ አማርኛ ቆንቆ ተናጋሪ እንጂ አማራ የሚባል ዘር የለም!!! ›› ‹‹እኔ ከአማራ ክልል ውጪ ነው የምኖረው ለምሳሌ ያህል አዲስ አበባ፡፡›› በማለት አዲስ አበባ የአማራ ክልል ውጪ ነው፣ የፌዴራል መንግሥቱ ካላዳነኝ፣የአማራ ክልል ሊያድነኝ አይችልም በማለት ለኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ፓርቲ የካድሬነት ሥራ ይሠራል፡፡ ግንቦት ሰባት ኢዜማ በአማራ ክልል ቢያሸንፍ ህዝቡን ከታች ጀምሮ የስልጣን ባለቤት በማድረግ የአማራን እድገትና ብልፅግና እንደሚያመጡ ተናግረዋል፡፡›› ኢዜማ አማራ ክልልን ሙጥኝ ያለው ለዚህ ነው፣ በሌሎች ክልሎች በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብ ወዘተ የጫማውን አፈር እያራገፉ ያስወጡት የፖለቲካ ሴራውን በማወቃቸው ነው፡፡

• ሻብያ ኦነግ ትጥቁን ሳይፈታ በትግራይ በወያኔ በኩል በአቦይ ስብሃት ተባርኮ የገባውን ማስታወስ ብልህነት ነው እንላለን፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር ከአስር ትንንሽ ወደ መቶ ትንንሽ ክልላዊ መንግስትነት በመከፋፈል በወሰንና ድንበር የማያባራ ጦርነትና ግጭት ከትቶ የእራሳቸውን ህልውና የማስጠበቅ የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘረኛ የጦር አበጋዞች ክልላዊ መንግስቶች እንደ አሸን በፈሉ ቁጥር የድንበርና የወሰን የጦርነት ግጭቶች እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል ጦሱም እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ፣ አፍጋኒስታ፣ ኢራቅ ህዝብ የጦር አውድማ፣ የማያባራ የውክልና ጦርነት መዛመቱን ማስታዋል ይገባል እንላለን፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተሰደው የመጡትን የሱማሌ፣የሶሪያና የየመን ዜጎችን እያየን ከእነሱ መማር የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

• የኢትዮጵያ ዶክተር አብይ አህመድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳይና የመከላከያ ግንኙነቶች በመርህ ላይ የተመሠረተ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለህዝብ ይፋ መሆን አለባቸው እንላለን፡፡ በሁለቱ ሃገራት መኃል ያለውም የድንበር ግጭት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአግባቡ መፈታት ይኖርበታል እንላለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መቼ ነው ልሂቃኖቻችን የሳይንስን መርህ ተከትለው የሚናገሩትና የሚጽፉት?

• ግንቦት ሰባት ኢዜማ፣ የሚያደርግበት አብዩት አደባባይ ሃዲያ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ ላይ ሁለት ወለል ያለው ትልቅ አዳራሽ፣ መኪኖች፣ ገንዘብ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ብልፅግና ተበርክቶለታል:: ዳክተር አብይ የራሱን መፅሃፍ በምን ያህል ኮፒና ገንዘብ እንዳሳተመው በይገለፅም የአንዳርጋቸው ፅጌ መፅሃፍ በ3.5 ሚሊዮን ብር 30 ሽህ ኮፒ አሳትሞለታል፣ መኖሪያ ፎቁን አስመልሶለታል፣ መኪና ሰጥቶታል፡፡
• ግንቦት ሰባት ኢዜማ፣ ህወሓት የትግራይ ክልልን ገንጥሎ፣ እስከአፍንጫው ድረስ መከላከያ ሠራዊት ገንብቶ፣ ልዩ ኃይል አሰልጥኖ፣ ሚሊሽያ አስታጥቆየአማራና የአፋር ግዛትን ቀምቶና የደህንነት ኃይሉን ገንብቶ የፌዴራል መንግስት መዳኘት ተስኖታል፡፡

• ግንቦት ሰባት ኢዜማ፣የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሃረር ከተሞች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር መካለል አለባቸው ብሎ ሲጠይቅ ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ኢዜማ ጆሮዳባ ብለዋል፡፡

• ግንቦት ሰባት ኢዜማ፣የፌዴራል ፖሊስ ዋና ፅ/ቤት፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ፅ/ ቤቱን አዲስ አበባ ተደርጎል፣ ማዕከላዊ እዙ አዲስአበባ ሆኖ በመላ ኢትዮጵያ ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት ለኦሮሚያ ፖሊስ ተሰጥቶል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የተረኝነት አገዛዝ በአጭር ጊዜ ይገረሰሳል፡፡
• በኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ፖሊስ ስልጠና ለ30ኛ ጊዜ በብዙ ሽህዎች ተመርቆል፡፡ ከሜቴክ የ300 ሽህ የክላሽንኮብ መሣሪያ ከአንድ ሚሊዩን ጥይቶች ለኦሮሚያ ክልል ማስታጠቅ የዘረኝነት ፖለቲካ ለዘር ፍጅት ዝግጅት አንድ እርምጃ መሰናዶ ነው እንላለን ይሄን ድርጊት፣ ብርሃኑም አንዳርጋቸውም፣ አንዱዓለምም፣የሽዋስም ኢዜማም መፅሃፉም ዝም ብሎል፡፡ ለሆዱ ያላደረው የህዝብ ልጅ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ እንዳለው ‹‹ያልተረጋጋ ፖለቲካ ባለበት ሁኔታ ቅድሚያ የምትሰጠው የህዝብን ህልውና ነው፡፡ ህልውናው ደግሞ የሚከበረው በሰለጠነና በተደራጀ ኃይል ነው፡፡ ያልተደራጀ ኃይል ህልውና ሊያስከብር አይችልም፡፡ ስለዚህ የተደራጀ የሰለጠነ ኃይል ለአካባቢው ሠላምና ደህንነት ዘላቂ እንዲሆን ያደርጋል፡፡›› የአማራ ክልል የሞግዚት አስተዳደር ያበቃል !!! አማራ ህዝብ ለመብቱና ነፃነቱ የአልገዛም የእንቢተኝነት ትግሉን በተደራጀና በሰለጠነ ኃይል ይቀጥላል!!! ግንቦት ሰባት አመራሮች

• የአዲስ አበባ ክልል የከተማ እድገት ተቀጭቶል፣ የህብረተሰቡን ያሳተፈ እድገት ከተማውን እያሰፋ ገጠሩን ከተማ በማድረግ፣ህዝቡን ተጠቃሚ በማድረግ እያዘመኑ የኮዬ ፈጫ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከቤት ሠሪዎች ገንዘብ ተዋጠቶ የተሠራ የህዝብ ኮንዶሚኒየም በኦሮሚያ ክልል ተወረሰ፣ የቤት ግንባታ ቆመ፣ ህዝብ ከባንክ ገንዘቡን ቆጥቦ ቤት እንዳይሠራ ታግዶል፡፡ በኦሮሞ ክልል የለገደንቢ የወርቅ መዕድን በአመት እስከ አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ኃብት ቆሞል፡፡ በዶክተር አብይ መንግሥት በዚህ ሁለት አመታት ውስጥ መፍትሄ መስጠት ተስኖቸዋል፣ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ወድቆል፣ ህዝቡ በኑሮ ውድነትና በኮሮናቫይረስ በሽታ አቅሉን አጥቶል፡፡ ችግኝ መትከል ጥሩ ነው ለውጡ ሰው ሰው እንዲሸት ኢኮኖሚው እንዲያድግ የኮንዶሚኒየሙን የወርቁን ችግር ይፍቱ እንላለን፡፡

{1} ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ “አማራ ክልል ብዙ መንቀሳቀስ አልቻልንም!”፣ “ኮሽ ባለ ቁጥር መግለጫ አናወጣም”፣ “ባላደራ ምናምን የሚባለው ነገር እኔ ብዙ አይመቸኝም”፣ “አብይ 5 መፅሐፎች ፅፎ ያሳተመ ምሁር ነው”፣ “እኔ እራሴ የአብይ አህመድ ያህል ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” ይለናል ‹‹ያህያ ባል ጅብ አያስጥልም›› አለ ያገሬ ሰው፡፡

{2} አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፤ ‹‹አዲስአበባ የአያቶቼ ጥጃ ማሰሪያ!!!››፣ ‹‹ፍኖተ ካርታውን ለአብይ የሰጠሁት እኔ ነኝ!!!››፣ ‹‹የሚገደሉትንና የሚገድሉትን ስም ለአብይ ሰጥቼዋለሁ!!!››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ታሪክ ነው!!!››፣ ‹‹አማራ የለም!፣ የአማራ ብሄርተኝነት የለም!!!አማራ የሚባል ብሄር የለም!!!››፣ ፣‹‹በኢትዮጵያ የምፅዓት ቀን ይመጣል (Doomsday)፣የዶክተር አብይ መንግሥት ከሌለ ኢትዮጵያ ለመፍረስ 80 በመቶ አደጋ ውስጥ ትገኛለች!!! በማለት የኒውክለር ቦንቡ ቁልፍ በአብይ እጅ እንደሆነ ይተርካል፡፡››

{3} ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የጋራ የፖለቲካ ሴራ፡- በኢሳያስ አፈወርቂ የግፍ አገዛዝ በኤርትራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ግድያ፣ እስራትና ስደት አንድ ቀን እንኮ ያልመሰከረ አደግዳጊና የፖለቲካ አጨብጫቢ ሥልጣን ናፋቂ ድርጅት ነው፡፡

ብልፅግና/ኢህአዴግ እንደ ህወሓት/ኢህአዴግ አብዬታዊ ዴሞክራሲ፣ የህገመንግስት አይነኬነትን፣ የቆንቆ የፌዴራል ሥርዓተ መንግሥት፣ የቡድን/ የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች መብት፣ የመገንጠል መብት (አንቀፅ 39) የሚደግፍ፣ የቡድን መብትና ነፃነት፣ መሬት የመንግሥት ኃብት መሆን፣ የኢትዬጵያ ህዝባዊ አብዬታዊ ዴሞክራሲያዊ ግነባር (ኢህአዴግ) የአራት ድርጅቶች ጥምረት ሲሆን ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን የተመሠረተ ግንባር ሲሆን፣በተመሳሳይ በብልፅግና ፓርቲነት ብአዴን (አዴፓ)፣ ኦህዴድ (ኦዴፓ)ና ደኢህዴን ሲመሠርቱ ህወሓት ከጨዋታ ውጭ ለመሆን ችሎል፡፡ አርበኞች ግንቦት ሰባትበ ኢዜማ በኩል የህወኃትን ቦታ ተረክቦል እንላለን፡፡ ሻብያ ወያኔና ኦነግ የነበረው ህብረት ዛሬ በሻብያ ፣ ኦነግና ግንቦት ሰባት ኢዜማ ቀጥሎል አንላለን፡፡ በኦነግ ሸኔ ‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣ 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው ፣72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን፣ እንዲሁም 23 (ሃያ ሥስት) ባንኮች መዘረፋቸውን ለግንቦት ሰባት ኢዜማና የብልፅግና/ኢህአዴግ የተደበቀ ሚስጢር አንድ ቀን ይጋለጣል እንላለን፡፡ በምድረ አሜሪካ ለአንድ ሰው ሞት ዓለም የተቃውሞ ሠልፍ ወጥቶል የእኛ አገር ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ብልፅግና/ኢህአዴግና ግንቦት ሰባት ኢዜማ የህዝቡን ስቃይ አባሳችሁ!!! ምድሪቱን ገሃነበ እሳት አደረጋችኃት!!! ሆ ብለን በእልልታ እንደተቀበልናችሁ፣ ሆ ብለን እናስወጣችኃለን!!! ቃል ለምድር ለሰማይ!!!
ታላላቅ ሰዎች መጽሃፍት በማንበብ ሰው እንሁን!!!

የኡቫል ኖኦሃ ሃራሪ ቃለመጠይቅ በማድመጥ አስተሳሰብዎን ያምጥቁ!!! የጥላቻ ንግግር በህግ ያስጠይቃል!!!

ምንጭ፡-
(1)https: youtube.com/watch?v=UTchioiHMOU/ On the Myths we need to survive
(2)https://www.youtube.com/results?search_query=yuval+noah+harari+interviewed+by+annelies+beck+on+vrt/yuval noah harari interviewed by annelies beck on vrt
(3) ነአምን ዘለቀ ሰሞኑን ልደቱ አያሌው ከጃዋር ጋር መገናኘታቸውን አስመልክቶ ለተናገረው የሰጡት ምላሽ/ by ዘ-ሐበሻ/May 19, 2020
(4) https://www.youtube.com/watch?v=E6UEc9wizBs (ESAT human right eyewitness testimony the massacre of Bedeno 1992 Ethiopia) 6 June 202

1 Comment

  1. ” የጀርመን ናዚዝም፣ የጦልያን ፋሽዝም፣ የጃፓን ዲክታተርሽፕ፣ የእኔ አገር ይበልጣል፣ የኔ ዘር ይበልጣል ታሪክ አክትሞል፡፡”

    ማክተሙን እንኳን እኔ እንጃ፣ ግን ራሱን ከጊዜው ጋራ አስተካክሎ አዋህዷል፣ ማለትም “Hauptsache man lässt sich nicht erwischen!, Wir müssen aber unsere Resourcen weltweit sicherstellen!” (እጅ ከፍንጅ ብቻ አትያዝ እንጂ በሆነልህ ሌገል ኢለጋል ዜቤ የምትፈልገውን ቁጥጥር ስር አስገባ) ነው የዘመኑ ፈሊጥ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.