///

በጀነቲክ ኢንጅነሪንግ ቴክኖሎጂ ስለተዳቀሉ ሰብሎች ጉዳይ ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል – በዘለቀ ወ.አ. ፤ ጆርጂያ ፤ አሚሪካ

3

በዘለቀ ወ.አ. ፤ ጆርጂያ ፤ አሚሪካ
(ሰኔ 2000 አ.ም. በፈለገ-ዴሞክራሲ መጽሔት ቅጽ አንድ በደራሲው በተጻፈ ጽሑፍ ላይ ተመርኩዞ የቀለበ)

መግቢያ

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ የመግብና ሌሎች ሰብሎች (genetically modified crops) በብዙ ቦታዎች ተሰራጭተው እንዳሚገኙ ግልጽ ከሆነ ስንብቷል። አነዚህን ሰብሎች መሰራት ወይም ማምረት የተጀመረው እ.አ.አ በ1970ዎቹ አካባቢ ሲሆን፣ ስብሎቹን ያለተቀናቃኝ በግል ባለቤትነት በሰሪ ድርጅቶች ለመያዝ መቻሉ (ማለት ፓተንት በማግኘት) ለመስፋፋታቸው ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል። አሰራራቸው የረቀቀ የሳይንስ እውቀትን የሚጠይቅ በመሆኑ ንብረትነታቸው በቴክኖሎጂ በዳበሩ ሃብታም አገሮች ውስጥ ባሉ ሰሪ ድርጅቶች/ኩባንያዎች እጅ እንዲሆን ግድ ብሏል። በአሁኑ ውቅት ሰብሎቹን ከሚስሩ ኩባንያዎች መካከል ቤየር-ሞንሳንቶ፤ ዱፓንት/ፓይነር ኤች ብሪድና ሲንጀንታ በዋናነት ይገኛሉ። በነዚህና በሌሎችም አነስተኛ ኩባንያዎች በርከት ያሉ የተዳቀሉ ሰብሎች እንደሚመረቱ ሲታወቅ፤ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ሩዝ፣ ድንች፣ ሶያቢንስ፣ ቲማቲም፣ ካዋላና ሙዝ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ስለሆነም የምግብ ስብልን የመለወጡ ስራ ያተኮረው በጣም አስፈላጊ በሆኑ የምግብ አይነቶች ላይ ነው ለማለት ይቻላል። እነዚህ ሰብሎች በከፊለም ቢሆን ተፈጥሮ ከሚፈቅደው ውጪ በሆነ መንገድ የተሰሩ ከመሆናቸውም በላይ በግል ንብረትነት እንዲያዙ መደረጉ ለተጠቃሚው ሕዝብም ሆነ ብዙ ለሆኑት አነስተኛ ገበሬዎች ስለሚሰጡት አገልግሎት እስካሁን የተሰበሰቡት መረጃዎች ከፍተኛ ክርክሮችን አስነስተዋል። ሰሪ የሆኑ ኩባንያዎችና አጋሮቻቸው (መንግስትንም ጭምሮ) የተልያዩ የጥቅም ነጥቦችን በማጋነን ሲያቀርቡ፣ አብዛኛው የአለም ተጠቃሚ ሕዝብና አነስተኛ የሆኑ አምራች ገበሬዎች ግን በነዚህ የተለወጡ ሰብሎች መኖር የተነሳ ለጉዳት እንደተጋለጡና ሊጋለጡም እንደሚችሉ በሰፊው ይታመናል።  በዚሀ ጽሑፍ እነዚህን ጉዳዮች በዝርዝር ለማየት የሚሞከር ሲሆን፤ ኢትዮጵያን አስመልክቶ በዚህ በኩል ሰላለው ሁነታም ባጭሩ ይዳሰሳል።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተለወጡ ሰብሎች አሰራር እንዴት ነው?

በጥቅሉ ሲገለጽ፤ እነዚህ ሰብሎች የሚሰሩት የዚህን ቴክኖሎጂ እውቀት በላበራቶርና በመሰክ ሰራ በመጠቀም ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በሰፊው በአገልገሎት ላይ ከሚውለው በይበልጥ “ተፈጥሮዊ” ከሆነው የማዳቀል ስራ የተለየ ነው። በዚህ ቴክኖሎጂ በላቦራቶሪ ውስጥ የአንድን ፍጡር ተፈላጊ የሆነ ጂን (gene ወይም የዲኤንኤ- DNA- ቁራጭ-) ለይቶ በማውጣት ወደሌላ ፍጡር ዲኤንኤ ማዛወር ይቻላል። ለዚህ ተግባር ውጤታማነት አስፈላጊ የሆነውን ጂን በቅድመያ ለይቶ ማወቅ ይገባል። ጂን የአንድን ፍጡር ፀባይ ሊወስን ወይም ሊያንፀባርቅ የሚችል የዲኤንኤ ክፍል ነው። የዕፀዋትም ሆኑ የእንሰሳት ዘሮች ሁሉ የተለያዩ ጸባያችውን የሚያንጸባርቁ የራሳቸው የሆኑ ጂኖች አሏቸው። ለምሳሌ ያህል የአበባ ቀለም፣ የዕፀዋት ፍሬ ብዛት፣ የእንሰሳት ቁመት፣ የከብት ወተት ብዛት፤ የሰው የጸጉር አይነትና የመሳሰሉት ሁሉ ከጂን አይነቶች ጋር የተሳሰሩ ፀባዮች ወይም ውጤቶች ናቸው። ሳይንቲስቶች በባዮቴክኖሎጂ ጥበብ የሰብልን ጂን በተለያዩ መንገዶች በመደባለቅ ወይም በመቀያየር የሰብልን ብዙ ፀባይና አገለግሎት ለመለወጥ እንደሚችሉ በሰፊው ተመዝግቧል። በሰብል ጂን ላይ ለውጥ በመፍጠር፣ ከዉጪ ሌላ ጂን በመጨመር ወይም ደግሞ ያለውን በመቀነስ ለውጥ ማምጣት ይቻላል። የሰብልን ምርታማንት ለማሻሻል ተብሎ ሳይንቲስቶች በሰፊው የሚጠቀሙበት የባዮቴክኖሎጂ ዘዴ ሪከምብናንት ዲኤንኤ (recombinant DNA) በመባል የታወቀ ነው። ባጭሩ በዚህ ቴክኖሎጂ ከአንድ ከተለየ ወይም ተቀራራቢ ከሆነ ፍጡር ጂን ተወስዶ በተለያየ መንገድ በማለፍ ተክል በሆነ በሌላ ፍጡር የዲኤንኤ ጥርቅም (genome) ውስጥ እንዲደባለቅ ይደረጋል። ይህ የሚደረገው ጂኑን ተቀባይ የሆነው ሰብል የሰጪውን ተፈላጊ ወይም ጠቃሚ የሆነ ፀባይ እንዲይዝ ለማስቻል ነው። ለምሳሌ ያህል በተባይ ማጥፊያ ኬሚካል ላለመበገር የሚያስችል የጀርም ጂን በሰብል ጂን ውስጥ ሲደባለቅ ሰብሉ በኬሚካሉ እንዳይጐዳ ይረዳዋል። እንዲሁም በተባዮች ላለመጠቃት የሚያስችል የጀርምን ጂን በድንች ዲኤንኤ ዉስጥ ማሰቀመጥ ድንቹን ተባይ እንዳያጠቃው ሊያደርገው ይቸላል።

ሰብሎችንና ምርቶቻቸውን በቴክኖሎጂ የመለወጡ ተግባር በዚህ መልክ በቀላሉ ይገለፅ እንጂ፣ ጠለቅ ተብሎ ሲመረመር ግን ውስብስብ የሆነ ነገር ነው። በመጀመሪያ ቴክኖሎጂው እንዲሰራ ለማድረግ ጐጂ ሊሆኑ የሚችሉ ቫይረሶች፤ ጀርሞችና ሊሎቸ ነገሮቸ ሚና ስለሚኖራቸው በሰውም ሆነ በእንሰሳት ላይ ያልተጠበቀ ጉዳት ወደፊት ሊያመጡ ይችላሉ። ሌላው ጉዳይ ደግሞ የሚፈለገው ጂን ከአንድ ፍጡር ወደ ሌላው ከተሻገረ በኋላ የመጨረሻውን ዉጤት ለማግኘት በሕዋሳት (cells) ውስጥ ብዙ ድርጊቶች መካሄድ አለባቸው። በጂኑ መዛወር ምክንያት በአዲሱ ሂዋሰ ዉሰጥ ለውጥ ስለሚኖር፣ ብዙዉን ጊዜ ሁሉም ተፈላጊ ድርጊቶች በትክክል ተካሂደው የሚፈለገዉን ውጤት ለማግኘት እርግጠኛ መሆን አይቻልም። እንዲያውም አንዳንዴ በተጠቃሚዎች ላይ በጣም ጐጂ ሊሆኑ የሚችሉ ዉጤቶች የሚገኙበት አጋጣሚዎች አሉ። ስለዚህ በአጠቃላይ በአሰራር አኳያ ብቻ እንኳን አተኩሮ ሲታይ፣ የጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የጥሩ ምርት አስተማማኝነት ብዙዎች በጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡት ጉዳይ ነው።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ጥበብ የተዳቀሉትን ሰብሎች የሰሩ ኩባንያዎችና አጋሮቻቸው ስለጥቅማቸው የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ጥቅምን ለማስገንዘብ ተብሎ ከሚቀርቡር ምክንያቶች መካከል ዋናዎቹ ቀጥሎ ባጭሩ የተመለከቱት ናቸው። በሰሪዎቹ ኩባንያዎችና በአጋሮቻቸው አመለካከት በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉት ሰብሎች ከሌሎች ካልተለወጡ ወይም በይበልጥ ተፈጥርያዊ ከሆኑ ሰብሎች ጋር ሲወዳደሩ፦

በመጠን አነስተኛና እንብዛም ጐጂ ባልሆኑ ኬሚካሎች በመጠቀም ሊመረቱ ስለሚችሉ በሰው፣ በእንሰሳትና በአካባቢ የተፈጥሮ ሃብት ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉት ጉዳት ዝቅ ያለ ነው።

ከፍተኛ የሆነ የእርሻ ምርት ፈጠን ባለ ጊዜ ለመስጠት ሰለሚችሉ የምግብን እጦት በመቀነስ ወይም በማጥፋት ርሃብን ለመግታት ወይም ጨርሶ ከአለማችን ለማስወገድ ያስችላሉ።

ለአንዳንድ በሽታዎች መንስኤ የሆነውን የአልሚ ምግብ ጉድለትን ለማስወገድ ሊያገለግሉ ይችላሉ። ለዚህም እንደምሳሌ ሆኖ ዘወትር የሚቀርበው ወርቃማው ሩዝ (golden rice) ተብሎ የሚጠራው የተዳቀለ የእህል ዘር ነው።  ይሀ የእህል ዘር በብዛት ቫይታሚን ኤ (vitamin A) የያዘ እንደሆነ ሲነገር ከምግብነቱ በላይ ዳፍንትን ለመከላከል የረዳል ተብሎ ይነገርለታል። ሆኖም ግን ይህ በተግባር ዎሎ አልተረጋገጥም።

ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን አነስተኛ በሆነ የሰው ጉልበት በማንኛውም ቦታና ጊዜ ማምረት ያስችላሉ።

ሊጠፉ ለሚችሉ የሰብል አይነቾች ተከላካይ ወይም ቅያሬ በመሆን እንዳይጠፉ ለማድረግ ያስችላሉ።

ሰለተዳቀሉት ሰብሎቹ ጥቅም እነዚህ እንደ ምክኒያቶቸ የሚቀርቡ ቢሆንም ሰለተግባራዊነታቸው ወይም እውነተኝነታቸው እሰካሁን አሰተማማኝ የሆነ ሁኒታ አልታየም።  እንዲያውም ለተሻለ አማራጭ ሊደረግ የሚችለዎን ጥረት ሊቀንሰና ሊጎዳም ቸሏል (ለተጨማሪ ከዚህ በታቸ ያለውን ይመልከቱ)።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ስለተዳቀሉት ሰብሎች ጐጂነትስ የሚቀርቡት ምክኒያቶች ምን የመስሉ ናቸው?

አብዛኛው ተጠቃሚ ሕዝብና አነስተኛ አምራች ገበሬዎች ስለእነዚህ ሰብሎች ጐጂነት ወይም ጥቅመቢስነት በርከት ያሉ የክርክር ነጥቦችን ሲያቀርቡ ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች የሰፈሩት ናቸው። በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተቀየሩት የስብል አይነቶች፦

ረዘም ላለ ጊዜ በምግብነት ሲወሰዱ በጤንነት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህ አመለካከት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው። ቀጥሎ ባጭሩ የተጠቀሱት የጤንነት ችግሮች ለዚህ በምሳሌነት የሚቀርቡ ናቸው።

የፀረ ሕዋሳት መድሃኒቶች አጠቃቀም ልቅ እንዲሆን በማድረግ አገልግሎታህቸውን አዳክሞ አንዳንድ በሽታዎችን ላለማዳንና ለጤንነት ችግር ማጋለጥ።

የምግቦችን የአልሚነት አገልግሎት ወይም ጸባይ (nutritional values) በመቀነስ ለበሽታ ማጋለጥ።

መርዝነት ያላቸውን ወይም ጐጂ የሆኑ ኬሚካሎችንና ጀርሞችን ወደ ተጠቃሚዎች ማስተላለፍና በይበልጥ ማሰራጨት፤ ብሎም ለበሽታ መጋለጥ።

ያልተጠበቁ ወይም አዲሰ የሆኑ ጎጂ ካሚካሎችን ወይም መርዞችን በሰብሎቹ ውሰጥ በመፍጠር   ተጠቃሚን ለተለያዩ በሰታዎቸ ወይም ጉዳቶቸ መዳረግ። በምሳሊነት አለርጂ (የሰውነት መቆጣት)፤ ካንስር፤ የጽንሰ ቸግር ሊጠቀሱ የሚቸሉ ናቸው።

ከነዚህ ሰብሎች ጋር አብረው ለሚያገለግሉ የተባይና የአረም አጥፊ ለሆኑ ኬሚካሎች ጉዳት መጋለጥ። በምሳለነት ካንሰር ሊያመጣ የሚትለዉ ራዉድ አፕ (Round-up) ሊጠቀሰ ይችላል።

ብዙዎቹ ከላይ የተጠቀሱት የጤና ችግሮች ሊከሰቱ የቻሉት ወይም የሚችሉት አስፈላጊ የሆኑት

ጥንቃቄዎች ሳይወሰዱ በግዲለሰነት ሰብሎቹ ከጥቅም አይ እንዲውሉ በመደረጉ ወይም ሲደለግ ነው።

በእርሻ መስክ አካባቢ የሚገኙን ከፍተኛ ጠቀሚታ ያላቸዉን ያልተዳቀሉ ሰብሎችን በመበከል የነዚህን ሰብሎች ጥራት፣ አገልግሎትና የሽያጭ ዋጋ እንዲቀነሱ ያደርጋሉ። በአሁኑ ወቅት ያልተበከሉ ሰብሎች (organic products) ተፈላጊነት በጣም እየጨመረ በመምጣቱ የዚህ ዓይነቱ የብክለት ችግር በይበልጥ ግልጽ ዕየሆነ መጥቷል፤ በተለይም በአነስተኛ አምራች ገበርዎች ላይ ።

ለእርሻ አግልግሎት የሚውሉ ለሰዉ ጎጂ የሆኑ ኬሚካሎች አጠቃቀም እንዲቀንስ ከማድረግ ይልቅ ብዙውን ጊዜ በይበልጥ የመጠቀምን ሁኒታ ስለሚበረታቱ ከዚህ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ጉዳቶችን ያስከትላሉ። እላይ ከተጠቀሰው የጤንነት ችግር ሌላ ኬሚካሎቹ ያለአግባብ በስራ ላይ ሲውሉ በአካባቢ የተፈጥሮ ሃብት ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት በሰፊው የተመዘገበ ነው። አሰፈላጊ ክሆነ ኬሚካሎችን ከሰሪዎቹ ኩባንያዎች ለመዛት የሚደረገው ከፍተኛ ወጪ ሌላው ከዚህ ጋር የተያያዘ የኢኮኖሚ ችግር ነው።

በይበልጥ ለሰፋፊ እርሻዎችና ለትላልቅ እንዱስትሪዎች ስራ አመቺና አትራፊ በመሆናቸው በብዙ ቦታዎች ለሚገኙ በሚሊዎን ለሚቆጠሩ ገበሬዎችና ለተጠቃሚው ሕዝብ ከፍ ያለ አገልግሎት ሰጪ የሆነውን የአነስተኛ ገበሬዎች የእርሻ አገልግሎት ያቆረቁዛሉ። በዚህም የተነሳ በአለም ሁሪያ ብዙ አነሰተኛ ገበሬዎች ከስራቸው ተፈናቅለዋል፤ እየተፈናቀሉም ነው። ተጠቃሚዉም ሕዝብ ተፈላጊ የሆኑ የስብል ምርት እጥረት የተነሳ ችግሩ ተካፋይ ሊሆን ቸሎዋል።  ለምግብ እጥረትና ለርሃብ ይህ አሰተዋጻኦ እንዳለው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።

በባለቤትነት የተያዙት (በፓተንት መልክ) ጥቂት በሆኑ የበለጸጉ አገሮች ኩባንያዎችና አጋሮቻቸው በመሆኑ የትኛውም ገበሬ እንደፈለገው ሊጠቀምባቸው አይችልም። ስለሆነም ባለቤትነት የሌላቸው ገበሬዎች እነዚህን ሰብሎች ለመጠቀም ከፈለጉ ከሰሪዎቹ ኩባንያዎች በየጊዜው መግዛት ወይም “ግብር” መክፈል አለባቸው ማለት ነው። ገብሪዎች የተዳቀሉተን ዘሮች አሰቀምጠው ወደፊት እንዲጠቀሙ አይፈቀድላችውም። ከሰብሎቹ ጋር የተያያዙ ሌሎች አገልግሎቶችንም አብሮ መግዛት የግድ ይሆናል። ለብዙ ገበሬዎች ይህንን ለማማላት ቀላል አይሆንም። ይህንን ችግር ለማቃለል ተብሎ፤ ገበሬዎቹ የከፈሉባችውን ሰብሎችና ሊሎች ነገሮችን ከተጠቀሙ በኋላ ዕዳቸውን ለመሸፈን ከሚያገኙት ትርፍ በየወቅቱ የተወሰነ ክፍያ እንዲያደርጉ የተለመደ የአስራር ዘዲ ሆኗል። ይህ ሁኔታ በተለይም አነስተኛ የሆኑ ገበሬዎችን የኩባንያዎቹና አጋሮቻቸው ጥገኛ እንዲሆኑ ገፋፍቷቸዋል። ድርጊቱ ቀሰ በቀሰ እነዚህን ገበሬዎች የኢኮኖሚም ሆነ የፓለቲካ ነፃነት እያሳጣቸው መጥቷል። ብዙዎች ታዛቢዎች እንደሚያምኑበት ይህ ሁኔታ በይበልጥ ሊከሰት የሚችለው የመካን እህል ዘር (terminator seed) በጥቅም እንዲውል ሲደረግ ነው።

ረዘም ላለ ጊዜ ለእርሻ ምርት አገልግሎት ከዋሉ ነባርና በይበልጥ ተቀባይነት ያላቸውን የእርሻ አሰራርና ልምዶችን እንደዚሁም የአካባቢን የተፈጥሮ ነባራዊ ሁኔታ በማናጋት ዘላቂነት ያለው (sustainable) የእርሻ ሰራና ምርት እንዲዳከም ወይም እንዲጠፋ ያደርጋሉ። ይኸ ደግሞ በብዙ አገሮች ዉስጥ ያሉትን የተለያዩ የእርሻ ሰራ አማራጮች ቀስ በቀስ በማመንመን ምርታማነትን ያዳክማል። በሊላ መልክ እላይ እንደተገለጸው በመጨረሻ ገበሬችም ሆኑ ተጠቃሚው ሀዝብ ለምግብ እጥራትና ርሃብ ያጋለጣሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ራዕይ ነበረው፣ ተቀጥሎበታልም።

ሁሉም ባይሆኑ አንዳንዶጭቹ የተዳከሉ ሰብሎት በማንኛውም የአሰራር መንግድ ቢሆንም ምርትን ከመጨመር ይልቅ እንዲቀንሰ ያደርጋሉ። በዚህ በኩል ጂኢ በቆሎ እንደምሳሊ የሚቀርብ ነው።  ምርትን ያልቀነሱትም፤ ሱጨምሩ የሚያመለክት በእርግጠኝነት የሚቀርብ መረጃ አስከአሁን የለም።

የተባይና የአረም ማጥፊያ የሆኑ ኬሚካሎች ካላስፈላጊ በጥቅም ላይ በብዛት እንዲውሉ ትክኖሎጂው ሰለሚገፋፉ በአረምና በተባይ መብዛት ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ከማቃለል ይልቅ እንዲያዉም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲባባሱ ያደርጋሉ።

በሚገኙበት አካባቢ በሌሎች ህይወት ባላቸዉ ፍጥረቶች ላይ የበላይነት ተፅዕኖ በማድረግ ለአካባቢ የእንሰሳትና የእፅዋት ሀብት መጐዳት ወይም ጨርሶ መጥፋት አስተዋፅዖ ያበረክታሉ። ይህ በተፈጥሮ ሃብት ላይ ትኩረት ለሚሰጡና ለሚመኩ አገሮች፤ ህብረተሰቦች፤ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጣም ጐጂ ይሆናል።

በከፊልም ቢሆን ተፈጥሮ ከሚፈቅደው ውጭ በሆነ መንገድ ምርቶቹ የሚሰሩ በመሆናቸው በዚህ በኩል ለተወሰደው ውይም ለሚውሰደዉ እርምጃ ትክክለኛለት ብብዙዎቸ ዘንድ የሞራል ጥያቄ አስከትሏል።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ስለተዳቀሉ ሰብሎቹ ሌላው በሰፊው ያልተነገረ ምስጢራዊ አገግሎት

ሰለእነዚህ ሰብሎች በይፋ ከሚነገሩት አገልግሎታቸውና ጉዳታቸው በተጨማሪ ከነዚህ ጉዳዮቸ ጋር የተዛመዱ ሌሎች ድብቅ አገልግሎት ለሰሪዎቻቸውና ለአጋሮቻቸው እንደሚኖራቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች በየጊዚዉ ብቅ እያሉ ነው። በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች የሚያመለክቱት የትላልቅ ኩባንያዎች ወይን ኮርፖሬሽን ዋነኛ ጥቅም አስከባሪ የሆነው የአሜሪካ መንግስት አብዛኛውን የአለምን (በተለይም የታዳጊ አገሮችን) የምግብ ምርት በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ በተሰሩ/በተቀየሩ ሰብሎች አማካኝነት በግሎባላይዜሽን ግንኙንት አማካኝነት ለመቆጣጠር በመቻል ዋነኛ የአለማችን ሃይል ሆኖ የመገኘት ፍላጎር እንዳለው ነው። በአለም የምግብ ምርት አይነትና መጠን ወሳኝ ሚና በመጫወት የሕዝብን ብዛት መቆጣጠርን ጨምሮ የአንድን አገር ሕልውና ለመወሰን ያስችላል ተብሎ ይገመታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታወቅ ያለበት፣ ይህንን የኩባንያዎና (ኮርፖሬሽን) የአሜሪካ መንግስር ስውር እቅድ ሁሉም የአግሩ ዜጋ የተገነዘበው ጉዳይ ሳይሆን በይበልጥ የሚያንጸባርቀው የጥቂት ባለስልጣኖችንና የሃብታሞችን ፍላጐት መሆኑን ነው። ለዚህ ዕቅድ ነባራዊነት ምን አይነት መረጃዎች አሉ?

የዚህ ድርጊት ታሪክ የሚጀምረው ሮክፈይለር (Rockefeller Foundation) ተብሎ በሚጠራው በቤተሰብ በተያዘ የግል ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በኒውዮርክ ከተማ እ.አ.አ. በ1913 ዓ.ም. በጆን ሮክፈይለርና በፍሬደሪክ ጌትስ የተመሰረተ ሲሆን ለዚሁም መነሻ የሆነው ከእስታንዳርድ ኦይል የቤንዚን ንግድ ስራ ሊገኝ የቻለው የገንዘብ ሃብት ነው። ይህ ድርጅት የሰውን ልጅ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ማሻሻልን እንደዋና ዓላማው አድርጐ ቢገልፅም በተዘዋዋሪ በተለያዩ መንገዶች የሚያደርገው የአለምን ሕዝብ መጠን (በተለይም በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለውን) ለመቆጣጠር የሚያስችልን መንገድ መፈለግን ነው። ለዚህ አላማ አንድ ዋንኛ ዘዴ ተደርጎ የተወሰደው በጀነቲክ ኢንጅነሪንግ ጥበብ የተዳቀሉ ሰብሎች ተሰርተው እንዲሰራጩ በማድረግ የአሜሪካ መንግስት ወይም ከበርተዎች የአለምን ሕዝብ ተቆጣጥሮ ገናናነቱንና ጥቅሙን እንዲረጋገጥ ማስቻል ነው። ቀጥሎ ባጭሩ የተዘረዘሩት ክሰተቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለዚህ እቅድ ሕያውነት አመልካችቺ ናቸው።

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ቀደም ብሎ ሮክፈይለር ድርጅት የአለምን ሕዝብ ብዛት ለመቀነስና “ምርጥ” የሆነ የሰው ዘር ለመፍጠር ተብሎ ለሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር ከፍተኛ ድጋፍ ሰጭ እንደነበረ ተመዝግቧል። ይህ ድርጊት የሰውን ዘር “ጥራት” ለማሻሻል በሚል አላማ ናዚ ያካሂደው የነበረውን ዘረኛ ፕሮግራም የመሰለ ነበር።

የናዚው ዘረኛ ፕሮግራም ከሁለተኛ የአለም ጦርነት በኋላ ሲጋለጥ፣ የሕዝብን ተቃውሞ በመፍራት ሮክፈይለር ድርጅት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ሕዝብ ቅነሳ ጉዳይ ላይ በማተኮር መስራትን መረጠ። ለዚህም ይበጃል በማለት የጀነቲክ ኢንጅነሪንግ ጥበበን ተጠቅሞ ሰብሎች በሰሪዎቻቸውና በአጋሮቻቸው ቁጥጥር ስር የሚዉሉበትን መንገድ ለመሻት ከሰላሳ አመታት ገደማ በፊት ጀምሮ ለዚህ ቴክኖሎጂ መዳብርና መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል፤ እያደረገም ነው። ይህንን ዓላማ በተግባር ለማዋል ድርጅቱ በይበልጥ ያተኮረው በተፈጥሮ ሃብትና በሕዝብ ብዛት ባለፀጋ በሆኑ ታዳጊ አገሮች ላይ ነው። ስለሆነም ቴክኖሎጂውም ሆነ የቴክኖሎጂው ውጤቶች በነዚህ አገሮች ውስጥ ገብተው በተግባር የሚውሉበትን ሁኔታ ድርጅቱ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ነው።

በሮክፈይለር ድርጅት አበረታችነት እ.አ.አ. በ1972 አ.ም. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን የድርጅቱን የቀድሞ ባለስልጣን ጆን ሮክፈይለር ሶስተኛን በመሾም የአሜሪካ የሕዝብ ብዛት ጉዳይ ኮሚሽን አቋቋሙ። በዚህ ድርጅት አማካኝነት ዶክተር ሄኔሪ ኪሲንጀር እ.አ.እ በ1974 አ.ም. የአገርን ደህንነትና ሕልውና አስመልክቶ የተፃፈውን ሰነድ (National Security Study Memorandum 200, NSSM 200) ለፕሬዘዳንት ኒክሰን በማቅረብ በተፈጥሮ ሃብት ባለፀጋ በሆኑ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለው የሕዝብ ብዛት የአሜሪካ ተቀዳሚ ስትራቴጃዊ ጉዳይ ሆኖ እንዲወሰድ አድርገዋል። በዚህ መሰረት አስራ ሶስት አገሮች በዋናነት ሲመዘገቡ ኢትዮጵያ ከነዚህ መካከል አንዷ ነች። ኪሲንጀር የአሜሪካ የአገር ደህንነትና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣን በነበሩበት ወቅት የምግብ ሽያጭና ዕርዳታ ስምምነቶች የመንግስታቸው አንድ ዋነኛ የጥቅም ማስከበሪያና የጠላት ማጥቂያ መንገድ ሆኖ እንዲሰራበት አድርገዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታወቅ ያለበት ኪሲንጀር የአሜሪካ መንግስት ባላስልጣን ከመሆናቸው በፊት በሮክፈይለር ድርጅት ሲሰለጥኑና ሲሰሩ እንደነበሩ ነው። ስለዚህ በNSSM 200 ሰነድ አማካኝነት የአሜሪካ መንግስት የሚከተለው የዉጭ ፓሊሲ ኪስንጀር ቢያንስ በከፊል ከሮክፈይለር ድርጅት የቀሰሙት ሃሳብ ነው ለማለት ይቻላል።

በኪሲንጀር በኩል ለመንግስት በቀረበው NSSM 200 ሰነድ ውስጥ የተመለከተውን ፓሊሲ መነሻ በማድረግ በታዳጊ አገሮች ውስጥ የሕዝብ ብዛት ከሚመረተው የምግብ መጠን በላይ ነው በሚል ሰበብ ሮክፈይለር ድርጅት ለችግሩ መፍትሔ ይሆናል በማለት ቀድሞ ያቀደውንና የጀመረውን ሰብልን የማዳቀል ስራ በሰፊው እንዲቀጥል አብቅቶታል። ይህንን እቅድ ከግብ ለማድረስ እንዲበጅ እንደሞነሳንቶ ካሉ የእርሻ ምርምር እንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት አጠናክራል።

በሮክፈይለር ድርጅት የተጠነሰሰውን የሕዝብ ብዛት ቅነሳና በጀነቲክ ኢንጅነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎች የመስፋፋት ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሜሪካ መንግስት ይበልጥ ተቀባይነት ስላገኘ እ.አ.አ በ1971 ዓ.ም. ይህ ድርጅት ከአለም ባንክ፣ ከፎርድ ድርጅትና (Ford Foundation)፣ ከአለም የእርሻ ምርምር ኮሚሽን ጋር በመተባበር በዚህ መስክ አንድ የምርምር ማዕከል (CGIAR) እንዲቋቋም አድርጓል። ይህ ማዕከል በተለያዩ አገሮች ቅርንጫፎች ሲኖሩት ቀድሞ የሮክፈይለርና ተባባሪዎቹ በነደፉት ዕቅድ መሰረት ስራዉን በይበልጥ የሚያካሂደው በታዳአጊ አገሮች ችግር ላይ በማተኮር ሆኗል። ስለሆነም በዚህ ማዕከል ከሚከናወኑት ስራወች መካከል አንዱና ዋንኛው በጀኔቲክ ኢንጅኒሪንግ ጥበብ የተዳቀሉ ሰብሎችን በነዚህ አገሮች ውስጥ ማሰራጨት ነው። በአሁኑ ወቅት ይህ ማዕከል በአለም ባንክ ስር ሆኖ እንዲሰራ ሲወሰን የተጠቀሰውን አላማ ለማሳክት የአለም ባንክ ለታዳጊ አገሮች “እርዳታ” ወይም ብድር ሲሰጥ የአሜሪካንን የውጪ ፓሊሲ ለማስከበር “ተረጂዎቹ” ወይም ተበዳሪዎቹ የሕዝባቸውን ቁጥር ለመቀነስ ወይም ለመቆጣጠር መስማማታቸውን ይጠይቃል። በተጨማሪም ማዕከሉ እነደ ሞንሳንቶ ከመሳሰሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር ከብዙ ታዳጊ አገሮች በስርቆት የተሰበሰቡ የሰብል ዝርያዎችን በባለቤትነት በመመዝገብ በባዮቴክኖሎጂ ሙያ አዳቅሎ አዳዲስ ሰብሎችን በመፍጠር በየአገሩ ያሰራጫል። የዚህ አይነቱ ስራ በየአገሩ እንዲያካሂድ ወይም እንዲስፋፋ በተለያየ መንገድ ድርጅቱ የበላይ ተቆጣጣሪ በመሆን ጥረት ያደርጋል።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ተክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎች “ሕጋዊ” በሆነ መንገድ በሰሪዎቻቸውና በአጋሮቻቸው በግል ባለቤትነት እንዲያዙ ለማድረግ ሮክፈይለር ድርጅት የተቻለውን ያህል የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ ድጋፍ ይሰጣል። ለዚህ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ልዪ መስሪያ ቤት (ISAAA) እንዲቋቋም አድርጓል ። ይህ በመሆኑ ኩባንያዎቹም ሆኑ አጋሮቻቸው በተለያዩ ሰብሎች የባለቤትነት መብት በቀላሉ እንዲያገኙ ተደርጓል፤ እየተደረገም ነው። በጥቅም የመተሳሰር ጉዳይ በመሆኑ ማዕከሉም በበኩሉ ከሮክፍይለር ድርጅት፣ ከሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና እንደ ሞንሳንቶ በመሳሰኡ የእርሻ ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ ይሰጠዋል።

የሮክፈይለር ድርጅት አላማና ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሜሪካ መንግስት አስተዳደር ተቀባይነት በማግኘቱ እ.እ.እ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም ፕሬዘዳንቶች በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ጥበብ ሰብልን የማዳቀልና የማሰራጨት ጥረት ተቀዳሚ የአገራቸው ስትራቴጂያዊ ጉዳይ አድርገው ወስደውታል። እነዚህን ሰብሎች አስመልክቶ ለተቋቋመው ማዕከልም ሁሉም ፕሬዚዳንቶች ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህም በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰብሎቹ ወደ ሚፈልጓቸው አገሮች እንዲሰራጩ ለማድረግ ሙከራና የድጋፍ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። እነዚህን ሁኔታዎች የሚያመለክቱት የኢንዱስትሪዎችና የመንግስት ስራዎች ምን ያህል የተሳሰሩ መሆናቸውን ነው።

የምግብ ሰብሎች ምርትንና የሕዝብን ብዛት ለመቆጠጠር በተለያዩ ድርጅቶችና በአሜሪካ መንግስት ለሚደረገው ጥረት ዋና መሳሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማሰብ በቅርቡ የመንግስትና የሌሎች ድርጅቶች ዕርዳት ተጨምሮበት በሞንሳንቶ የመካን ሰብል ዘር (terminator seed) ተሰርቷል። ይህ ሰብል በባለቤትነት የተመዘገበው በሞንሳቶና በአሜሪካ መንግስት የግብርና መስሪያ ቤት ነው። ይህን ሰብል የመፍጠሩ ዓላማ ያተኮረው በተለይ በታዳጊ አገሮች ገበርሬዎች ላይ ሲሆን፣ በአገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጎ የተሰራው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው። ስለሆነም ከዚህ ሰብል የሚመረቱ ዘሮችን በተቀጣይ የእርሻ ወቅት ለመጠቀም አይቻልም። ስለዚህ ገበሬዎች ዘሩን (ሌሎች አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ጋር) ከሰሪው ኩባንያ በየጊዜው መግዛት አለባቸው ማለት ነው። በዚህ መልክ ቀድሞ እንደታቀደው ይህ የተዳቀለ ሰብል በሰፊው አገልግሎት ላይ ዕንዲውል ከተደረገ ገበሬዎችንም ሆነ ተጠቃሚውን ሕዝብ በቀላሉ የኩባንያዎችና የተባባሪዎቻቸው ጥገኛ ወይም ተገዥ ሊያደርጋቸው ይችላል። በዚህ አማካኝነት አሜሪካ ታዳጊ አገሮችን እንደምትፈልገው ለመቆጣጠር ይቻላታል የሚል አመለካከት አለ። በጋትና (GATT) በአለም የንግድ ድርጅት (WTO) በኩል አሜሪካ በታዳጊ አገሮች ላይ የምታደርገው አድሏዊ ተፅዕኖ ለዚህ ሁኔታ መሳካት አስተዋፅዖ ሰጪ ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ የጋት፣ የአለም የንግድ ድርጅትና የመሳሰሉት ሰምምነቶች በይበልጥ የሚጠቅሙት የበለፀጉትን አገሮች (በተለይም አሚረካን) ስለሆነ፤ በተዳቀሉ ሰብሎች አማካኝነት በታዳጊ አገሮች ላይ የሚከተለው መዘዝ በቀላሉ የሚገመት አይደለም።

ሮክፈይለር ድርጅት በሕዝብ ብዛት ላይ ለማተኮሩ ሌላው መረጃ በዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት በኩል የታዳጊ አገሮችን ሕዝብ ለመቀነስ በየወቅቱ ያደረገው እንቅስቃሴ ነው። በዚህ በኩል ካደረጋቸው ነገሮች መካከል ከዓለም ባንክ፣ ከሕዝብ ቁጥጥር ካውንስልና ከፎርድ ድርጅት ጋር በመተባበር በዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት በኩል የሚካሄድ የሕዝብ ቅነሳ ፕሮግራም እንዲኖር አድርጓል። በዚህ መሰረት ሮክፈይለር ድርጅት በተዳቀሉ ሰብሎች ላይ የሚያካሂደው ስራ ከሕዝብ ቁጥር ቅነሳ ጋር የተያያዘ መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።

በቅርቡ ደግሞ የሮክፈይለርና የቢል ጌትስ ድርጅቶች (Gates Foundation) በመተባበር የአፍሪካ አዲሱ “አረንጓዴ አብዮት” ሕብረት (AGAR) የተሰኘ በኮፊ አናን ሊቀመንበርነት የሚመራ አዲስ ድርጅት በማማቋቋም በዚህ አማካኘለት በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎች (መካን ዘርን ጨምሮ) በአፍሪካ አገሮች ውስጥ በስፋት እንዲሰራጩ ተጨማሪ ግፊት እየተደረገ ነው። ከዚህም ሌላ እነዚህ ድርጅቶች ከኖርዌ መንግስት፣ ሞነሳንቶ፣ ሲንጁንታ፣ ዱፓንት-ፓይነር፣ ዓለም ባንክና ከመሳሰሉት ጋር በመተባበር የአለማችንን የዕፅዋት ዘሮች በመሰብሰብ ኖርዌ ውስጥ በሚገኝ አንድ ደሴት (ስቫልባርድ) ውሰጥ ባለ ቦታ በሚሰጥር እያከማቹ አንዳሉ ተመዝግባል። በዚህ ቦታ ይህ ጽሁፍ እሰከተጻፈ ድረስ ወደ 270 ሽህ የሚጠጉ ዘሮቸ ሲከማቹ፤ በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮ ተኩል በላይ የሆኑ ዘሮቸ እንደሚስበሰቡ ተገምታል። አዋቂዎች ኢንደሚያስቡት ይህ ሁኒታ የሚጠቁመው በጀኔቲክ ኢንጂነሪንግ ጥበብ የተሰሩት ሰብሎች (በተለይም መካን ዘር) በዓለማችን በየቦታው የሚገኙትን ንፁህ ውይም ተፈጥራዊ የሆኑ የእጽዋት ዘሮቸን ቀሰ በቀስ ሊያጠፉ እንደሚችሉ ፍርሃቻ እንዳለና ለጥንቃቄ ያህል ከአሁኑ ተጠባባቂ ዘሮችን ማስቀመጡ አስፈላጊ እንደሆነ ነው። የተገለፀው ሁኔታ ከተከሰተ ዘሮቹን ያስቀመጡት ድርጅቶች ለሌሎች ፈላጊዎች አዳይ በመሆን ከሚፈጠረው ችግር ዋነኛ ተጠቃሚ ይሆናሉ ማለት ነው። በዚህ መልክ ሰብሳቢዎቹ በብዙ መንገዶች ምግብንም ሆነ ሌሎች የተያያዙ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላሉ። ለዚህ ችግር በይበልጥ ሊጋለጡ የሚችሉት እንደሚጠበቀው ታዳጊ አገሮች ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ገደል (ሥርጉተ ሥላሴ)

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉት ሰብሎች በተለይ በታዳጊ አገሮች ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉት ተጨማሪ ችግር አለ?

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ዘዲ የተሰሩት ሰብሎች ሊሰጡ የሚችሉት ጥቅምም ሆነ የሚያስከትሉት ጉዳት አጠቃላይ በሆነ አቀራረብ እላይ ተዘርዝሯል። እነዚህ ሰሎች በይበልጥ እንዲሰራባቸው ወይም እንዲሰራጩ ጥረት የሚደረገው በታዳጊ አገሮች ውስጥ፤ በተለይም በአፍሪቃ እንደሆነም ተጠቅሷል። ከላይ የተመለከቱት ችግሮች የብዙ ቦታዎችን ሁኔታዎች በአጠቃላይ የሚገልፁ ሲሆኑ ሰብሎቹ በታዳጊ አገሮች ውስጥ ተጨማሪ ጉዳት የሚኖራቸው መሆኑም የታመነበት ጉዳይ ነው። ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ተደምረው በእነዚህ አገሮች ውስጥ የስብሎቹ መኖር ወይም መሰራጨት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ጥርጥር የለውም።

በብዙ ታዳጊ አገሮች ላይ በተዳቀሉ ሰብል ሰሪዎችና ደጋፊዎቻቸው በሚደረገው ተፅዕኖና በአንሰራፋውም ሙስና የተነሳ ነዋሪ ወይም የአገር ገበሬዎች እነዚህን ሰብሎች ገዘተው እንዲጠቀሙ ከፍተኛ ግፊት ይደረግባቸዋል። ብዙ ገበሬዎች ደሃ በመሆናቸው ሰብሎቹን (ከሌሎች አስፈላጊ ከሆኑ ሸቀጦች ጋር) ገዝተው ለመጠቀም ቀላል አይሆንላቸውም። ሰብሎቹ የሚገዙበት ዋጋም ሆነ ለአጠቃቀማቸው የሚደረገው ወጪ ከብዙዎች አነስተና ገበሬዎች አቅም በላይ ነው ለማለት ይቻላል። ስለሆነም የቴክኖሎጂውን ውጠት በተፅዕኖም ሆነ በምርጫ ደፍረው የሚጠቀሙ በርከት ያሉ ገበሬዎች ጥቅም ስላላገኙበት እዳቸውን ለመክፈል ሲሉ ንብረታቸውን አጥተው ስራቸውን በመተው በቦዘኔነት ከተማዎቸን ሲያጣብቡ በብዙ ቦታዎች በይፋ የሚታይ ጉዳይ ሆናል። ስለዚህ የዚህ ቴክኖሎጂ በታዳጊ አገሮች ውስጥ መስፋፋት ለብዙ ገበሬዎች ከቆዩበትና ዋስታና ከሆናቸው የእርሻ ሞያ አግላይ ሆኗል፤ ይሆናልም። በዚህም የተነሳ ተጠቃሚው ሕዝብ አብሮ የችግሩ ተካፋይ ሊሆን ችሏል።

ባላቸው የመሬት አቀማመጥ ምክንያት ብዙ ታዳጊ አገሮች በየቦታው ተለዋዋጭ የሆነ የአየር ፀባይና የተለያየ የአፈር አይነት አላቸው። ስለሆነም ለሁሉም ሁኔታውች የሚስማሙ ሰው ሰራሽ ሰብሎችን ለማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። ይህም በመሆኑ የተዳቀሉ ሰብሎች በነዚህ አገሮች ውስጥ በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ ሲደረግ ከጥቅም ይልቅ ብዙውን ጊዜ ከሚጠበቀው ውጤት ውጪ የሆኑ የተለያዩ ችግሮችን ይፈጥራሉ። ይህ በመሆኑ ንብረትንና ጊዜን ካማባከን አልፎ ተጨማሪ ችግርን መጋበዝ ይሆናል።

የጀነቲክ ኢንጅነሪንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተነሳ ችግር ሲፈጠር ወይም ቢፈጠር ታዳጊ አገሮች አስፈላጊዉን ዕርማት ለማድረግ አቅም ያንሳቸዋል። ስለሆነም ከሊሎች አገሮች ጋር ሲሰተያይ የበለጠ ችግር ያጋጥማቸዋል። “የአረጓዴው አብዮት” ልምድ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ለዚህ ሁነታ ትምህርት ሰጪ ነው። የአሁኑ “የጂን አብዮት” ችግር ደግሞ የባሰ ቢሆን ነው እንጂ ያነሰ ሊሆን አይችልም። በአየር ፀባያቸውና በአፈር ይዞታቸው ምክንያት አብዛኛዎቹ አገሮች በርከት ላሉ ለተለያዩ የንፁህ ሰብሎችና የሌሎች ፍጥረቶች መኖሪያ በመሆናቸው ችግር ቢከሰት የእነዚህ ዉድ የተፈጥሮ ሃብቶች መጥፋት ወይም መለወጥ ከፍትኛ ዕድል ይኖረዋል። አንዳንድ የሰብል ፀባዮችም (ማለት ጂን) ከተዳቀሉ ወዳልተዳቀሉ ዘሮች የመተላለፍ አጋጣሚም በነዚህ ቦታዎች ከፍ ያለ ነው። በዚህ ሁኔታ ያልተዳቀሉ ንፁህ ሰብሎች በሌሎቹ ይበከላሉ ማለት ዪሆናል። ይህ ጉዳይ ራሱን የቻለ የማይናቅ የተፈጥሮና የኢኮኖሚ ችግር ቀስ በቀስ ሊያመጣ የሚችል ነው።

ከዳበሩ አገሮች ገበሬዎች ጋር ሲነጻጸር፤ በመንገስታችው ድጐማ ሰለማይደረግላቸው ስራቸውም ሆነ የስራቸው ዉጤት እምብዛም ብቃት አይኖረዉም። እንዲያዉም በአንድ ታዳጊ አገር ዉስጥ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች እነዚሁ ገበረውች ናቸው። ስለሆነም ምርታቸውን በአለም ገበያ ተወዳድረው ለመሸጥ ችግር ይኖራቸዋል። በዚህ የተነሳ ቀስ በቀስ ምርታቸው እየቀነሰ ሲመጣ እላይ እንደተጠቀሰው ስራቸውን ጭራስኑ እስከመተው ይገደዳሉ።

ቀደም ብሎ እንደተገለፀዉና ብዙዎችም እንደሚያምኑበት በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ የተዳቀሉ ሰብሎች ርሃብን ከማሰወገድ ይልቅ ሊያባብሱ የሚችሉ ናቸው። “አረንጓዴው አብዮት” በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያሳየው ውጤት ለዚህ በቂ ምስክር ነው። በ”አረንጓዴው አብዮት” መካሄድ ምክንያት ብዙ በሆኑ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ምርት እንዲቀነስ፤ የተፈጥሮ ሃብት እንዲቀጭጭና ብዙ ገበሬዎች ባለዕዳና ይበልጥ ድሃ እንዲሆኑ ተገድደዋል። ከነዚህ “ዘመናዊ” እርሻ ዘዴዎች አገልግሎት ውጪ፣ በየጊዜው በታዳጊ አገሮች ውስጥ ለሚከሰተው ርሃብ ዋነኛ ምክንያት ነው በማለው ብዙዎች የተቀበሉት የምግብ እህል አሰረጫጨት ጉድለትን ነው። ለዚህ ዋና ማረጋገጫው፣ በቂ የሆነ የምግብ ምርት በነበረባቸው ቦታዎች ውይም ወቅቶች በነዚህ አገሮች ውስጥ ርሃብ ተደጋግሞ መከስቱ ነው። ይህ ሊሆን የቻለው አስፈላጊው ምግብ በወቅቱ ለርሃብተኛው ለመድረስ ባለመቻሉ ነው። ስለዚህ የርሃቡ መፍትሔ ጥቅሙ ገና ያልተረጋገጠውን ቴክኖሎጂ በጭፍን መቀበል ሳይሆን የተመረተውን ወይም ያለውን ምግብ በትክክል ለፈላጊዎች ማዳረስን ይካትታል።

በሮክፈይለር ድርጅት ተፀንሶ በኮርፖሬሽንና በአጋሮች ድርጅቶቸ በተግባር ላይ እንዲዉል በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ በተቀየሩ ሰብሎች አማካኝነት የሚደረገው ጐጂ ጥረት በይበልጥ ያተኮረው በታዳጊ አገሮች ላይ ነው። ስለዚህ ይህ ሰብልን ለማዳቀል ተብሎ የሚሰራበት የሳይንሰ ጥበብ በዚህ በኩል በጥቅሉ ሲታይ ለእነዚህ አገሮች ይበለጥ ጉዳት አምጭ እንጂ ጥቅም ሰጪ አለመሆኑ ግልፅ ነው።

 

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎች በእርሻ ምርት ላይ የዋሉባቸው ዋና ዋና ቦታዎችና የሚደረገው ተቃውሞ

በአጠቃላይ ለማስገንዘብ ያህል እ.አ.አ. በ2006 ዓ.ም. አንደተመዝገበዉ አለም ከሁለት መቶ አምሳ ሁለት ሚልዮን ሂክታር በላይ የሚጠጋ የእርሻ መረት ለተዳቀሉ ሰብሎች ምርት የዋለ ሆኖ፣ ከሃያ ሁለት በላይ የሆኑ አገሮች በዚህ ስራ ላይ በቀጥታ ተሰማርተውል። ከነዚህም መካከል ዋነኛው (50% በላይ) አሜሪካ ሲሆን ተከታዮቹ አርጀንቲንያ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ፓራጉዋይ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቡልጋሪያ፣ ኮሎምቢያ፣ ሆንዱራስ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሜክሲኮ፣ ሮማንያና ስፔይን ናቸው። ሆኖም ሰብሎቹ በነዚህና ሌሎች ባልተጠቀሱ አገሮች ውሰጥ የሚመረቱ ቢሆንም፣ በንግድና በዕርዳታ መልክ በለሎች በብዙ አገሮች ውሰጥ ተሰረጭተዋል። ሰብሎቹ በተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ሁኔታ የተሰራጩ ቢሆንም፣ ቀደም ብሎ በተጠቀሱት ምክኒያቶች በብዙ አገሮች ውስጥ ተቃውሞ እየተደረገባቸው ነው። ከነዚህም ተቃውሞዎች መካከል ዋናዎቹ የሚቀጥሉት ናቸው።

እ.አ.አ. በ2004 ዓ.ም. የአውሰትራሊያ መንግስት በብዙ የአገሪቱ ቦታዎች ይደረግ የነበረውን የተዳቀሉ የምግብ ሰብሎች እርሻ እዲቋረጥ አድርጓል። ይህም የሆነበት ምክንያት ሰብሎቹ በጤንነት ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን ቀውስ በመፍራት ነው። በአሜሪካ ውስጥም እንደዚሁ ለምግብነት የሚሆኑ የተዳቀሉ ሰብሎች በርካታ በሆኑ ቦታዎች ያለ ተገቢው ቁጥጥር እንዳይሰራጩና እንዲያውም በአንዳንድ ቦታዎች እሰከጭራሱ መዘራታቸው እንዲቆም ሆኗል። ለዚህ ድርጊት እንደምሳሌ ቬርሞንትንና ሜንዶሲኖ ካዉንቲን (ካሊፎርኒያ) መጥቀስ ይቻላል። በዚሁ በአሜሪካ ውስጥ ተጠቃሚው ሕዝብ ስለሰብሎቹ በይበልጥ እያወቀ በመጣ ቁጥር ተቃውሞውም እንደዚሁ በየቦታው እየበዛ መጥቷል። በእንግሊዝ አገርም ቢሆን በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ጥበብ በተለወጡ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ሲኖር በብዙ ቦታዎች ሰብሎቹ እንዳይሸጡና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ሆኗል። በጃፓንም በኩል ደግሞ ሕዝቡ ከካናዳ የሚመጣውን የተዳቀለ የምግብ ስንዴ ወደ አገር እንዳይገባ ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርቧል። የአውሮፓው ሕብረት እነዚህን ሰብሎቸ አሰመልክቶ ከአሚረካን የተለየና የጠበቀ ህግ ሲከተል፤ በዚህ በኩል በአባል አገሮች የሚነሱትን ጥያቄዎች እንደአግባቡ እያንፀባረቀና በየፈርጁ መልካም ውጠት ያለው ስራ እያካሄደ ነው። ለምሳሌ ያህል በሕዝብ በተነሳው ተቃውሞ እ.አ.እ. በ2002 ዓ.ም. 61% የሆኑ የአውሮፓ የግል ድርጅቶች በተዳቀሉ ሰብሎች ላይ የሚያደርጉትን ሳይንሳዊ ምርምሮች እንደያቆሙ ሆናል። እላይ እንደተመለከተው የጐላ ባይሆንም በሌሎች በተለያዩ አገሮች ውስጥ በነዚህ ሰብሎች ላይ በየጊዘው ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳለ ግልፅ እየሆነ መጥቷል።

በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ስናተኩር ከደቡብ አፍሪካ በስተቀር በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተለውጡ ሰብሎች ለአገልግሎታቸው በየትኛውም አገር ሕጋዊ ተቀባይነት አላገኙም። በደቡብ አፍሪካ በሕጋዊነት ተመዝግበው አስፈላጊ የሆኑት ሰብሎች ይመረታሉ፣ ከውጪ አገር ወደ አገር ውስጥም ይገባሉ፤ ከጥቅምም ላይ በሰፊው ይውላሉ። በአንፃሩ ደግሞ አስፈላጊ ያልሆኑት በሁሉም መንገድ ይከለከላሉ።

የቀሩት የአፍሪካ አገሮች የተለወጡትን ሰብሎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ ባይቀበሉም፣ ይህን አቋም እንዲሽሩ ከሀያላን አገሮች፣ ኩባንያዎችና ከሊሎች ድርጅቶች ከፍተኛ ተፅዕኖ ይደረግባቸዋል።  ከብዙዎቸ መካከል እላይ የተጠቀስው የአፍሪካ አዲሱ “አረንጓዴ አብዮት” ሕብረት (AGAR) አንዱ ተጽንኦ አድራጊ ነው። በአገራቸውም ውስጥ የተንሰራፋው የሙስና ተግባር ይህንን አስመልክቶ የተደነገገው ሕግ ከጊዘ ውደ ጊዘ እንዲጣስ አድርጓል። ይህን አሰመልክቶ ለምሳሌ ያህል፤ ኢትዮጵያንም በመጨመር፤ በርከት ያሉ የአፍሪካ አገሮች ከውጪ የሚወስዱት የምግብ እርዳታ በብዛት በተዳቀሉ ሰብሎች የተበከለ ነው። ሆኖም ይህንን አስገንዘቦ በሚነሱት የተቃውሞ ጥያቄዎች ምክንያት አንዳንድ አገሮች (ምሳሌ፦ ሱዳን፣ ዛንቢያ፣ አንጐላ) ድርጊቱን ለማቆም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ጠበቅ ያለ እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው። ሌሎችም የዚህን ፈለግ ለመከተል የተገደዱ ይመስላል። የተዳቀሉ ሰብሎችን በይበልጥ በአፍሪካ ለማሰራጨት ከውጭ በኩል የሚደረገው ተፅዕኖም እንደዚህ በብዙ ቦታዎች ተቃውሞ እየደረሰበት ነው። ለዚህ ተቃዉሞ ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያደርጉ የሕዝብ ድርጅቶች ውይም ማህበሮች ተቋቁመዋል። ተቃውሞ ከሚደረግባቸው የውጭ ድርጅቶች መካከል ጌትስ ድርጅት በዋናነት የሚጠቀስ ነው። ይህ ፋውንዴሽን ከሮክፈይለር ድርጅት ጋር በመሆን የአፍሪካ “አረንጓዴ አብዮት” ሕብረት (AGAR) የተሰኘ ማዕከል ማቋቋሙ እላይ ተመልክታል። እንደገና ለማሰገንዘብ ያህል፤ የዚህ ማዕከል ዋና አላማው በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተለወጡ ሰብሎችን በአፍሪካ ውስጥ በይበልጥ ማሰራጨት ነው። ለጥንቃቄ ያህል በተጨማሪ እ.እ.እ በ2007 ዓ.ም. አርባ የሆኑ የአፍሪካ አገሮች የተዳቀሉ ሰብሎች ከአንድ አገር ወደ ሌላ ሰለሚተላለፉበት ሁኔታ ለመቆጣጠር ያሚያስችል ስምምነት አድርገዋል። በሌላ አባባል ይህ ስምምነት ሰብሎች ያለገደብ አንድ አገር ውስጥ ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱ የሚከላከል ነው። ነገር ግን ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ አገሮች አቅምም ቁርጠኝነትም ያላቸው አይመስልም። የተቀየሩ ሰብሎችን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ባለመቃወም በአሁኑ ጊዜ ዘጠኝ የሆኑ አፍሪካ አገሮች ደግሞ በነዚህ ሰብሎቹ ላይ የእርሻ ሙከራ ምርምር እንደሚይደርጉ ተመዝግቧል። ሃያ አራት የሚሆኑት ደግሞ በሰብሎቹ ላይ መሰረታዊ የሆነ የላቦራቶር ምርምር ያካሂዳሉ። በሁሉም በኩል ለምርመር ተብሎ የሚደረገው አብዛኛው ወጪ ከውጪ የሚገኝ ሲሆን፣ ምርምሩ ወደፊት ወዴት አቅጣጫ እንደሚያመራ ግልፅ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬም አይመረንም - ይገረም አለሙ

 

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎችን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ምን የመሰለ ነው?

የህ ጽሁፍ እሰከተዘጋጀበት ጊዘ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂን ከጥቅም በማዋል ስለሚመረቱ ሰብሎች በይፋ የታወቀ ብዙ ነገር የለም። ነገር ግን በርከት ያሉ ውሰጣዊ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት እነዚህ ሰብሎች በምግብነት አገልግሎት ላይ እንዲውሉና በአገርም ውስጥ እንዲመረቱ ጥረት እየተደረገና ጥናትም እየተካሂደ ነው።

ለአገሪቷ የእርሻ እንቅስቃሴና ዕድገት የባዮቴክኖሎጂን አስፋላጊነት የሚያመለክት ብሔራዊ ፖሊሲ ወይም ፕሮግራም እንደተረቀቀ ተገልጻል። በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተለወጡ ሰብሎችን ከአንድ አገር ወደ ሊላ ማሰተላለፊን ለመቆጣጠር ተብሎ የተደረገውን አለም አቀፍ ስምምነት በስልጣን ላይ ያለው ኢትዮጵያ መንግስት ለማስመስልም ይሁን ውይም በማመን ተቀብላል። የባዮቴክኖሎጂን ስራ መሰፋፋትን አስመልክቶ የአመሪካ መንግስት ወይም ድርጀት ለሚሰጠው “እርዳታ” ኢትዮጵያ (ወይም የኢትዮጵያ ገበሪ) አንዷ ተቀባይ አገር እንድትሆን ተደርጋል። ለምሳሊ ያህል የምግብ እርዳታ ፕሮግራም በሚል ሰም የአገሪቱ ደሃ ገበሪዎች በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ተክኖሎጂ የተለወጡ ሰብሎችን እንዲያመርቱ በማታለል ዘር ሰጪ ኩባንያዎች (ሞንሳንቶ፤ አርች ዳኒል ሚድላንድ) የማያቃርጥ ክፍያ ከገበሪዎች በመጠየቅ መላውን የግብርና ሰራ በቁጥጥራቸው ሰር ለማድረግ ጥረት እያረረጉ ነው። በተጨማሪም የአገሪቱ የእርሻ ምርምር ድርጅት በራሱ ምግብን በሚመለከት በባዮቴክኖሎጂ ስራ የተሰማራ ሲሆን፣ በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ተክኖሎጂ በተዳቀሉ የድንች ዘሮች ላይ ጥናት  ከሚያደርግ አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበርም ይሰራል። ይህ አለም አቀፍ ድርጅት በዩጋንዳና ኪንያ ውስጥ ካሉ የድንች ምርምር ማዕከሎች ጋር ተመሳሳይ የስራ ግንኙነት አለው። ድርጅቱ ዋነኛ አላማዬ ነው ብሎ በይፋ የሚያሳውቀው የጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም “የተሻሉ” የድንች ዘሮችን በነዚህ አገሮች መፍጠርን ወይም ማስፋፋትን ነው።

ርሃብን ለመቋቋም ተብሎ የኢትዮጵያ “መንግስት” ከውጭ አገሮች የምግብ እርዳታ በመደጋገም ተቀብላል። በዚህ ሰበብ በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ የእህል ዘሮችና ዉጤቶቻችው በሰፊው ወደ አገሪቱ ገብተዋል። ስለሆነም ረሃብ በኢትዮጵያ ውስጥ ደጋግሞ ሊከሰት መቻሉ እነዚህን ሰብሎች ያለችግር ለማስገባት ለሰሪዎቻቸው ኩባንያዎችና አጋሮቻቸው ጥሩ ምክንያት ሆኗቸዋል። እንዲያውም ይባስ ብሎ ሰብሎቹን ወደአገር ውሰጥ ማስገባቱ እንዲጨምር ይርሃብ ችግር ሳይኖር እንዳለ ተቆጥሮ የተወሰደበትና የታወጀበት ጊዜ ነበር። እዚህ ላይ በይበልጥ የሚያሳስበው እነዚህ እህሎች በተመጋቢዎች ባለማቋረጥ በብዛት ሲወሰዱ በጤንነት ላይ ሲያስከትሉ የሚችሉት ጉዳት በትክክል አለመታወቁና ጥሬ ዘሮቹም በእርሽ አካባቢ ያለፕላን የመዘራት ውይም የመተከል እድል እንደሚኖራችው መገንዘቡ ነው።

ያለውን የምግብ እጥረትና የአገሪቱን የተበላሸ አሰተዳደርና የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም የዉጭዎቹ ድርጅቶች በከፊልም ቢሆን የነበሩትንና አሁንም በየቦታው ያሉትን የአገሪቱን የእህል ዘር ማከፋፋያ አውታሮች በመግዛት ውይም ሆን ብለው በማውደም የራሳቸው ንብረት የሆኑትን የተዳቀሉ የህል ዘሮች በተፈጠረው ቀዳዳ አማካኝነት በብዛት እያሰገቡ እንዳሉ የሚያመለክቱ መረጃዎች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች አገሮች በብዙ ሁነታዎች ልዩ የሆኑትን የአገሪቱን የእህል ዘርና ሌሎች ዕፀዋትን በድብቅ በመውሰድ ወይም በማስወጣት በቴክኖሎጂ ጥበብ ለውጠዋቸው የግል ባለበትነት መብትን በማግኘት ላይ ናቸው። ይህ ሁኔታ እየቀጠል ከሄደ እላይ በሰፊው እንደተዘረዘረው በመጨረሻ የአገሪቱ አጠቃላይ የምግብ ይዘትና የተፈጥሮ ሀብት በሌሎች ቁጥጥር ስር ሊውል የሚችል ይሆናል። ጉዳዩን በይበልጥ አሳሳቢና አሳዛኝ የሚያደርገው ለተሸረበው ተንኮል የዜግነትንና የሃለፊነትን ግዴታ ተቀብለዉ ለሰፊው ህዝብ የሚበጅ መፍትሔ ከመሻት ይልቅ፣ የአገሪቱ አስተዳዳሪዎች የጀነቲክ ኢንጂነሪንግ በአኢተዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ያለአዋቂ ምክር በትመስፋፋት በይፋ ድጋፍ መስጠታቸው ነው። ይህ ድርጊት ብቻውን ከአብዛኛዎቹ የአለም (እንዲያውም የባሰ ብሎ ከአፍርካም ጭምር) መሪዎች የኢትዮጵያን መሪዎች ተልዩ የሚያደርጋቸው አንዱ ፀባያቸው ነው። አሜሪካና ሊሎች ተመሳሳይ የዳበሩ አገሮች በኢትዪጵያ ላይ ካላቸው ወቅታዊ ፓሊሲ ጋር ሲገናዘብ ምናልባት ይኼ ዶክተር ሄኔሪ ኪስንጀር እ.አ.አ. በ1974 ኢትዮጵያንና ሌሎች አስራ ሁለት ታዳጊ አገሮችን አስመልክተው በNSSM 200 ሰነድ ውስጥ ከጠቀሱት ፓሊሲ ጋር ይገናኝ ይሆን? መልስ ሊያገኝ የሚገባው ተግቢ ጥያቄ ነው።  እዚህ ላይ ሳይጠቀሰ መታለፍ የሊለበት፤ ይህም ሁሉ ችግር ኖሮ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጉዳይ ድርጅት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/አግዚአብሃር ለሶሰተኛ አለም አገሮች ዘላቂ ጥቅም በማሰብ ከዚህ በፊት በዚህ በኩል የሚያደርጉት ጠንካራ ትግል ነው።  ይህ መልካም ሰራቸው ተግባሪያዊነቱ ገና ብዙ የሚቀረው ቢሆንም በብዙዎች ዘንድ እንዲታወቅና እንዲመሰገኑም አድርጛቸው ነበር።  ሊሎች የሚመለከታችው ባለሞያዎችም የሃብታም (የዉጭ) የእርሻ ኢንዱሰትሪዎች የጥቅም ተግዢና ጭፍን የመንግሰት አገልጋይ ከመሆን ይልቅ በያሉበት የዶክተር ተወልደን ፈለግ በመከተል ለሰፊው ህዝብ ወይም ላገር የሚበጅ አግልግሎት በዚህም በኩል የመሰጠት ሃላፊነት አለባቸው፤ ህሊና ካላቸዉ የሞያም ግዲታቸው ነው።

በጀነቲክ ኢንጂነሪነግ ቴክኖሎጂ ሰብሎችን በመቀየር ለብዙሃን ጐጂ የሆነው ተግባር እንዳይቀጥል ከተፈለገ ምን መደረግ አለበት?

ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በእርሻ ምርት አማካኝነት ሊያመጣ የሚችለውን ጥፋት ለማስወገድ የሚወሰደው እርምጃ እንደቦታዉና ሁኔታው የሚለያይ ሊሆን ይችላል። ሊወሰዱ የሚገባቸው ዋንኛ ወይም መሰረታዊ እርምጃዎች ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡት ቀጥሎ ባጭሩ ተጠቅሰዋል።

የባዮተክንሎጂ አገልግሎት በአጠቃላይ በብዙ ሁኔታዎች አስፈላጊ ቢሆንም፣ በፅሁፉ በሰፊው እንደተገለፀው በዚህ በቴክኖሎጂው ጥበብ የተለወጡ ሰብሎች ለጥቅም እንዲውሉ ከመደረጋቸው በፊት በጤንነትም ሆነ በአካባቢ የተፈጥሮ ሁኔታ ላይ ጐጂ አለመሆናቸው መረጋገጥ አለበት።

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ጥበብ የተዳቀሉ ሰሎችን አስመልክቶ የሚካሄዱት ምርምሮች ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል ከግል ኩባንያዎች ይልቅ ሕዝባዊነት ባላቸው ድርጅቶች (public institutions) በኩል ቢካሄዱ ይመረጣል። ተመሳሳይ ለሆኑ ቸግሮቸ የዚህ አይነቱ አስራር የተሳለ ውጢት ማምጣቱ ተመዝግባል።

የተዳቀሉት ሰብሎቸ ወይም የሰብሎቹ ውጤቶች በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ ከሌሎች ካልተለወጡ የሰብል አይነቶች ወይም ውጤቶች (organic products) በቀላሉ ተለይተው የሚታወቁበት መንገድ መኖር አለበት።  ይህ ሲሆን ተጠቃሚዎቸ የሚፈልጉትን የመምረጥ እድል ይኖራቸዋል፤ አንሰተኛ አምራች ገበሪዎቸም ቢሆኑ አሰፍላጊውን ጥንቃቂ ለመውስድ ይረዳቸዋል።

ታዳጊ አገሮች በተጠቀሱት የባዬቴክኖሎጂ ውጤት በሆኑ ሰብሎች ላይ ተስፋቸውን ከመጣል ይልቅ ተፈጥሯዊ (organic) በሆኑ ምርቶች ላይ በይበልጥ ቢያተኩሩ የተሻሉ ውጤቶችን እንደሚያገኙ በብዙዎች ይታመናል። በተፈጥሮ ላይ በተመረኮዙ ምርቶች ማተኮሩ ቢያንስ ቢያንስ የሚከተሉት ጥቅሞች ይኖራሉ። በባዮቶክኖሎጂ ጥበብ ከተዳቀሉት ስብሎቸ ጋር ሲወድደሩ እነዚህ ምርቶች፦

በጤንነት ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉት የተለየ ጉዳት የላቸዉም።

በአካባቢ የተፈጥሮ ሁኔታ ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉት ለውጥ ውይም ጉዳት አነሰተኛ ወይም የማይቆጠር ነው።

በአሁኑ ወቅት በብዙ ቦታዎች በተጠቃሚዎች ተፈላጊ ስለሆኑ (በተለይም የጢንነትን ጉዳይ አሰመልክቶ) አምራቾቻቸው ከሽያጭ ትርፍ በይበልጥ ይጠቀማሉ።

ዘላቂነት ያለው የእርሻ ስራን ያበረታታሉ፤ ሰልሆነም በተልይ በታራጊ አገሮቸ ውሰጥ በምርት እጥረት ምክኒያት ሊመጢ የሚቸሉ ቸግሮቸን (ምሳሊ፤ ርሀብ) ይቀንሳሉ።

አነስተኛ የአገር ገበሬዎች የዉጥ ሃብታም ድርጅቶችና የተባባሪዎቻቸው ጥገኛ ከመሆን ይጠብቃቸዋል።  በተጥማሪም  ገበራዎች የንብረታቸዉ ባለባትና የራሳትዉን አድል ወሳኝ ድርሻ አንዲኖራቸዉ ይረዳሉ።

በባዩቴክኖሎጂ አገልግሎት በተፈጠሩ ሰብሎች ዙሪያ ያለው ችግር እላይ እንደተል ወሳኝ ጠቀሰው ሊቃለል የሚችል ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ውስጥ ያንሰራፋው የአስተዳደር ጉድለት ሁሉንም ጥረት ውጤተቢስ የሚያደርግ ነው። ስለዚህ በሰብሎቹ ምርት በኩል ለማሻሻል ተበሎ የሚፈለገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ሕዝብ የሚፈልገው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደሩ ከሁሉ በፊት እንዲኖር የግድ ነው።  ይሀም በምኞት ብቻ ስይሆን በጥረት የሚገኝ ነው።

 

ማጠቃለያ

በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የተዳቀሉ ሰብሎችን በአለም በሰፊው ለማሰራጨት ስሪዎቻቸውና ሊሎች የሚመለከታቸው የመንግስተም ሆኑ የግል ድርጅቶች ያልተቋረጠ ጥረት እያደረጉ ነው። በዚህ በኩል ታዳጊ አገሮች (በተለይም በሕዝብ ብዛትና በተፈጥሮ ሃብት ባለፀጋ የሆኑት) የበለጠ ትኩረት እየተሰጣቸው ነው። እነዚህ ሰብሎች በባለቤትነት የተያዙት በጥቂት የሃብታም አገሮች ኩባንያዎችና አጋሮቻቸው ሲሆን፤ ጉዳዩ በተጠቃሚው ሕብረተሰብ ዓይን ሲታይ የስብሎቹ አገልግሎት መሰረታዊ ከሆኑ የጢና፤ የኢኮኖሚ፤ የአካባቢ ሁኒታና የጥገኝነት (የባርነት) ዝንባሌ ችግሮች ጋር የተያያዘ ነው። ይህም በመሆኑ በሰብሎቹ ባለቤቶችና በተባባሪዎቻቸው በዚህ በኩል የሚደረገውን ጥረት ከፊሉ ተጠቃሚዉ ሕብረተሰብ በከፍተኛ ጥርጣሪ የሚያየው ከመሆኑም በላይ በየቦታው ተቃውሞ እየደረሰባቸው ነው። ይህንን ተቃውሞ በማጠናከር እንደአስፈላጊነቱ የሰፊዉን ሕዝብ ፍላጐት ለመጠበቅ የተሻለ አማራጭ ማግኘት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። የአካባበን ሁኒታ በመጠበቅ ተፈጥሯዊ በሆነ የእርሻ ስራ (organic farming) ላይ በይበልጥ ማተኮሩ ታዳሪ አገሮች ወደተሳለ አቅጣጫ በአፋጣኝ እንዲያመሩ ከሚያስችሏቸው ተግባሮች መካከል አንዱና ዋነኛ ሊሆን የሚችል ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሰብል ምርትና የአጠቃቀም ችግር ከአስተዳደር ቀውስ ጋር የተቀናጀ በመሆኑ፣ በቅድሚያ የአስተዳደሩን ችግር ማቃናት የግድ ይላል።

 

ዋቢ ጽሁፎች (Major references)

ወ.አ. ወልደሚካኤል፤ በጀኔቲክ ኢንጂኔሪንግ ቴክኖሎጂ የተለወጡ የእህል ዘሮች ድብቅ አገልግሎታቸው። ሐዋርያ 11:14፤ ኦገሰት 2006 (እ.አ.እ)።

Gebre-Egziabher, T.B. The use of genetically modified crops in agricultural and food production, and their impacts on the environment- a developing world perspective. Acta Agric. Scand. Sect. B. Soil and Plant Sci. Supplementation 1: 9-13, 2003.

Chossudovsky, M.  Sowing the seeds of famine in Ethiopia.  Addis Tribune, September 3, 2004.

Chossudovsky, M. Global Famine. http://www.globalresearch.ca/PrintArticle.php?articleID=8877

Smith, J.  Frankenstein peas.  Ecologist, 36: 18-23, 2006.

Engdahl, W. Seeds of destruction: the geopolitics or GM food.

www.mindfully.org/GE/2005/Geopolitics-GM-Foodmeer05.htm

Paras Chopra. Genetically modified crops in India. Current Statistics of GM Crops in India, 2004.

Anonymous, Part 1. Genetically modified food.

http://bioserv.fill.edu/~biolab/labs/Genetics/ploidy%20and%20genetically_modified_food.htm

Senze Moole and Victor Munnik. GMOs in Africa: food and agriculture status report 2007, The African Center for Biosafety, 2007.

Engdahl, W. “Doomsday seed vault” in the Arctic, Bill Gates, Rockefeller and the GMO giants know something we don’t Global Research, December 4, 2007.

www.globalsearch.ca/PrintArticle.php?articleID=7529.

 

 

3 Comments

 1. The above article on GMO by Zeleke WA is one of the best written specifically on Ethiopia and for Ethiopians. It is a comprehensive article that describes the science of genetic modifications, and politics and economy of GMO in a simple way. The article emphasizes the risk of losing ones own natural/food resources and sovereignty through indiscriminate and uninformed adoption of GMO as designed by manufacturers from the West. In short, it is an educational article that can help readers understand the intricates associated with GMO and provide the necessary knowledge base to protect ones own natural resources, including food sources. It is a must read article.

 2. ወንድም ዘለቀ ምስጋናዬን ወደር የለውም። የእህል ዝርያን ማዳቀል ብሎም በጀኔቲክ ኢንጂነሪንግ የተሰሩ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስራ ላይ እንዲውሉ የአሁኑ መንግሥት ተፈራርሟል። ምናልባትም ይሄንን ጉዳይ የጠለቀ ጉዳዩን የተገነዘቡት አይመስልም ። ምናልባትም በውሉ አጓዋጊ የገንዘብ ጉርሻ እንዳለበት መገመት አያዳግትም ።የሚገርመው የሕወሐት ኢህአዴግ ይሄንን ሁኔታም አልተቀበለውም ነበር። ይሄ ኖቤል ሽልማት ገና ብዙ ዋጋ ሳያስከፍለን አይቀርም።
  ለምሳሌ ጀርመን በአውሮፓ አቆጣጠር 2009 ጀምሮ ምንም አይነት በጄኔቲክ ኢንጂነሪንግ የተፈጠረን በህግ ከልክለዋል። ሌላው ቀርቶ የዚህ እህል የተቀየጠ በማናቸውም ምግብ እንዳይገባ ተወስኗል ። ሌላው ቀርቶ ለከብት መኖነትም አይፈቀድም። በአውሮፓ ህብረት አማካኝነትም ጀርመን ብዙ ተከራክራበታለች ።ብሎም ከአሜሪካ ወደ አውሮፓ የሚገቡ የምግብ አይነቶች በውስጣቸው የተለወጡ ዝርያ ውጤቶች ካለባቸው በየመጠቅለያውና ፓኬጅ ላይ በግልፅ እንዲፃፍ በመፈለጋቸው ፣ከአሜሪካ ጋር ትልቅ ውዝግብ ፈጥሯል።
  በቅርቡ የተፃፈን መረጃ አጣቃሽ በሰፊው እንዲነበብ ቀጥሎ ያለውን አመላካች አንባቢ ይመልከተው።
  https://www.satenaw.com/usda-pleased-with-ethiopian-govt-for-its-willingness-to-approve-gmos/

  • Thank you very much Ato Tsegaw for the nice words, sending me the Satenaw article and, more importantly, for reading my article critically. When you think about it, it is heart-breaking to see our people going through difficult times for so long due to maladministration. However, we should not give-up and try whatever we can to make desirable changes. I am eager to read the article sent me.

   NOTE: Please share my article with friends and others as much as you can. It may even be more useful if you send it an official who may be involved in agriculture related activity or something like that.
   Zeleke

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.