/

ታንኩም ባንኩም ፣የሻቢያ፣ ወያኔና፣ ኦነግ  ጦር አበጋዞች ሆነ፣  የህወሓት ፓርቲ ንግድ ድርጅቶች ዘረፉ! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

 (ክፍል አንድ)

ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ዮሐንስ አያሌው፣ አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ ባጫ ጊና

አሁንም ያሉት ከርቸሌ፣ የሚገቡትም ከርቸሌ!!!

“ብልፅግና ፓርቲ ጠንክረን ሰርተን ስልጣናችን ማራዘም ካልቻልን እና ምርጫ ተካሂዶ ሌላ ፓርቲ ካሸነፈ ጠቅላላችን ወደ ከርቸሌ እንደምንገባ ማወቅ አለባችሁ ሲሉ የብልጽግና ዋና መሪዎች በዝግ ስብሰባ ተናገሩ። በዝግ ስብሰባው የተናገሩት ከአባላቱ ደርሶኛል ብሎ ኢትዮ 360 የኢሳት የበኹር ልጅ የሆኑት እነ ምናላቸው ስማቸው ኤርምያስ በዜና እንደተገለፀው ከሆነ ብልፅግናዎች በኮረና በሽታ በውጪ ጦርነት ትንኮሳ አመካኝተን እና የህገ መንግስቱን ትርጉም አምጥተን ምርጫዉን አራዝመን ካልቆየን ወደ ፌደረሽንም ወስደን እንደምንም አሻሽተን ካልቆየን በቀር እያንዳንዳችን ወደ ከርቸሌ የሚያስገባን ነው ሲሉ Ethio 360 ከፓርቲው ተላላኪዎች አገኘሁት ብሎ እንደጠቀሰው ከሆነ።” (April 28, 2020)

የክሱን ቻርጅ  እነሆ!!! ወያኔና አርባዎቹ ሌቦች!!!

የሻቢያ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የወያኔ መለስ ዜናዊ፣ ኦነግ/ኦዴፒ ብልፅግና ዶክተር አብይ አህመድ የጦር አበጋዞች፣ ሃገሪቱን በታንክ ወረሩና  የፓርቲ ንግድ ድርጅቶቻቸው መሬቱን፣ ባንኩን፣ ወርቁን  ሁሉ ዘረፉ፡፡ ለሻብያና ወያኔ ኦነግ የጦር አበጋዞች ሁሉን ነገር ያመቻቹላቸው የፋይናንስና ባንክ ዘርፍ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ካድሬዎች  ሚስጥሩን በተለይም ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድና ተክለወልድ አጥናፉ የመለስ ዜናዊ ቡችላ በመሆን ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ያስበዘበዙ አድርባይ ምሁራን በወንጀሉና በዘረፋው በተባባሪነት አገልግለዋል፡፡ ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ዮሐንስ አያሌው፣ አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ ባጫ ጊና በሃገራችን ህግና ተጠያቂነት ሲኖር የህዝብ ተቀማጭ ገንዘብ ያለአግባብ በአድሎ በማበደር ኢፍህታዊ ሥራቸው  አንድ ቀን በሰሩት ወንጀል ይጠየቃሉ፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ የተደበቀው አድሎዊ አሠራርና የሙስና ወንጀል ለናሙና ያህል እንጠቅሳለን፡-

አንደኛ ከ1983 እስከ 2010ዓ/ም (የህወሓት /ኢህአዴግ መለስ ዜናዊ ዘመን)

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር የወሰዱ የትዕምት ኩባንያዎች ዝርዝር (ኢልባ ዋና መስሪያ ቤት)1

 • በኤርትራ ይገኙ የነበሩ ባንኮችና ኢንሹራንሶች በኢሳያስ አፈወርቂ ሃብትና ንብረት መሆናቸው አንሶ፣ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በብድር የተሰጠ አንድ ቢሊዮን ብር ሳይመለስ ቀርቶል፡፡
 • በትግራይ አልሜዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን 678,545,855 ሚሊዮን ብር
 • መሶቦ የህንጻ መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን መጀመሪያ 589,015,862 ሚሊዮን ብር ፣ለሁለተኛ ጊዜ 386,428,085 ሚሊዮን ብር ሲሆን ጠቅላላ ድምር 975, 443,947ቢሊዮን ብር
 • አዲስ የመድሃኒት ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን መጀመሪያ 396,162,029 ሚሊዮን ብር፣ ሁለተኛ 21,184,354 ሚሊዮን ብር፣ ሦስተኛ 18,013, 652 ሚሊዮን ብር ሲሆን ጠቅላላ ድምር 435,360,035 ቢሊዮን ብር
 • ሳባ የቆዳ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን 115,701,605 ሚሊዮን ብር
 • ደደቢት የብድር ቁጠባ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን አንደኛ 61,792,652 ሚሊዮን ብር፣ ሁለተኛ 40,000,000 ሚሊዮን ብር ሦስተኛ 26,188,000 ሚሊዮን ብር አራተኛ 20,500,000 ሚሊዮን ብር ሲሆን ጠቅላላ ድምር 148,480,652 ሚሊዮን ብር
 • አበርጌል ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2002ዓ/ም የተወሰደ የብድር መጠን 40,268,489 ሚሊዮን ብር
 • ለኢፈርት ኩባንያ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተሠጠ ጠቅላላ ብድር በ2002ዓ/ም 2,393,800,583 ቢሊዮን ብር
 • በልማት ባንክ የተሠጠ ጠቅላላ ብድር በ2002ዓ/ም 6,816,863,944 ቢሊዮን ብር

ምንጭ

በኢፈርት ስም ካፒታላቸው የሚታወቁ ድርጅቶች ውስጥ አብርሃ ደስታ ይፋ ያረጋቸው ካፒታላቸው የሚታወቅ የትዕምት ኩባንያዎች 2

 • መሶቦ ሲሚንቶ ቁጥር 1 ቆሚ ንብረት ካፒታል 3.467 ቢሊዮን ቁጥር ሁለት 4.395 ቢሊዮን ጠቅላላ ድምር 862 ቢሊዮን ብር
 • ሱር ኮንስትራክሽን ቆሚ ንብረት 4.179 ቢሊዮን ብር
 • ትራንስ ኢትዮጵያ 650 ቆሚ ንብረት 2.934 ቢሊዮን ብር
 • መስፍን ኢንጂነሪንግ መቀሌ ቆሚ ንብረት 2.500 ቢሊዮን ቃሊቲና ዱከም 2.643 ቢሊዮን ትናንሽ መኪና መገጣጠሚያ 350 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ድምር   493 ቢሊዮን ብር
 • ጉና ኮርፖሬሽን በመላ ኢትዮጵያ 23 ቅርንጫፍ 5412 ቢሊዮን ብር
 • ሜጋ ኮርፖሬት ቆሚ ንብረት 1.2 ቢሊዮን ብር
 • ውቅሮ ሳባ ቆዳ ፋብሪካ ቆሚ ንብረት 600 ሚሊዮን ብር
 • አዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ 700 ሚሊዮን ብር
 • ኢዛና ወርቅ ማዕድን 900 ሚሊዮን ብር
 • ብሩክ ተስፋ ላስቲክ ፋብሪካ 480 ሚሊዮን ብር
 • ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ 746 ሚሊዮን ብር
 • ህይወት እርሻ ሜካናይዤሽን 820 ሚሊዮን ብር
 • ተከዜ ጥልቅ ጉድጎድ ቁፋሮ 467 ሚሊዮን ብር
 • አድዋ እምነበረድ ፋብሪካ 790 ሚሊዮን ብር
 • አድዋ ጨርቃጨርቅ ስፌት ፋብሪካ 315 ሚሊዮን ብር
 • አድዋ ጨርቃጨርቅ ቁጥር አንድ ፋብሪካ 1.757 ቢሊዮን ብር፤ ቁጥር ሁለት ፋብሪካ 1.917 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ድምር 3.674 ቢሊዮን ብር
 • ስታር መድኃኒት አስመጭና አከፋፋይ 150 ሚሊዮን ብር
 • ደደቢት ብድርና ቁጠባ 6.25 ቢሊዮን ብር
 • ፔርሲ የተሸከርካሪ ጎማ አከፋፋይ 560 ሚሊዮን ብር
 • ጥጥ መዳመጫ ሁመራ 200 ሚሊዮን ብር

በኢፈርት ስም ካፒታላቸው የማይታወቅ የንግድና ኢንዱስትሪ ድርጅቶች ውስጥ አብርሃ ደስታ ይፋ ያረጋቸው 3

ካፒታላቸው የማይታወቅ የትዕምት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ካፒታላቸው ከ39.304 ቢሊዮን ብር ይገመታል፡፡

 • ኤክስፕሬስ ትራንዚት (አዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ዱከም፣ ደቻቱ፣ጅቡቲ)
 • ድምጽ ወያኔ ትግራይ
 • ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል
 • ሬዲዩ ፋና
 • ወጋገን ባንክ 32 ቅርንጫፍ 51 በመቶ የህወሓት ሼር
 • አፍሪካ ኢንሹራንስ 18 ቅርንጫፍ 20 በመቶ የህወሓት ሼር
 • በለንደን፣ ዱባይ አሜሪካ፣ ሳውዲ አረቢያ ያሉ ቤቶች ኪራይ
 • የትግራይ ተራድኦ ድርጅት (ሬስት)
 • የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ)
 • የትግራይ የጦር አካል ጉዳተኛ ከቢሊዮን በላይ ካፒታል
 • የህወሓት ታጋዬቸ መረዳጃ ማህበርአበርገሌ የፍየል፣ የበግና ከብት ማድለቢያ
 • የቻይና ኢፈርት ወርቅ ቁፋሮ በሽሬ መደባይ
 • ኢፈርት ወርቅ ቁፋሮ በሽሬ ፅንበራ

{I} የክልላዊ መንግስቶች የንግድ ኢንተርፕራይዝ (Regional state-owned enterprise (SOE) sector)

የህወሓት ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ትግራይ እንዶንምንት (ትእምት) The Endowment Fund For The Rehabilitation of Tigrai (EFFORT)

አንደኛው በህወሃት የፖለቲካ ድርጅት የሃብት ቁጥጥር ስር የሚገኘው (ትእምት)  የሚባል የንግድ ድርጅት በ1987 ሲሆን የዚህም የሃብት ምንጭ ህወሃት በሽፍትነት ለአስራ ሰባት ዓመታት ከኢትዬጵያ ህዝብ የዘረፈው ሃብት ነው፡፡ ኢፈርት ሁለት ክንፎች አሉት አንደኛው ክንፉ የኢንቨስትመንት መዓከል ሲሆን ሁለተኛው ክንፉ ደግሞ በጎአድራጎት ማዕከል ናቸው፡፡ የኢፈርት የኢንቨስትመንት መዓከል በ14 የተለያዩ ካንፓኒዎች የተደራጅ ናቸው፡፡በኢፈርት ሙሉ ውክልናና ኃላፊነት ተሰጥቶቸው ካንፓኒዎቹን የሚያስተዳድሩትና የሚመሩት ሼር ሆልደርስ ናቸው፡፡ የኢንቨስትመንት መዓከሉ ሁሉን ዓቀፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት (socioeconomic development) ሊያመጡ የሚችሉ በአስተዳደር ቴክኒክና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ምጡቅና ቅልጡፍ ሠራተኖች ማስማራቱን ይገልፃል፡፡

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኢኮኖሚ ምሶሶ የሆነው ኢፈርት የቢዝነስ ኢምፓየር በኢትዬጵያ የግሉን ዘርፍ ባለኃብት በመቀናቀንና ሥራዎችን በመንጠቅ የሃገሪቱን ኃብት በሞኖፖል የሚቆጣጠር የህቡዕ ወይም ሚስጥራዊ ስውር ድርጁት ነው፡፡  የኢፈርት መሠረቱ የተጣለው በ1978 አ.ም ማሕበረ ረድኤት ትግራይ(ማረት) (Relief Society of Tigrai (REST) የህወሃት የገንዘብ ጃንጥላ፣ ሆኖ እንደ በጎአድራጎት ድርጅት  በተቆቆመበት ግዜ ነበር፡፡ ምንም እንኮን ማሕበረ ረድኤት ትግራይ የጎአድራጎት ድርጅት  ቢሆንም ቅሉ የሚመራው በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ማእከላዊ ኮሚቴ ነበር፡፡ በተለይ በርሃቡ ዘመን ከዓለም አቀፍ ኮሚኒቲውና ከውጭ ዲያስፖራ የሚጎርፍልትን የገንዘብ ድጋፍ ህወሓት የደርግን ወታደራዊ አገዛዝ ለመደምሰስ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጎለታል፡፡

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በ1991እኤአ በትረ ስልጣኑን ከደርግ እንደተረከበ ማረት በእርዳታና መልሶ ማቆቆም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በበጎ አድራጎት ድርጅት(“NGO”) ስም ተመዝግቦ  የህወሓት መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጡጦ እየተጋተ ከአፍሪካ አህጉር ውስጥ በኃብት ትልቁ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (ኤንጂኦ) ለመሆን በቃ፡፡ በ1995 እኤአ ህወሓት ለማረት ብረት መዝጊያና ጠንካራ አጋር ድርጅት መሠረተለት፣ትግራይ እንዶንመንት (EFFORT), የተቆቆመበት የኢንቨስትመንት የቢዝነስ ዶሴ ኢፈርት በሁለት ነጥብ ሰባት (2.7) ቢልዩን ብር መሆኑን ገልፆ በማግስቱ አንድ ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር መሆኑ ተገልፆል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኬኒያው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ምን እንማራለን? - በታምሩ ገዳ (ጋዜጠኛ)

It is interesting that despite the restrictions of the law, EFFORT and its branch plants are in every dent of the Ethiopian economy. As a party owned conglomerate, EFFORT is divided into 5 sectors – each having its own share companies headed by senior officials and Cadres.

1-The first area they control is Industry, which is directed by Abadi Zemo. This [industrial] branch has the group companies of Meseo Building Materials Construction, Sheba Tannery, Almeda Textile, Almeda Garment, Addis Pharmaceuticals and Mesfin Industrial Engineering.

2-The second area of control is mining, which is directed by Tedros Hagos, and has under it, Meskerem Investment and Ezana Mining.

3-The third area of control is Finance and Trade directed by Sebhat Nega. This branch owns Wegagen Bank, Africa Insurance and Guna Trading.

4-The fourth branch of control is Construction and Transport directed by Arkebe Uqbay which has under it Addis Consultancy House, SUR Construction and Trans-Ethiopia.

5-The fifth area of control is Agriculture directed by Tsegaye Taimyalew. This branch runs Hiwot Mechanisation, Tesfa Livestock and Rahwa Goat and Sheep Export.

የማኑፋክአሪንግ ዘርፍ (Manufacturing Sector)

(1) ሼባ የቆዳ ኢንደስትሪ (Sheba Leather Industry) በ1993 እኤአ የተቆቆመው፣ ከመቀሌ ከተማ 45 ኪሌ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ውቅሮ ከተማ ውስጥ ያለ ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው የተከፈለ ካፒታል( paid up capital) አስር ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር የተቆቆመ ሲሆን ለ670 ሠራተኞች የስራ እድል ፈጥሮል፡፡

(2) መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ (Mesfin Industrial Engineering)

በኢፈርት የተቆቆመው፣መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ በመቐሌ ከተማ በ1992 ዓ.ም በሰባት ሚሊዩን ብር ካፒታልና በ30 ሠራተኞች እንደተመሠረተ ይታወቃል፡፡ካንፓኒው በመቐሌ በ120000 ሽህ ሜትር ስኮየር ቦታ ላይ  በ35000 ሜትር ስኮየር ቦታ ላይ የተገነባው ማኒፋክቸሪንግ ፋብሪካ ሲሆን በአዲስ አበባም 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በገላን ተመሳሳይ ቅርንጫፍ ፋብሪካ  አለው ፡፡ በአሁኑ ግዜ ካንፓኒው 300 ሚሊዩን ብር ወይም 17.9 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ካፒታል እንዳለው ተገልፆል፡፡  ካንፓኒው 800 ሚሊዩን ብር ወይም 47.6 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር የሚገመት ንብረት ሲኖረው 650 ቆሚ ሠራተኞች እንዲሁም 350 ግዚያዊ ሠራተኞች አሉት፡፡

(3) መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ (የህንፃ መሣሪያዎች ማምረቻ (Messebo Building Material Production)

መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ በ1995እኤአ ከመቐለ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ፋብሪካው የተቆቆመበት የተከፈለ ካፒታል 240 ሚሊዩን ብር  ነው፡፡ የፋብሪካው ኢንቨስትመንት ካፒታል መጀመሪው መስመር 1.2 ቢሊዩን ብር እንዲሁም አዲሱ መስመር 2 ቢሊዩን ብር ወጪ ወጥቶበታል፡፡ ፋብሪካው በ2000 እኤአ ምርት ሲጀምር፣ ኦፒሲና ፕሮቲያን (OPC, protean cement) ሲሚንቶ ዓይነቶች አመረተ፡፡ ፋብሪካው በሃገሪቱ 30 በመቶ የሲሚንቶ ገበያ ድርሻ ሲኖረው በአማካይ 83 ሚሊዩን ዶላር በአመት የንግድ እንቅስቃሴና የተጣራ ትርፍ 25 ሚሊን ዶላር በአመት ሲያገኝ አጠቃላይ ንብረቱም 83 ሚሊዩን ዶላር ሲገመት   ለ1600 ሠራተኞች የስራ እድል ፈጥሮል፡፡

(4) አዲስ መድኃኒት/ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካ(Addis pharmaceutical factory)

አዲስ መድኃኒት ፋብሪካ በ1992 እኤአ በሁለት ሰዋች በጋራ ንብረትነት የተመሠረተ የንግድ ድርጅት ነበር፡፡ፋብሪካው ደቡብ ምዕራብ ትግራይ በአዲግራት ከተማ የተቆቆመ ፋብሪካ ነው፡፡ በ1995 እኤአ አንደኛው ሰው የንግድ ድርሻውን ለኢፈርት አስተለላለፈ፡፡ በ1997 እኤአ ፋብሪካው ምርት ማምረት በመጀመር 30 በመቶ ብቻ የማምረት አቅሙን እንደተጠቀመ ከዛም በህወሓት መንግስት ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች ወደሃገር ውስጥ እንዳይገቡ በማገድና ከአዲስ መድኃኒት ፋብሪካ እንዲገዙ ትእዛዝ በማስተላለፍ የመድኃኒት ገበያ ድርሻውን ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡ በአሁኑ ግዜ የፋብሪካው የምርት አቅርቦት 77 በመቶ መድረሱ ይገለፃል፡፡ ፋብሪካው ምርቱን 130 ዓይነቶች አድርጎ በመጨመርና በ10 የምርት ማምረቻ የመስመር ስርጭት

(5) አልሜዳ ጨርቃጨርቅ(Almeda Textile)

አልሜዳ ጨርቃጨርቅ በ1996 እኤአ በአድዋ ከተማ በኢፈርት የተመሠረተ ድርጁት ነው፡፡ ፋብሪካው ዘመናዊ የጨርቃጨርቅ፣የተለያዩ አልባሳቶች ያመርታል፡፡ ፋብሪካው የጥጥ ማዳወሪያ፣የመፍተያ፣የማቅለሚያና ሁሉን አቀፍ የአልባሳት ማምረቻ ያካተተ ሲሆን የሲዊስ፣ሆላንድ፣የጀርመንና የጣሊያን ስሪት ማሽኖች ተገጥመውለታል፡፡Almeda Textile Factory has a yearly production capacity of 7,020 tonnes of yarn, 16,751,100mt.of grey fabric, 15,387,000mt.of processed fabric, and about one million pieces of basic shirt equivalent garments. የፋብሪካ የግንባታ ወጭ 94 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡ አልሜዳ ፋብሪካ 3600 ሠራተኞች በመቅጠር በዘርፍ በሦስት ፈረቃ ሠራተኞች ያሰማራ ካንፓኒ ለመሆን በቅቶል፡፡ ፋብሪካው በ2007/08 እኤአ 14.6 ሚሊዩን ዶላር  ያለቁ ምርቶች ወደውጭ በመላክ ገቢ አግኝቶል፡፡

የአገልግሎት ዘርፍ (Services Sector)

{1}ትራንስ ኢትዩጵያ (Trans Ethiopia)

ትራንስ ኢትዩጵያ ኃ/የ/የ/ማ በ1993 እኤአ በኢፈርት በተከፈለ ካፒታል 100 ሚሊዩን ብር የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን የደረቅና የፈሳሽ  ጭነቶችን በትራንስፕርት አገልግሎት ዘርፍ ለማመላለስ፣እንዲሁም ከውጭ ሃገር ጎማ ፣ባትሪዎች፣የመኪና ቅባት መሳሰሉትን አስመጥቶ ለማከፋፈልና ለመሸጥ እንዲሁም ከሦስተኛ እስከ አምስተኛ መንጃ ፍቃድ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሣሪዎችን በመጠቀም ስልጠና መስጠት በሚል ሥራ ጀመረ፡፡ ከ2009እኤአ ጀምሮ ትራንስ ኢትዩጵያና ኤክስፕሬስ ትራንዚት ስርቨስ ኢንተርፕራይዝ( Express Transit Service Enterprise) ጋር ሽርክና በመፍጠር ካፒታላቸውን 102.5 ሚሊዩን ብር ከፋ በማድረግ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡ ካንፓኒው ከትግራይ ረድኤት ድርጅት ጋር በመሆን የደረቅና የፈሳሽ ጭነት የትራንስፕርት አገልግሎትና የመኪኖች የጋራዥ አገልግሎት በ458 ጭነት መኪና ከነተሳቢውና በ23  የፈሳሽ ጭነት መኪኖች ይጠቀማሉ እንዲሁም የእቃ ማስቀመጫ መጋዘኖች በኪራይ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ካንፓኒው 1248 ሠራተኞች አሉት፡፡  እንደ አዜብ መስፍን ገለፃ፣ትራንስ ኢትዩጵያ ለአለፍት 20 አመታት የሂሳብ ደብተሩን ኦዲት እንዳላስደረገ ሆኖም የካንፓኒው ካፒታል 270 ሚሊዩን ብር እንደሆነና  ቅርብ ግዜም 2 ቢሊዩን ብር እንደደረሰ ገልፃለች፡፡ በዚች ዓይነት የፖለቲካ  ሥራ አስኪያጅ ተመርቶ እንዴት ትርፋማ መሆን ይቻላል!!! ስንት የተማረ ባለባት ትግራይ ከማለት በስተቀር ምን ይባላል!!!

{2}ኤክስፕሬስ ትራንዚት ሰርቪስ (Express Transit Service)

ኤክስፕሬስ ትራንዚት ሰርቪስ ካንፓኒ በኢፈርት በ1995እኤአ ሲቆቆም በ30 ሚሊዩን ብር ካፒታል የተመሠረተ ድርጅት ነው፡፡ ኤክስፕሬስ ትራንዚት ሰርቪስ ፖርት ሱዳን ወደብን ተጠቃሚ ብቸኛ ትራንዚት ካንፓኒ ነው፡፡ ካንፓኒው የዓለም አቀፍ ትራንስፖርት ድርጁት አባል ነው፡፡ ካንፓኒው ትራንዚት ሰርቪስ በግሉ ዘርፍ የአንበሳውን ድርሻ እንዳለውና በመንግስታዊ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና   የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ብዙ ደንበኞች እንዳሉት በድረ-ገፅ ላይ ገልፆል፡፡

{3}ጉና ትሬዲንግ ሀውስ ኮንስትራክሽን(Guna Trading House Construction)

ጉና ትሬዲንግ ሀውስ ኮንስትራክሽን በ1992 እኤአ በኢፈርት የተቆቆመ የንግድ ድርጅት ሲሆን በ10 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ካፒታል የተመሠረተ ነበር፡፡ በአሁኑ ግዜ በአመት የሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ ( annual turn over) 60 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር እንደሆነ ተገልፆል፡፡ በ2005/6 እኤአ 170  ሚሊዩን ብር የነበር ሲሆን በ2008/9 እኤአ 796 ሚሊዩን ብር ደርሶል፡፡በአሁኑ ግዜ 1ቢሊዩን ወይም 60 ሚሊዩን ዶላር በአመት እንደሚያንቀሳቅስ ተገልፆል፡፡  በአለፉት አምስት አመታት ውስጥ በአጠቃላይ 33.6 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ከሰሊጥ ገቢ አግኝቶል፡፡በአሁኑ አመት ብቻ ካንፓኒው 20000ቶን ሰሊጥ ወደ ውጭ በመላክ 38 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር አግኝቶል፡፡ ይህም የሆነው በዓለም አቀፍ ገበያ የሰሊጥ ምርት ከ900 ወደ 2000 ዩኤስ ዶላር በቶን ከፍ በማለቱ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትዝብት፤ዮንግ ፖለቲከኞች! (ቦጋለ ካሣዬ/ አምስተርዳም)
በኢትዮጵያ 36 ካንፓኒዎች የቅባት እህሎችና ጥራጥሬዎች ወደ ውጭ ሃገር የሚልኩ ሲሆን ዋነኛው ላኪ ጉና ትሬዲንግ ሀውስ ነው፡፡ካንፓኒው ለሳውድ አረቢያና ቱርክ የቅባት እህሎች ይልካል በ2008/9እኤአ 180 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ገቢ በኢፈርት ድርጅቶች የአንደኛ ደረጃ አግኝቶል፡፡ በዚሁ ግዜ ትራንስ ኢትዩጵያ 80 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ገቢ በማግኘት የሁለተኛ ደረጃ አግኝቶል፡፡ እንዲሁም በሃገሪቱ በግሉ ዘርፍ ኤክስፖርት በማድረግ፣የተሰማሩ 60 ካንፓኒዎች የቡና ምርት ወደ ውጭ ሃገር የሚልኩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በኢትዩጵያ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን የጀመሩ የግሉ ዘርፍ ባለኃብት በዚህ መንገድ ነው ከንግዱ ጫዋታ የወጡት፡፡ ቀሪውን ለአንባቢው ህሊናና ፍርድ መተው በቂ ነው፡፡

{4}ሱር ኮንስትራክሽን (SUR Construction)

ሱር ኮንስትራክሽን በ1992 እኤአ በ180 ሚሊዩን ብር መነሻ ካፒታል በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተመሠረተ ካንፓኒ ነው፡፡ በ1995 እኤአ በኢፈርት ድርጅት ሥር ሆኖ በ2003 እኤአ ኃ/የ/የ/ድርጅት ሆኖ በኢፈርት ሥር ተዋቀረ፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን በአሁኑ ግዜ አንድ ቢሊዩን ብር ወይም 60 ሚሊዩን ዩኤስኤ ዶላር ንብረት ያለው ድርጅት ነው፡፡ የሱር ካፒታል 200  ሚሊዩን ብር ወይም 12  ሚሊዩን ዩኤስኤ ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ የሱር አመታዊ ተንቀሳቃሽ ገንዘብ 690 ቢሊዩን ብር ወይም 41 ሚሊዩን ዩኤስኤ ዶላር ደርሶል፡፡ሱር በአሁኑ ግዜ የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች  ዋጋ 3.5 ቢሊዩን ብር እንደሚገመት ኢፈርት አስታውቆል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን በሃገሪቱ ውስጥ ያለው በግንባታው ዘርፍ ያለው የገበያ ድርሻ 10 በመቶ ይዞል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን 1000 የግንባታ ማሽነሪዎችና ፕላንት ሲኖሩት እንዲሁም 1500 ቆሚ ሠራተኞችና 6000 የቀን ሠራተኞች እንዳሉት ኢፈርት በ2010እኤአ ገልፆል፡፡

{5}ሮማናት (Romanat)

ሮማናት በ2009እኤአ በኢፈርት የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡ ሮማናት በዚሁ አመት ልዩ ልዩ ተጣጣፊ የዕቃ ማሸጊያ ካርቶኖች፣ፖሊፕሮፕሊን ቦርሳ/ጆንያ ለአግሮ ፕሮስሲንግና ማኑ-ፋክቸሪንግ ማሸጊያ ምርቶች ማምረት ጀምሮል፡፡ የሮማናት ካንፓኒ ደንበኖች የሆኑ የኢፈርት ድርጅቶች ለመሶቦ የሲሚንቶ ማሸጊያ፣ ለሼባ፣ ለትራንስኢትጵያ፣ጉና እንዲሁም ለብዙ ዱቄት ፋብሪካዎች ምርት ማሸጊያ ሠርቶል፡፡ ሮማናት 260 ሠራተኞች አሉት፡፡ ሮማናት የእቃ ማሸጊያ ካንፓኒ በጉምሩክ አስራርና በአበዳሪ ባንኮች ያለውን ቅሬታ ያንቡት፡፡

{6}ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ (Tower Trading Company)

ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ ወይም ሰናይ ትሬዲንግ ካንፓኒ በ1993እኤአ በኢፈርት በታላቆ ብሪታንያ፣በሎንዶን ከተማ በሼር የተቆቆመ በተከፈለ ካፒታል ሦስት መቶ ሽህ ፓውንድ (share capital of UK£300,000) ተመሠረተ፡፡ የታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ ማኔጀሮች የነበሩ በሎንደን የኢትዩጵያ ኢንባሲ ሁለት ዲፕሎማቶች ከንፓኒውን መርተዋል፡፡ ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ በ2006 እኤአ ዓመታዊ ትርፍ መቶ ሃያ አምስት ሽህ  ፓውንድ (UK£125,000) ፣በ2007 እኤአ መቶ ሁለት ሽህ (UK£102,000) በአጠቃላይ ዓመታዊ ትርፍ ከአንድ ሚሊዩን እስከ 1.2 ሚሊዩን ፓውንድ ይደርሳል፡፡ ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ ያሰገኘው ትርፍ ከኢፈርት አጠቃላይ እንቅስቃሴ አንፃር ገቢው ምንም ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የውጭና ገቢ ንግድ አገልግሎት በመስጠት ትልቅ ሚና ተጮውቶል፡፡ ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ እስከ 2008 እኤአ ምንም ዓመታዊ ትርፍ ገቢ አልተገለጸም፣ታወር ትሬዲንግ ካንፓኒ፣ብሎም በ2010 እኤአ ካንፓኒው በታላቆ ብሪታንያ የካንፓኒዎች መዝገብ እንዲሠረዝ አድርገዋል፡፡

{2} ሳባ ማርብል ፋብሪካ (Saba Stone)Saba Dimensional Stones

ሳባ ማርብል ድንጋይ በ1992 እኤአ በመሃከለኛው ትግራይ በአድዋ በ75 ሚሊዩን ብር ወይም 4.5 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ተመሰረተ፡፡ ሳባ ማርብል ፋብሪካ ምርቶች እብነ-በረድ፣ላይም ስቶን፣ግራናይትና ቴሬዞ ታይልስ ለሃገር ውስጥ ያቀርባል፡፡ ለዓለም አቀፍ ገበያ ንግድ ጥሬ ያላለቀ ማርብል በብዛት ለሳውዲ አረቢያ፣አሜሪካ፣ጣሊያን ያቀርባል፡፡ካንፓኒው በአዲስአበባ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቐለና አድዋ ቢሮዎቹ ለሃገር ውስጥ ገበያ ምርቶቹን ያቀርባል፡፡ ካንፓኒው 200 ሠራተኞች አሉት፡፡

{1} ሕይወት የግብርና ሜካናይዤሽን ኃ/የ/ማ (Hiwot Mechanised Agriculture)የግብርና ዘርፍ

ሕይወት የግብርና ሜካናይዤሽን ኃ/የ/ማ በ1992 እኤአ የተቆቆመ በግብርና ንግድ (ኮሜርሻል ፋርሚንግ)ና የግብርና ማሽነሪዎች መሣሪያዎች (ትራክተር፣ ኮምባይነር፣ ወዘተ) በማከራየትና ለገበሬዎች አገልግሎት ለመሰጠት በትግራይ ውስጥ የተመሠረተ ድርጅት ነው፡፡ ካንፓኒው ሁለት እርሻና አንድ የጥጥ መፈልቀቂያ መኪና/ፋብሪካ በሁመራና በጸገዴ(በአማራ ክልል) ወረዳ አሁን በህወሃት ዘመን በምዕራብ ትግራይ ክልላዊ መንግስት ስር ተከልሎ ይገኛል፡፡ ካንፓኒው በተጨማሪ በራውያአን የከብት ኃብት  ልማትና የእርባታ የእርሻ መሬት አለው፡፡ ካንፓኒው ከተመሠረተ ጀምሮ በአጠቃላይ ያለማው የእርሻ መሬት ከባቦ እርሻ 2,400ሄክታር፣ባናት እርሻ 3,096 ሄክታር፣ኒጉአራ እርሻ 2,382 ሄክታር ማልማቱ ታውቆል፡፡ ሕይወት የግብርና ሜካናይዤሽን በሃያ አምስት ሚሊዩን ብር ካፒታል እንደተመሰረተና 14,000 ሄክታር የእርሻ መሬት በዝናብ በማልማት የተለያዩ ሰብሎችን፣ሠሊጥ፣ጥጥ፣ማሽላ በሁመራና በጸገዴ ወረዳ አልምቶል፡፡ ካንፓኒው መቶ ትራክተሮችና አስር ኮንባይነሮች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ ካንፓኒው አንድ የጥጥ መፈልቀቂያ መኪና/ፋብሪካ 2,100 ቶን ጥጥ ምርት በአመት ከእራሱና ከገበሬዎች እርሻ እያመረተ ለአልሜዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የጥጥ ያቀርባል፡፡

{2}አበርገሌ ዓለምአቀፍ የከብት ኃብት(Abergelle International Livestock Development)

አበርገሌ ዓለምአቀፍ የከብት ኃብት በመነሻ ካፒታል አስር ሚሊዩን የኢትዩጵያ ብር በ2004 እኤአ ተመሠረተ፡፡በአሁኑ ግዜ 27 ሚሊዩን ብር ካፒታል ያለው ድርጅት ነው፡፡ ካንፓኒው በመቀሌ ከተማ የቆራ አገልግሎት፣ በመሆኒ እና በአላማጣ(ወሎ የአማራ ክልል የነበረው) አሁን  (ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ተብሎ የተካለለ) የከብት መኖ ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ  እንዲሁም ሦስት የከብት ማድለቢያ ጣቢያዎች በአላማጣ፣አግቢ፣ሽሬ ይገኛሉ፡፡ ድርጅቱ 80 ቆሚ ሠራተኞች ሲኖሩት ወደፊት በመካከለኛው ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የከብት ሥጋ ምርት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡

{3}ብሩህ ተስፋ የመስኖና ውሃ ቴክኖሎጅ(Bruh Tesfa (Bright Hope) Irrigation & Water Technology)

የብሩህ ተስፋ የመስኖና ውሃ ቴክኖሎጅ በ2004 እኤአ በመቐሌ ውስጥ ተመሰረተ በአዲስአበባም ቅርንጫፍ ቢሮውን ከፍተ፡፡የካንፓኒው ዋንኛ ዓላማ በምስራቅ አፍሪካ አገሮች በመስኖና ውሃ ቴክኖሎጅ መሣሪያዎች አቅርቦት መሪ መሆን ነው፡፡ ካንፓኒው ይህንንም ለመተግበር የሚያመርታቸውን የውሃ ቴክኖሎጅ መሣሪያዎች ጥራትና ንድፍ ለዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በማድረግና የመገጣጠም አገልግሎት በመስጠት ጭምር ነው፡፡ ካንፓኒው ከሚያመርታቸው ምርቶች ውስጥ፣ ዘመናዊ የመስኖ የእርሻ አገልግሎት፤የመስኖ   ተንጠባጣቢ የውሃ ፕላስቲክ ቱቦ፣ኤችዲ ፒኢ ቱቦዎችና መገጣጠሚያዎች፣ የውሃ ቁጠባና የኃይል ፍጆታን ቀናሽ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለደንበኞቹ ለገበሬዎች፣ ለኮሜርሻል ፋርም፣ ለመንግስትና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ምርቱን በማቅረብ አገልግሎት ይሠጣል፡፡

{4}ማጨው የችፑርድና ካንፔልሳቶ ፋብሪካ(Maichew Particleboard Factory)

የማጨው የችፑርድና ኮንፔልሳቶ ፋብሪካ፣ከትግራይ በስተደቡብ በማጨው ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው ባለ ፣የባህርዛፍ ተክል የእንጨት የችፑርድና ኮንፔልሳቶ ምርትና የቤት ዕቃዎች ያመርታል፡፡ፋብሪካው ከነ ባህርዛፍ ተክሉ በ80,000 m2 ሜትር ስካDር ቦታ ላይ የተገነባ ነው፡፡ ፋብሪካው   400 ሠራተኞች እንዳሉት ይታወቃል፡፡

{5}መቐለ የእፅዋት ዘረመል ላብራቶሪ (Mekelle Plant Tissue Culture Propagation Laboratory)

የመቐለ የእፅዋት ዘረመል ላብራቶሪ በ2006እኤአ ሲመሠረት የግብርና ምርት ስርዓቱን ለመለወጥና በተትረፈረፈ የግብርና ምርቶች፣በምግብ እራስን ለመቻል ዓላማ ነበር፡፡ የካንፓኒው ዓላማ የችግኝ ምርቶችን በዓመት ከ3 ሚሊዩን ወደ 5 ሚሊዩን ከፍ ለማድረግ ነበር፡፡ ከችግኞቹ መኃከል ሙዝ፣ድንች ስኮር፣ vines አፕል፣ citrus ባህር ዛፍ፣የሸንኮራ አገዳ፣ አናናስ፣ጉደሬና የአበባ ምርቶች ይገኙበታል፡፡ ይህ ካንፓኒ ቅርብ ግዜ፣ በኢፈርት ለመቐሌ ቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት በስጦታ ተበርክቶል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከራዳር የወጣች፣ ኮምፓሷም የጠፋባት ሀገር - አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

{6}ብሄራዊ የጨርቃ ጨርቅ ቴክኖሎጅ (National Geotextile Technologies (Wukro Gabion Factory)

ብሄራዊ የጨርቃ ጨርቅ ቴክኖሎጅ በ2004 እኤአ በውቅሮ ተመሠርቶ ከአንድ ኣመት በኃላ ምርት መስጠት ጀመረ፡፡ ድርጁቱ የተቆቆመበት መነሻ ካቲታል አስር ሚሊዩን ብር ሲሆን በአሁኑ ግዜ ወደ 17 ሚሊዩን ብር ከፍ ብሎል፡፡ካንፓኒው ለደንበኞቹ ለክልል መንግስት ቢሮች፣ለግል ግንባታ ድርጅቶች፣ለመንግስትና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ምርቱን በማቅረብ አገልግሎት ይሠጣል፡፡ ካንፓኒው 120 ቆሚ ሠራተኞችና 240 ጊዜያዊ ሠራተኞች  አሉት፡፡

{7}አላጌ የደን ልማት አገልግሎት (Alage Forest Development & Utilisation)

አላጌ የደን ልማት አገልግሎት በ2005 እኤአ በመቐሌ ከተማ በደጀና ኢንዶንመንት ስር ተቆቆመ፡፡ የካንፓኒው ዓላማ የደን ልማት ኢንደስትሪ ለማስፋፋት including lumber, and essential oil and briquette production from eucalyptus. የካንፓኒው በቤተሙከራ  ጃትሮፓን፣ aloe, and sisal ጃትሮፓን፣እና የባህር ዛፍ ምርት ለማጨው ችፑርድና ኮንፔልሳቶ ፋብሪካ ያቀርባል፡፡

በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ሌሎች የትግራይ ተዋናዩች (Other economic actors in Tigray)

EFFORT and its companies form part of a network of organisations active in the regional economy of Tigray, many of which also have close links to the ruling party. Some of them also emerged during the TPLF’s military campaign against the previous government. Of these, EFFORT companies enjoy co-operative or collaborative relations with each of:

❑ትግራይ ረድኤት ድርጅት  (The Relief Society of Tigray (REST);

❑ትግራይ ልማት ማህበር ( The Tigray Development Association (TDA);

❑ትግራይ ከዘመቻ የተመለሱ ማህበር (The Tigray Veterans’ Association;)

❑የገበሬ፣ የሴቶች፣የወጣቶች ማህበር (Farmers’, Womens’ and Youth Associations;)

❑ኮፕሬቲቨ (Co-operatives;)

❑ደደቢት የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲዩሽን ሼር ካንፓኒ (Dedebit Credit and Savings Institution Share Company (DECSI).

የክልላዊ መንግስቶች የንግድ ኢንተርፕራይዝ (Regional state-owned enterprise (RSOE) sector)

የኢህአዴግ ፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶችና ክልላዊ የልማት ድርጅቶች (Regional development organizations &  endowment-owned businesses)

ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተወረሱ የንግድ ድርጅቶች( endowment-owned businesses) በፓርቲዎች በስጦታ ወይም በችሮታ የተላለፉ የንግድ ድርጅቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲና ቢዝነስ (የንግድ ሥራ) እጅና ጎንት በመሆን የግሉን ዘርፍ ደፈጠጡት፡፡በህወሓት መንግስት የቢዝነስና ፖለቲካ ግንኙነቶች ከ1990እኤአ ጀምሮ በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተወረሱ ኃብቶች ኢፈርት በትግራይ፣ ጥረት በአማራ፣ ቱምሳ በኦሮሚያና ወንዶ በደቡብ ክልላዊ መንግስቶች ውስጥ እነደአሸን ፈሉ፣ የክልላዊ መንግስቶች የንግድ ድርጅቶች እየተንሰራፋ መጡ፡፡

የክልል መንግስታት የጋራ የንግድ ኢንዶንመንት ካንፓኒዎች (Joint endowment-linked companies)

የክልል መንግስታት የጋራ የንግድ ኢንዶንመንት ካንፓኒዎች ኢፈርት የትግራይ፣ጥረት የአማራ፣ ቱምሳ ኦሮሚያና ወንዶ የደቡብ የክልል መንግስታት የህብረት የንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡ እነሱም 1ኛ/ ወጋጋን ባንክ፣2ኛ/አፍሪካ ኢንሹራንስ 3ኛ/ሜጋ ፓብሊሽንግ 4ኛ/ ዋልታ መረጃ መዕከል 5ኛ/ ፋና ሬዲዩ ያካትታል፡፡

1ኛ/ ወጋጋን ባንክ፣(Wegagen Bank)

ወጋጋን ባንክ በ1997እኤአ ሲቆቆም  ኢፈርት 15 በመቶ  ሼር ነበረው፡፡የኢትጵያ ህግ አንድ ኢንቬስተር 5 በመቶ ሼር ብቻ መሸፈን እንዳለበት ህግ በመደንገጉ ኢፈርትና የሌሎቹም  ሼር 4 በመቶ ሆነ፡፡ በ2010 እኤአ ወጋጋን ባንክ 223 ሚሊን ብር ከታክስ በኃላ ትርፍና 23 በመቶ እድገት ማግኘቱን አስታውቆል፡፡  ወጋጋን ባንክ የተቆቆመበት የተከፈለ ካፒታል 633 ሚሊዩን ብር በመሆን በሃገሪቱ ካሉት ባንኮች ትልቁ መሆን ችሎል፡፡ ወጋጋን ባንክ 3.8 ቢሊዩን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሲሆን ብድር የማበደር  አቅሙ ስፊ መሆኑ  ይስተዋላል፡፡

2ኛ/አፍሪካ ኢንሹራንስ(Africa Insurance in the financial sector)

አፍሪካ ኢንሹራንስ ሁለተኛው የፋይናንሻል ዘርፍ ካንፓኒው ሲሆን በ2009/10እኤአ 19 ሚሊዩን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቶል፡፡ አፍሪካ ኢንሹራንስ 291 ሚሊዩን ብር አጠቃላይ ንብረት እንዳለው ተገልፆል፡፡ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ 15 ቅርንጫፍች አሉት፡፡ አፍሪካ ኢንሹራንስ 40 ሚሊዩን ብር ሼር በወጋጋን ባንክ አለው፡፡

3ኛ/ሜጋ ፓብሊሽንግ(Mega Publishing)

ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ ዋና ዓላማ በሃገሪቱ የአሳታሚነት፣የህትመት፣የመዝናኛና የማስታወቂያ  ስራዎች ከግሉ ዘርፍ ባለሃብቶች ሥራ እየተሸማ ዘርፍን ለመቆጣጠር በቅቶል፡፡ ሜጋ ኢንተርፕራይዝ ከፌዴራል የትምህርት ሚኒስቴር ብዙ የትምህርት ቤት መፅሃፍቶች እንዲያትም ያለጨረታ በማሸነፍ በዘርፉ የተሰማሩ ማተሚያ ቤቶች ከጨዋታ ውጭ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ለናሙና በደቡብ ክልል በሜጋ ታትሞ በህዝብ የተቃጠለው መፅሃፍት  በብዙ ሚሊዩን ብር ወጭ ወጥቶበት እንደነበረ ልብ ይበሉ፡፡ ሜጋ  ኢንተርፕራይዝ  በአዜብ መስፍን ዋና ስራ አስኪያጅነት ይመራ ነበር፡፡  ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ በ1995እኤአ በ13ሚሊዩን ብር ኩራዝ ፓብሊሽንግ ድርጅትን ከ35 መደብሮቹ ጋር እንደገዛ ልብ ይበሉ፡፡

4ኛ/ ዋልታ መረጃ መዕከል (Walta Information Centre (WIC)

ዋልታ መረጃ መዕከል፣አስቀድሞ ዋልታ የዜና ኤጀንሲ ይባል ነበር፡፡ በ1996 እኤአ ዋልታ መረጃ መዕከል በሜጋ ኢንተርፕራይዝ ሥር ተደራጀ፡፡ ዋልታ ብቸኛው የሃገር ውስጥ ተወዳዳሪ በመሆን የኢትዩጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ድርጅት በመሆን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዜናዎች በመሸጥ መተዳደር ጀመረ፡፡ ዋልታ መረጃ መዕከል፣ በመላ ሃገሪቱ መረቡን በመዘርጋት ሪፖርተሮቹን ሰየመ፡፡ ዋልታ በኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ በሼር ካንፓኒ የተቆቆመ ካንፓኒ ነው፡፡

5ኛ/ ፋና ሬዲዩ (Fana Radio in the areas of publishing and broadcasting)

ፋና ሬዲዩ የህወሃት/ኢህአዴግ ሬዲዩ በመሆን ጫካ እያሉ ያገለግል የነበረ በደርግ አገዛዝ  ዘመን የተቆቆመ የህወሃት የሬዲዩ ጣቢያ ነበር፡፡ ደርግ ከወደቀ በኃላ በሽግግር መንግስት ዘመን ፋና ሬዲዩ ስርጭቱን ቀጠለ፡፡ ፋና በሬዲዩ የግል ንግድ ዘርፍ ስርጭት ከሌሎች የግል ሬዲዩ ጋር ሆኖ ፍቃድ ተሰጠው፡፡  ፋና ሬዲዩ/ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ፕሮግራሞች በኮንትራት በመስራት ለተለያዩ ክልላዊ መንግስቶች ለሱማሌ፣ለኦሮሚያና ለአፋር በኮንትራት በመስራት ዳጎስ ያለ ጥቅም አገኘ፡፡  ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተወረሱ ኃብቶች ኢፈርት በትግራይ፣ ጥረት በአማራ፣ ቱምሳ በኦሮሚያና ወንዶ በደቡብ ክልሎች ውስጥ እየተንሰራፋ ይገኛሉ፡፡ የኢትዩጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የኢኮኖሚ እኩልነት በምን ላይ የተመሠረተ ይሆን!!! የተወሰኑ ብሔሮች ሌሎቹን ብዙሃኑን የሚበዘብዙበትና የሚጨቁኑበት ሥርዓት መተከሉን ማንም ህሊና ያለው የሚገነዘበው ነው፡፡ ለአለፈው ሃያ ሰባት ዓመታት፣ ኢፈርት የአንበሳውን ድርሻ ሲያገኝ፣ ጥረት ሙዳ ሥጋ፣ቱምሳና ወንዶ ቅንጣቢ ሥጋ የደረሳቸው ይመስላሉ፡፡ ለሌሎቹ የብሄር ብሄረሰቦች  ቀን በአመት አንዴ ይከበርላቸዋል፡፡

ክፍል ሁለት፡- ሁለተኛው ከ2010 እስከ 2012 ዓ/ም (ኦህዴድ፣ ኦዴፓ፣ ብልፅግና/ ኢህአዴግ ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን)  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ ባጫ ጊና  የፋይናንሻልና ባንክ ዘርፍ  የባንክ ብድር አሰጣጥ አድሎዊ የተረኛነት አሰራርን  ይገመግማል፡፡

ምንጭ

 1. ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር የወሰዱ የትዕምት ኩባንያዎች ዝርዝር (ኢልባ ዋና መስሪያ ቤት)
 2. በኢፈርት ስም ካፒታላቸው የሚታወቁ ድርጅቶች ውስጥ አብርሃ ደስታ ይፋ ያረጋቸው ካፒታላቸው የሚታወቅ የትዕምት ኩባንያዎች (“የመለስ ልቃቂት”ኤርሚያስ ለገሰ)
 3. በኢፈርት ስም ካፒታላቸው የማይታወቅ የንግድና ኢንዱስትሪ ድርጅቶች ውስጥ አብርሃ ደስታ ይፋ ያረጋቸው የትዕምት ኩባንያዎች (“የመለስ ልቃቂት”ኤርሚያስ ለገሰ)

4/28/2020

 

መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ (Mesfin Industrial Engineering)

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ (የህንፃ መሣሪያዎች ማምረቻ(Messebo Building Material Production)

አዲስ መድኃኒት/ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካ(Addis pharmaceutical factory)

አልሜዳ ጨርቃጨርቅ(Almeda Textile)

የአገልግሎት ዘርፍ (Services Sector)

ትራንስ ኢትዩጵያ (Trans Ethiopia)

ኤክስፕሬስ ትራንዚት ሰርቪስ (Express Transit Service)

ጉና ትሬዲንግ ሀውስ ኮንስትራክሽን(Guna Trading House Construction)

ሳባ ማርብል ፋብሪካ (Saba Stone)Saba Dimensional Stones

ብሩህ ተስፋ የመስኖና ውሃ ቴክኖሎጅ(Bruh Tesfa (Bright Hope) Irrigation & Water Technology)

ማጨው የችፑርድና ካንፔልሳቶ ፋብሪካ(Maichew Particleboard Factory)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.