ብልጽግና ሽኩቻ ላይ አይደለም (አሁንገና ዓለማየሁ)

ብዙ ከየዋህነትም በከፋ የፖለቲካ ድንቁርና ላይ ያሉ ሰዎች ብልጽግና እየተሻኮተ ነው የሚል ከንቱ ትንተና ሲሰጡ ይታያሉ። እርግጥ ተከፋይ ካድሬዎቹ ይህንን መሰል ወሬና ትንተና ቢያናፍሱ አይገርምም። ሥራቸው ለፖለቲካ ትርፍ ሕዝብን መሸወድ ነውና።

በምርጫ ዋዜማ የብልጽግና የተጠና የሽኩቻ ድራማ ዓላማው የብሔር ድርጅቶች ጥርቅም ከመሆኑ የመነጨ ነው። ብሔርተኛ ድርጅቶቹ እንወክለዋለን በሚሉት በየክልላቸው ሌላ የቀየሱት የሠለጠነ የምርጫ ቅስቀሳ ስልት ስለሌላቸው በዚያው በጎሰኛ ቅስቀሳ ልምዳቸው ነው የሚጠቀሙት።  ለሕዝቡ የሚያቀርቡለት ተጨባጭ የልማትም ሆነ የበለጠ ለማብራራት የኦሮሞ ብልጽግና ለኦሮሞ ተቆርቋሪ መስሎ ከኦነግ በላይ ኦነግ ሆኖ ለመታየት የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ያካሂዳል። የአማራ ብልጽግና ደግሞ መግለጫ ያንጋጋል። እሱም ተቆርቋሪ ለመምሰል። ሁሉም የወያኔ ምስለኔ አራጆች ስለነበሩ ለሚያልቀው ሕዝብ ወይም ነገ ለማይቀረው የበቀል እርምጃ ለሚያመቻቹት ሕዝብ ቁብ የላቸውም።  የብሔር ድርጅቶቹ አፈጣጠር ያው ስለሆነ ይሄው ስትራቴጂ በሱማሌም ሆነ በአፋር በሌሎቹም ሁሉ የብልጽግና ክንፎች በተመሳሳይ የፉገራ “ተቆርቋሪነት” እና ወገንተኝነት ድራማ እየመደረከ የምርጫ ቅስቀሳው (ወይም ጭፍጨፋው) ይካሂዳል። በጣም ብንወደውም ሙስጠፌም በዚሁ ስልት ተጠልፎ ይታያል። በግዕዝ ቅዳሴ መካከል በጀርመንኛ ማዜም አይቻልምና ሥርዐቱ ውስጥ የተነከረ ሁሉ በዚያው በሥርዐቱ ኦርኬስትራ ሊሳተፍ ግድ ይለዋል።

ስለዚህ ብልጽግና የተጠናና ከአፈጣጠሩ የመነጨ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እንጂ ሽኩቻ ላይ አይደለም። ሁሉም ለየመጡበት ክልል ነዋሪ ሌላ የሚያቀርቡለት የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተስፋ ስለሌላቸው ተቆርቋሪነታቸውን የሚገልጹበት የእልቂትና የለቅሶ ተውኔት ያቀርባሉ።

እግዚአብሔር ነቅተን ከዚህ ከሰው በላ ኋላቀርና ዘር ቋጣሪ ሥርዓት ራሳችንን ነጻ የምናወጣበትን ማስተዋል ይስጠን።

 

በምርጫ ዋዜማ
ሽኩቻዊ ድራማ
ለአንዲት ዓላማ

አንደኛው ከርስትህ ሲልክብህ አፍላሽ
ሌላኛው ድንበርክን ይመስላል አስመላሽ

አንደኛው ለማጽዳት ሲፈጅህ በሜንጫ
ሌላኛው ያወጣል “ነበልባል” መግለጫ
በብልጽግናዊ ቅስቀሳ ለምርጫ።

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.