“ወጣቱ ትውልድ በዓድዋ ላይ በደም ማኅተም የታተመውን አንድነት ጠብቆ ሀገርን የማሻገር ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል”

1

የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት – ዳኝነት አያሌው

“ወጣቱ ትውልድ በዓድዋ ላይ በደም ማኅተም የታተመውን አንድነት ጠብቆ ሀገርን የማሻገር ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል” የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ዳኝነት አያሌው

ባሕር ዳር፡ የካቲት 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ዳኝነት አያሌው በባሕር ዳር የዓድዋ የድል በዓል ሲከበር እንዳሉት የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በአይበገሬነት የሀገራቸውን ነጻነት በማስከበር ለአንድ ዓላማ የሚሰለፉ የኩሩ ሕዝቦች ሀገር መሆኗን ያስመሰከረችበት ነው፡፡ ትውልዱም ይህንን በውል ሊረዳው እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ዓድዋ በዓለም ላይ የጥቁር ሠራዊት በነጭ ላይ አምርቂ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመዘገበበት የታሪክ ቦታ ነውም ብለዋል፡፡ በዓለም ላይ የሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች ኢትዮጵያን ምስሌ በማድረግ ለመብታቸው እንዲቆሙም በር የከፈተ ነው ብለዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የዓድዋ ድል የመተባበርና የሕብረትን ጥቅም ከፍ አድርጎ አስተምሮ ያለፈ ክስተት መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ሰንደቅዓላማ በመውሰድም የራሳቸው አድርገዋል ያሉት ፕሬዝደንቱ ታሪክን በውል ያልተረዱና ጥቅም ፈላጊ አንዳንድ አካላት ኢትዮጵያውያንን በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በጎጥና በመንደር በጥላቻ እንዲተያዩ ማድረግ የለባቸውም ብለዋል፡፡ ይህም ከዓድዋ የድል ታሪክ ጋር የሚቃረን፤ ለታሪክም የሚመጥን አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘርን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አደረጃጃት ወገንን ከወገን የሚለያይና ሀገርን የሚያፈርስ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ወጣቶች ዘረኝነትን አጥብቀው ሊያወግዙ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መከባበርን፣ ለሉዓላዊነት ተቆርቋሪነትንና ሀገራዊ ስሜትን ወጣቶች ከዓድዋ ጀግኖች መማር እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡ “ወጣቱ ትውልድ በዓድዋ ላይ በደም ማኅተም የታተመውን አንድነት ጠብቆ ሀገርን የማሻገር ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል”ብለዋል፡፡

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ የዓድዋ የድል በዓል በከተማ አስተዳደሩ በልዩ ልዩ ክንውኖች ሲከበር የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጀግኖች አባቶች ለኢትዮጵያ ልዕልና የከፈሉትን መስዋዕትነት የአሁኑ ትውልድ በልማት መድገም እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የዓድዋ ድል በሰው ኀይልና በጦር ብዛት የተገኘም አይደለም ያሉት ዶክተር ድረስ ከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ሥራ በመሥራት ድሉን በልማት ለመድገም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

1 Comment

  1. The victory of Adwa was first and foremost the victory of the great Tegaru residents of Adwa, Tigray.
    Currently the victory of Adwa is being celebrated in mass breathing Covid-19 at each other’s throat in Addis Ababa and elsewhere so it might look like the victory Adwa is not the residents of Adwa’s victory as much as it is the other parts of Ethiopia, but this is just for the time being if you know what I mean.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.