“የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ያከተመለት ነው” (አቶ ቹቹ አለባቸው)

2
ሰሞኑን ደግሞ የትግራይ ብልፅግና እና የትግራይ ሊህቃን፣ወልቃይትና ራያ ወደትግራይ ይመለሱ ማለታቸዉን ተከትሎ ፣ በአማራ አክቲቢስቶችና ሊህቃን ጠንከር ያሉ ምላሾች እየተሰጡ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
ይገርማል! የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፤የትግራይ ብልፅግና እንደ አጠቃላይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ፥ወልቃይትና ራያን ወደ አማራ መጠቃል በፀጋ ይቀበሉታል ብሎ ራሱን ያታለለ አማራ አለ ማለት ነዉ? እንዴት ነዉ ነገሩ ጎበዝ?
ለሁሉም እኔ እንደማምነዉ ህወሀት የአማራን ህዝብ በጠላትነት የፈረጀ ድርጅት ነበር። ይሄንን የጠላትነት አመለካከት የማይደግፍ የትግራይ ብሄር አባልና ሊህቃን ይኖሩ ይሆናል ብየ አስባለሁ። ነገር ግን ሁሉም የትግራይ ህዝብ ፣ሊህቅ በለዉ ሌላ በወልቃይትና ራያ ጉዳይ አቋሙ አንድና ወጥ ስለመሆኑ መጠራጠር አይገባም። ስለሆነም ከነዚህ የአማራ ህዝብና መሬት / አካባቢወች አንፃር ፤አንድም የትግራይ ተወላጅ የአማራን ፍትሀዊ ጥያቄ ይቀበላል ብሎ መጠበቅ ጅልነት ነዉ። ስለዚህ በዚህ በኩል የሚመጣ ነገር አስደንቆን ልናጮኸዉ አይገባም እላለሁ። ምክንያቱም እነሱ የሚሉትና የሚሰሩት ማለትና መስራት ያለባቸዉን ነዉ።
አሁን ጥያቄዉ የትግራይ የፖለቲካ ሀይሎችና አጠቃላይ የትግራይ ህዝብ፤ ወልቃይትና ራያን በተመለከተ ማለት ያለባቸዉንና መስራት ያለባቸዉን እያሉና እየሰሩ ከሆነ፤የአማራ ፖለቲከኞችና የአማራ ህዝብስ ከዚህ ጉዳይ አኳያ ምን እያልንና እየሰራን ነዉ? የአማራ ሀይል መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ ይህ ነዉ። በተለይም የሚከተሉትን ጥያቄወች እንመልስ:+
1. ወልቃይትና ራያ ምድር ላይ የተሰራዉ አደረጃጀት ምን ያክል ጠንካራ ነዉ?
2. በየ አካባቢወቹ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ እንዴት እየሄደ ነዉ? ቅሬታወች አሉ? እንዴት ተፈጠሩ ? ካሉ እንዴት እየተፈቱ ነዉ?
3. የህዝቦች ሰላምና ደህንነት እንዴት እየተረጋገጠ ነዉ?
4. አሁን በተዘረጋዉ አስተዳደር የየ አካባቢዉ ህዝብ ምን ያክል ደስተኛ ነዉ? ወጣቱን ምን ያክል በሀሳብ ይዘነዋል?
5. የየ አካባቢዉ ህዝብ በተለይም ወጣቱ በመሰረታዊ ጥያቄወቹ ዙሪያ ጠንካራ አቋም ላይ ደርሷልን? ምን አይነት ጥያቄ/ቅሬታ አለዉ?
ከላይ ያነሳሁዋቸዉ ጥያቄወች በጤናማ ሁኔታ ካሉ ችግር የለም። ካልሆነ ግን.በዋነኛነት ዉዝግቡ የሚነነሳዉ ከትግራይ ወገን ሳይሆን ፤በራሳችን መካከል መሆኑ አይቀሬ ነዉ። ምክንያቱም በህወሀት አገዛዝ የኖሩት የወልቃይትና ራያ አማራወች ከነበሩበት የህወሀት የአገዛዝ ዘመን፣ በተሻለ ሁኔታ በብልፅግና ዘመን የበለጠ ሰላም፤ልማትና ዴሞክራሲ ተረጋግጦላቸዉ ማየት መጠበቃቸዉ አይቀሬ ነዉ። አሁን ጥያቄዉ ለነዚህ አካባቢወች ከህወሀት ዘመን የተሻለ ሁለንተናዊ ልማት የምናረጋግጥ መሆናችንን የማሳየትና ያለማሳየት ጉዳይ ነዉ። ከቻልን ቀሪዉ ነገር ገለባ ነዉ፤ካልቻልን ግን ዋነኛዉ ጠባችን ከትግራይ ህዝብና የፖለቲካ ለይሎች ጋር ሳይሆን ከራሳችን ጋር መሆኑ አይቀርም። ምክንያቱም የትግራይ ብልፅግናም ሆነ ፖለቲከኞች እንዴዉ ለማለት ያክል እንጅ ወልቃይትና ራያን ወዲህ በሉ የሚሉት፤ የወልቃይትና ራያ እህል ዉሀ ከትግራይ ጋር እስከወዳኛዉ የተፋታ ስለመሆኑ ከቴዉንም ዘንግተዉት አይደለም። ብቻ ግን ማለት ስላለባቸዉ ይላሉ፤ከነሱ አንፃር ደግሞ ልክ ኔቸዉ።
ሰለዚህ ወልቃይትና ራያን በተመለከተ እከሌ እንዲህ አለ፤እከሊት እንዲህ አለች እያልን ነገር ሰናንገላዉድ ከምንዉል ዝም ብለን መሬት ላይ ያለዉን ስራችንን እንሰራ!

2 Comments

  1. woyane invaded and controlled wolkait-tegede mainly to gain access to sudan , so that it can smuggle weapons through the border . secondly, woyane needed to gain access to sudan to get its wounded tegadalay treated in sudan. Sudan was also seen as a safe place to run to if woyane needed to retreat if it got attacked by the ethiopian army.
    At the beginning when woyane started its guerrila war , shabia was supplying the access routes to sudan via Tessenne to Kassala in sudan that woyane neede. When the two groups split because of disagreements, woyane bandits invaded wolkait -tegede and opened up access route to sudan. Gradually they controlled the whole region by force. That is how they made Wolkait-tegede part of tigrai, which they consollidated after they took power in Ethiopia.
    Wolkait tegede has never been and will never be part of tigrai.

  2. ወልቃይት እና ራያ የትግራይም የአማራውም ሳይሆኑ የሚኖሩበትን ሁኔታ እንደ አማራጭ መጠቀም አይቻልም ወይ።ምርጫውን ለነዋሪው ብንተወውሳ።ለምን አገር ስለምትቀድም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.