የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለበትን ሕጋዊ ሓላፊነት እና ግዴታ ይወጣል-የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ

1
የኢፌዴሪ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለበትን ሕጋዊ ሓላፊነት እና ግዴታ እንደሚወጣ፣ እየተወጣም እንደሚገኝ ማረጋገጫ እንደሚሰጡ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ።
ሰብሳቢዋ ይህንን ያሉት ለፓርቲዎች አመራር አባላት፣ የፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች እና በግላቸው ለሚተሳተፉ እጩዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ነው።
ሰብሳቢዋ በመልእክታቸው ለ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በእጩነት ስትመዘገቡ ወይም እንደ ፓርቲ እጩዎቻችሁን ስታስመዘግቡ ከፊታችን ያለው መንገድ ከፊል ተስፋ፣ ከፊል ስጋትን አዝሎ እንደሚጠብቃችሁ፣ እንደሚጠብቀን ለሁሉም ግልጽ ነገር ይመስለኛል ብለዋል።
ይሁንና ስጋትን ለመቀነስ ብሎም ወደ መልካም ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችለን አቅም እና እድል በየፈርጃችን ይዘን ይህን የጋራ ሙከራችንን በዝለት ሳይሆን በጥንካሬ ልንጀምረው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
በቀደሙ ምርጫዎቻችን ባልነበረ ሁኔታ የሂደቱን ዋና ተዋናዮች ማለትም ተፎካካሪዎቹን ግራ ወይም ቀኝ፣ ትንሽ ወይም ትልቅ፣ አገራዊ ወይስ ክልላዊ ሳይል፣ በጥረታቸው ሊያግዝ እና ሳንካቸውን ሊፈታ የተዘጋጀ፣ አቅሙን የጨመረ፣ የገለልተኝነቱን መጠን እና ስፋት ከተፅዕኖ ሁሉ የሚከላከል የምርጫ ቦርድ ሂደቱን እያስተዳደረ ይገኛልም ብለዋል።
በፍትሐዊነት በተቃኘ በጎ ሐሳብ ሳይሆን በሸፍጥ፣ ሌላውን በማክበር ሳይሆን ማንኛውንም መንገድ ተጠቅሞ በእንጻሩ የቆመውን በማጥፋት ባለመ ሐሳብ፣ የሁሉንም የዜጐችን ሐሳብን የመግለጽ ሰላማዊ ዕድል ሳይሆን ኋላቀር የሆነ ግጭታዊ መስተጋብርን ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫን ያሰበ ተወዳዳሪ ቢኖር፣ ይህን ከምርጫ ፖለቲካ ውጪ የሆነ ሥራውን ለአደባባይ አውጥተው ለሰው ዓይን እና ጆሮ ሊያደርሱ የሚችሉ በቁጥር ትንሽ የማይባሉ የሚዲያ አውታሮች እንደ አገር ያለን መሆኑም ለተሻለ ሽግግር ወደፊት ለመቀጠል የሚያስችል አንድ በጎ እውነታ ነው በማለት ተናግረዋል።
የሲቪል ማኅበራቶቻችንንም አናቂ ይባል ከነበረ የሕግ ማእቀፍ ወጥተው ዜጐችን ስለ እውነተኛ ምርጫ ሊያሳውቁ እንዲሁም የምርጫ ሂደታችን ጉበኛ ሆኖ በታዛቢነት ለማገልገል በጣት በሚቆጠሩ ሳይሆን በመቶዎች በሚቆጠሩ አደረጃጀቶቻቸው ላይ መሰናዶአቸውን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የአውሮፓ እና የአሜሪካ ታዛቢዎችም ይህን ለአገራችን ትልቅ ትርጉም ያለውን ኩነት በእንግድነት ሊታዘቡ ከመንግሥት ግብዣ ደርሷቸው ከእኛ ጋር የሂደቱ አካል ሊሆኑ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ነው መሆኑን አመልክተዋል።
ብዙ ሌሎች የምርጫ ማሻሻያችን ብዙ ጎኖች መጥቀስ ይቻላል ብለዋል-የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ።
በመጨረሻም ፓርቲዎች በአገራችን የተለያየ አካባቢ እጩዎችን በማስመዝገብ፣ በእጩነት በመመዝገብ የምርጫ ዘመቻውን ምእራፍ ስትከፍቱ ለሂደቱ የሚጠቅም በጎ እሴት ለመጨመር፣ በችግር ፈቺነት በጋራ ለመሥራት፣ የፖለቲካ ጥቃትን አሮጌ ባሕል ዕለት ዕለት ለመተው፣ ለዘመናዊ እና ሥልጡን ውድድር ራሳችንን ለማደስ፣ ከምንም በላይ የዜጐቻችንን ባለሥልጣንነት በማክበር እንዲሆን ጠይቀዋል።
በዚህ አስፈላጊ እና ትልቅ ትርጉም ባለው ሥራ የሁላችንንም አብሮነት እና የእያንዳንዳችንን ድርሻ ሳንረሳ በበጎ መንፈስ የምርጫ ውድድሩን እንጀምር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

1 Comment

  1. It is very hard to expect tangible solutions from the Woyane/EPRDF cadres. Bertukan Mideqsa was hand-picked by Meles, the brutal dictator, to become a senior judge, without any experience. According to sources, her demise was related to her personal relationship with Siye. Then the abolition of the Hibret. Then the formation of Kinijit. Then her exile to America, the CIA land, for preparation for another round of suppression under the OLF domination. Now the head of the Election Board. What election? How can you arrange any fair election a) without free movement throughout the country, b) while genuine party leaders and members are sent to jails to deny them chances of participation in the so called national election, c) all institutions are under the control of the regime, from the Federal, Regional, Zone, Woreda and Kebele levels???? I am so worried about their dangerous actions at national, regional, Addis Ababa and local levels.
    Wake up Ethiopia people. Don’t be victims of ‘Hod Aderoch’ and fight for unity and genuine democracy.
    Struggle for personal

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.