በጀርመን የገባውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ያለው ቴከኒካዊና ተቋማዊ ልምድና አስተያየት – ክፍል 12

Medical masks shielding on a white background with clipping mask.

ለተከበራቹህ ወገኖች                                                                           

የኮሮና ልምድ ከጀርመን – የከረርው ሎክዳውን እና የህክምና ማስክ ግዴታ    19.01.2021

ካለፈው በመቀጠል በዛሬው ዕለት የጀርመን መንግስት ቻንስለር ክብርት አንጌላ ሜርክል ከፌዴራል መንግስታት ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር በመመካከር ከዚህ በፊት በ10ኛው እና በ11 ኛው ገለፃ አቅርቤ የነበርውን የከረርው ጥብቅ ሎክዳውን በማራዘም እና ተጨማሪ ግዴታዎችን በመወሰን እስከ የካቲት 15 ቀን 2021  የሚቆይ እርምጃ እና ሎክዳውን ጥለዋል።

በቀን ከ20ሺዎቹ በላይ የነበርው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትም በዚህ ሳምንት በመጠኑ ቀንሶ ወደ 10ሺዎቹ ገብቷል። ቢሆንም የሟቾቹ ቁጠር በቀን ከ1ሺ በላይ ወይም ወደ 1ሺ የሚጠጋ መሆኑን አላቋረጠም።

  1. የህክምና ማስኮች ግዴታ ከ21.01.2021 ጀምሮ 

በመገበያያ ቦታ እና በትራንስፖርት ወቅት የህክምና የአፍና አፍንጫ መከላከያ መጠቀም ብቻ በመላው አገሪቱ አስገዳጅ ነው። የህክምና የአፍና አፍንጫ መከላከያ የሚባሉት (በጀርመንኛ OP-Mask) ወይም (በአንግሊዘኛ surgical mask /medical face mask) እና KN95 ወይም FFP2  የሚባሉት የአፍና አፍንጫ መከላከያ  ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ናችው። KN95 / FFP2  የሚባለው ወደፊት ሾጠጥ ያለ  በአብዛኛው ነጭ ቀለም ያለው ማስክ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች የፊት ማስክ (OP-Mask) የሚባለው ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚሆን በአብዛኛው የሚታወቀው ሰማያዊ ቀለም ያለው ማስክ ነው። በእርግጥ አረንጓዴ፣  ሮዛ፣ ጥቁርም ቀለማት ያላቸውም ይገኛሉ።

  1. የሥራ ቦታ Home Office (HO)

አሠሪዎች በኩባንያዎች ወይም በተቋማት ለሰራተኞቻቸው የቤት የስራ ቦታዎችን Home Office በአስቸኳይ እና በተጠናከረ መልኩ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል።

  1. ክትባት

እስከዛሬ በ23 ቀናት ውስጥ ወደ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። ይህም ዝግተኛ አካሄድ እንደተጠበቀው ሊፈጥን አልቻለም። ምክንያት ሆኖ የቀረበው የክትባት መጠን በተጠበቀው ብዛት አለመመረትን ነወ።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩት ምስሎች እንደጀርመን የሎክዳውን አገር ውስጥ ለተቀመጠ ሰው እጅግ ግራ የሚያጋቡ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኝ ጠፋ እንዴ የሚያስብል ነው። ስለኮሮና መከላከል ሲወራ የነበረው የተረሳም የሚያስመስል ነው። የባህሪይ ለውጥም አይታይም።  ስርጭቱ እንደቀነሰ ብቻ አንዲቆይ ተስፋ ከማድረግ በስተቀር ተመክሮ የሚጠቅም አይመስልም። በተለይም ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ በሚሰብስባቸው ቦታዎች እጅግ ጥቂት ሰዎች ብቻ ማስክ አድርገው አብዛኛውን ያለማስክ ማየቱ ማስክ የማድረግ ወይም ያለማድረጉ ትርጉሙ ግራ ያጋባል። አሁን ያለው ምክር  ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ እንዲጠብቃቸው እና እንዳይስፋፋ ተስፋ ማድረጉ ላይ ነው።

መልካም ጥምቀት!

                                               ትልቁ አደጋ የሚከሰተው ሰው አሸንፊያልሁ ብሉ ሲዘናጋ እና ሲዝናና ነው።

–      ሱን ሱ (The Art of War)

ከመልካም የጤንነት ሰላምታ ጋር
ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

——-

Dr. Tsegaye Degineh


Berlin, Germany
—–

Email: mail@degineh.de,
Website: www.degineh.com

—–

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.