ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ

የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ ብራሰልስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ13 ዓመታት በሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን አሻሻለ፡፡

በትውልድ ሶማሊያዊው የሆነው ሞ ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው በኃይሌን ተመዝግቦ የነበረውን 21 ነጥብ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው፡፡

የ37 ዓመቱ ሞ ፋራህ የውድድሩን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጠው አስተያየት የዓለም ክብ ረወሰን መስበር ከባድ መሆኑን አንስቶ ትናንት የተወዳደረበትም ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር መቆየቱን አንስቷል፡፡

ፋራህ ከማራቶን ከተመለሰ በኋላ ያስመዘገበው በመሆኑ በውጤቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ሞ ፋራህ ክብረ ወሰን በያዘበት በዚህ ውድድር ተወዳዳሪዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚያስመዘግቡት ርቀት ነው የሚያዘው፡፡

በሴቶች ኔዘርላንዳዊቷ ሲፈን ሐሰንም በተመሳሳይ በትናትናው ዕለት ክብረ ወሰን አሻሽላለች፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን በአንድ ሰዓት ውስጥ 18 ነጥብ 930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው ከ14 ዓመታት በኋላ ያሻሻለችው።

ከዚህ ቀደም ክብረ ወሰኑ ድሬ ቱኔ በ18 ነጥብ 517 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነበር ያስመዘገበችው።

ኤፍ.ቢ.ሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.