ዶክተር ዐቢይ ኢትዮጵያችንን ወዴት እየወስዷት ይሆን?

4

ሐምሌ 20 2012 / July 27 2020

በ1980ዎቹ በቀድሞው ሶቭየት ህብረት ተማሪ ነበርኩ። በውቅቱ ፕሬዜዳንት የነበሩት ብሬዝነቭ   በዕድሜአቸው የገፉ አንጋፋ ሰው ነበሩ። ብርዥነቭ ከእርጅና ጋር በተያያዘ ህመም ሲሞቱ የKGB  የስለላ ድርጅት መሪ የነበሩት አንጋፋው አንድሮፖቭ  በቦታው ተተከትው የመሪነቱን ቦታ ያዙ። አሳቸውም በዕድሜ የገፉ ስለነበር በተመረጡ በዓመቱ ሞቱ።ከዚያም ሌላው የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባል የነበሩት አንጋፋው ቸርኒንኮ ፕሬዜዳንት ሆነው የተመርጡ ቢሆንም ብዙ ሳይቆዩ በ13 ወራት በሥልጣን ላይ እንደቆዩ  አረፉ።  ከዚህ በኋላ ዕድሜው አንጋፈ ያልሆነ መመረጥ እንዳለባቸው ተነጋግረው በውቅቱ  በመካከላኛ የዕድሜ ገደብ የሚገኙትን ሚካኤል ገርቫቾብን በፕሬዜዳትነት እንዲመረጡ ተደረገ።

ወቅቱ የሶሻሊስት አገሮች ኢኮኖሚ የተዳከመበት፤ አባል የነበሩ አገሮች ከፍልስፍናው እየራቁ የመጡበትና በሶሻሊስት አገርች መካከል የነበረውም የኢኮኖሚ መደጋገፍ/ ህብረት  WARSO /እየላላ የመጣበት ጊዜ ነበር።

በአንጻሩ የካፒታሊስት አገሮች ኢኮኖሚ ጠንካራ ስለነበር ይህን የተረዱት ሚካኤል ገርቫቾብ አገራቸውን ከአውሮፓ አገሮች ጋር በኢኮኖሚ በማስተሳሰር የአውሮፓን የበላይነት ማስጠበቅ የቻላል በሚል የግላቸውን አመላካከት ከወቅቱ የዓለም ተጨባጭ  ሁኔታ ጋር ሳያገናዝቡ “ፕሪስትሮይካ በጥልቀት መታደስ/ deep transformation” በሚል ፍልስፍና ተነሳስተው የአገራቸውን ኢኮኖሚ ለማሻሻል ግልጽነትና ተጠያቂነትን የፕሮግራማቸው ማስፈጸሚያ በማድረግ ሥረዓቱን ለማሻሻል ደፋ ቀና ማለቱን ተያያዙት ።  ከአሜሪካና ከአውሮፓ አገሮች ጋር ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ለማለዘብና ኢኮኖሚውን ለማዘመን ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ።

ዓላማቸው አወሮፓን የኢኮኖሚ አጋር አድርገው አገራቸውን ለማስቀደምና አሜሪካ በአውሮፓ ላይ ያለውን ተጽኖ ላማዳከም አቅደው መንቀሳቀስ ጅመሩ። የአሜሪካ የመረጃ ኤጅንሲ CIA እና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች ደግሞ የተከፈተውን ቀዳዳ በመጠቀም የሶሻሊስት ኅብረት አገራቱ እንዲበታተኑ ከራሻ ሪፓብሊክ ጋር ያላቸውን አንድነት እንዲአቋርጡ ወስጥ ውስጡን መቀስቀስ ሥራየ ብለው ተያያዙት።በተለይም የራሻው ሪፓብሊክ መሪ የነበሩት የልሲን ታላቋን ራሻ ገንጥለው መሪ ለመሆን የነበራቸው ፍላጎት ያጤነው ኃይል በአደርገው ስውር ድጋፍ  ለገርቫቾብ መንግሥት ትልቅ ራስ ምታት ሆኑባቸው ።

 ከዚያም የውጭው ግፊት እያየለና እሳቸውም በየጊዜው ከየልሲን ጋር ያላቸውን አለመግባባት ከቁጥጥራቸው ውጭ ከመሆኑ በፊት ፈጥነው ማሰተካከል ባለመቻላቸው መጀመሪያ ሶስቱ ባልቲክ አገሮች ከዚያ ሌሎች የሪፓፕሊኩ አባል አገራት መገንጠል ሳይፈልጉ በነቦሪስ የልሲን ገፊነት ተናንሽ ነጻ መንግሥት መስርተው የ15 አገሮች ጥምረት “ታላቁ ሶቭየት ኅብረት “ የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

እንዲያ ዓለም በሁለት የፋልስፍና አመለካከት ተከፍሎ እኔ እበልጥ እኔ አሸንፍ በሚአካሄዱት ፍጥጫ ሚዛን አስጠባቂ በመሆን ያገለግል የነበረው የሁለት ዓለም ጎራ ታሪክ ሆኖ ቀረ። የራሳቸውን አገር የራሻ ሪፓፕሊክ መሪ የነበረውን የልሲንና የውጭ አገራትን አገር አፍራሽ ተጽኖ መቆጣጠር ሲገባቸው ባሳዩት ዳተኛነትና ቸልተኝነት ገርቫቾብ አገር አልባ መሪ ሁነው ለሶቭየት ኅብረት መፈራረስ ምክንያት በመሆናቸው በአሜሪካን አገር ስደተኛ ሁነው ይኖራሉ።

እንደዚያ ተከብራና ተፈርታ የነበረችው ዓለምን አንድ ጎራ ወክላ የምትገዳደር ትልቅ አገር ዛሬ እንዲህ በሚአስገርም ሁኔታ ተበታትና በመንግሥት ይዞታ የነበረው የሕዝብ ሀብት ለጥቅት ግለስብ /እንደ ወያኔ  ላሉ/ መበልጽጊያ ሆኖ  የከርሰ ምድር ተፈጥሮ ሃብቷን  እይቸበቸበች የምትኖር አገር ሆነች ። አልፎ ተረፎ ቀድሞ የዛሩ ንጉሥዊ  አጋዛዝ ጀምሮ በራሻ ስር የነበረችውን ክሪሚያ ሶሻሊስት በነበሩበት ወቅት በዩክሪን ስር እንድትተዳደር በመደረጉ ይክሪየኖች የአውሮፓ የኢኮኖሚ ኅብረት ለመቀላቀል ጥያቄ ሲያቀርቡ፤

የፑቲን አስተዳደር ሌሊቱን ክሪሚያን ወሮ በቁጥጥር ስር በማደረጉ ያጋጠማቸው የአሜሪካና የአውሮፓ አገራት ንቀት የተሞላበት ውግዘትና  የተጣለባቸው የኢኮኖሚ መአቀብ  ያናዳዳቸውና ያስቆጫቸው ፕሪዜዳንት ፑቲን ቀድሞ ያስክብራቸው የነበረው ኃያልነት ከሕዝቡ ቁጥር መቀነስና የአጋር አገሮች መፍረስ ጋር በተያያዘ የተከሰተ በመሆኑ “ እኛ ራሻኖች የሠራነው ትልቁ ስህተት ቢኖር የነበረነን የሪፓፕሊኩን ጥምረት ማፍረሳችን ነው” ሲሉ ነበር የተናገሩት።

  እናማ ይህን የቆየና የተረሳ ታሪክ እንዳነሳ ምክንያት የሆነኝ  የአገራችን የኢትዮጵያ ሁኔታና ለውጡን ተግባራዊ ለማድረግ እየሄድንበት ያለው ጉዞ ከላይ የገለጥኩትን የሶቭየት ኅብረት አገሮችን እንዲበታተኑ ከአጋጠማቸው ሁኔታ ጋር ተቀራራቢና ተማሳሳይ መስሎ ስለታየኝ ስጋቴን ላካፍላችሁ መሪአችንም ለማሳሰብ ነው።

ሁላችንም እንደምናውቀው በከፍተኛ መስዋአትነት የተገኘውን ለውጥ ሊአሻግሩን ቃል የገቡልን ዶክተር ዐቢይና የሚመሩት የቀድሞው ኢሕአዴግ “ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ“ በሚለውና የመደመርን ፍልስፍና እያቀነቀነ አንድ ወጥ በሚመስል ወደ” ብልጽግና ፓሪቲ” የመጣበት የሁለት ዓመት ጉዞ በበጎ መልኩ የሚታዩ ተጨባጭ ተግባሮችን ማካናወኑ ብዙዎቻቻን ልንመስክር የምንችለው ሐቅ ነው።

 በአንጻሩ ጽንፍ የረገጠ የጎጥ አመላካከት የሚአቀነቅኑ ዞጎኞች በተለይ የኦሮሞና  የወያኔ ባለሥልጣናትና ሆድ አደር ባንዳ ተከታዮቻቸው እንዳሻችሁ ተብለው ያለበቂ ሃይ ባይ ዝም ስለተባሉ የሕዝባችን ድህንነትና የአገራችን ሰላም ከመቸውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ፈተና ላይ የወደቀበት ጊዜ ሆኗል።  

 አስካሁንም ከአንድም ሁለት ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ ከፍተኛ የአገር ንብረት እየወደመና የበርካታ ንጹሃን ዜጎቻቻን ሕይወት መስዋአትነት እየተከፈለ የአገሪቱን ለአላይነት ለማስጠበቅ ሲባል ትግሥት በተሞላበት ሁኔታ የመንግሥትን ዳተኝነትና ቸልተኝነት አይቶ እንዳላየ አገር ትበልጣለች በሚል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አቋሙን ሳይለውጥ ከዶክተር ዐቢይ ጎን ተሰልፎ ድጋፉን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሆኖም እነዚህ ጽንፈኛ የዞግ አቀንቃኞች የመንግሥትን ትግሥት ከፍራቻና ከአቅም ማነስ የመነጨ አድርገው በመቁጠራቸው ከእኩይ ተግባራቸው ሊቆጠቡ  አልቻሉም።ይህ በዕብሪተኞችና በውጭ አገር ጠላቶቻቻን ሰውር ድጋፍ የሚካሄድ ጥቃት ከእንግዲህ በኋላ በቃህ ሊባል ካልቻለ እኛ ፈርሰን ከአለቅን በኋላ አገራችንን ከመፈረስ ማዳን ስለማንችል፤ እኛም አገራችንም እንዳትፈርስ ቆራጥ አመራር እንሻለን።

 ስለዚህ እየሆነ ያለውንና  መንግሥት መውሰድ የገባዋል የምላቸውን ሀሳቦች እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

 እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት ለተድጋጋሚ ጊዚያት ወያኔ፣ ኦነግና መኖሪያቸውን በውጭ አገር ያደረጉ ጥቂት የኦሮሞና የትግራይ ተወላጆች በሰላምና በአብሮነት የሚኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በብሔርና በጎጥ በመከፋፈል ተነሳ ግደል፣ ንብረቱን ዝረፍና አቃጥል በሚል በአማራና በሌሎች ብሔር ብሔረስብ ላይ የሚአደርጉት የዘር ማጥፋት ቅስቀሳና ዘመቻ በተደጋጋሚ ጊዜ በኦሮሞ ክልል ተብየ በሚኖሩ አማራዎችና ሌሎች ብሔረሰቦች ላይ ተካሄዷል።

ይህን በተጠናና በተደራጅ ሁኔታ ዘር እየተመረጠ የሚካሄድ ጥቃትና ግድያ  የአካባቤ ባላሥልጣናት ፖሊስ፣ሰላም አስጠባቂ ሚሊሻና መከላከያ በቦታው ተገኝተው መታደግ ሲገባቸው ከፊሉ ቁሞ ተመልካች፣ አንዳንዶችም የድርጊቱ ተባባሪና አለቆቹ ደግሞ አልታዘዝኩም በሚል ስንካላ ምክንያት ዝምታ በመምረጣቸው ከየቦታው ተሰባሰበው በመንጋ የሚጓዙ ሽብረተኞች ዋና ከተማ  አዲአ አባባ ሳይቀር በሌሊትና በቀን እየለዩ የሌሎች ጎሳዎችን ሕይወትና ንብረት እንዲጠፋ ተደርጓል።

 በተለይ ነፍጠኛ አማራ እያሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኋላ ግዳይ እንደጣለ ጅግና ሲጎማለሉና ከአውሬነት በአነሰና በወረደ ደረጃ  በዜጎቻችን ሬሳ ላይ አሰቃቂና ዘግናኝ ድርጊት ፈጽመው በሰላም ወደ መጡበት እየፎከሩ ሲመለሱ ይህ ነው የተባለ አስተዳደራዊ እርምጃ በለመወሰዱ እንዲያውም የዞግ ፖለቲካ ቱሩፋት “ አንዱን መጤ ሌላውን ባለአገር “ የሚአደርግ ትርክት ለወንጀለኞቹ ሕጋዊ ሽፋን ስለሰጣችወ የድርጊቱ ተዋናዮች “ የመንጋ ስብስብ” እየተመላላሱ እንዲአጠቁ አጋጣሚዎን ሲጠቀሙበት ይስተዋላል ።

 የችግሩ ቀስቃሾች አገሪቱን ወደ ከፋና ማባሪያ ወደ ለለው የእርስ በእርስ ጦርነት ለመማገድ በተለይ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ልዩነቱን የዘር ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ ሃይማኖታዊ ባህሪ እንዲይዝ አድርገውታል። በአካባቢው የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተካታይ ምዕመናን እየተመረጡ እንዲገደሉ፣ አባያተ ክርስቲያናትን እንዲቃጠሉና ንበርትም እንዲወድም ሲደረግ ሌላው ወገን መንግሥት አለኝ ውይም ይከላከላል በሚል የአገሩን አንድነት በመሻት ዝምታን በመምረጡ እንደፍራት ተቆጥሮ በተደጋጋሚ ለጥቃት ተዳርጓል።

 መንግሥት በተለይ የዶክተር ዐቢይ በፕሬዜዳንትነት የሚመሩት የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አባላት አብዛኛዋቹ ከወያኔ ጋር በሙስና የተዘፈቁና ከፊሎቹ ደግሞ የኦነግ ተካታዮች በመሆናቸው በተግባር ላይ የሚአሳዩት ኢትዮጵያዊነትን ያላማከለ፤ የአንድ ወገን የበላይነትና ተጠቃሚነት ያስቀደመ፤ አድሏዊ አሰራር  ሠራ ላይ እየተተገበረ ስለሆነ ከወዲሁ ለማስተካካል ካልተሞከረ የሕዝብን አሜኔታና ቅቡልነት አጠያያቂ እያደረገው መምጣቱ አይቀሬ ነው።

   በትግራይና በኦሮሚያ ከልል ተብየ የሚካሄደውን ሕዝብን ከሕዝብ ለማለያየት ዘር ተኮር የውሸት ቅስቀሳና  ብሎም ጎሳና ሃይማኖት ለይቶ እርስ በእርሱ እንዲጨፋጨፍ ሌት ተቀን ሥራ ጉዳየ በለው የሚነቀሳቀሱ የመገናኛ አውታሮች ፣ድርጅቶችና ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥፋት እያጠፉ አድሏዊ በሚመስል መንገድ በዝምታና በማማባል መታለፋቸው እራሳቸውን ከሕግ በላይ በመቁጠር ከመንግሥትና ከሕዝብ በላይ አግዝፈው እንዲያዩ አድርጓቸዋል።

  መንግሥት በራሱ እየተከተለ ያለው  ፊድራሊዝም እራስን በራስ የማስተዳደር ዘይቤ የሕዝቡን አብሮነት ግምት ውስጥ ያላስገባ አንድ ሰው ከብዙ ቦታ ይወለድ ይመስል እትብቱ የተቀበረበትን ወይም  የተወለደበትን መንደር አያት ቅድመ አያቱ ከአስረከቡት አገሩ ላይ መኖር የማያስችል መጤ የሚአስብለው ሆኗል። እንደዚህ ያለ ማንነትን ሰጭና ከልካይ ሥረዓት መስርቶ የሁላችህ መሪ ነኝ ቢባል  በዘርና በጎጥ የተቃኘ አመራር እስካልተወገደ ድረስ ድምጹን ላልሰጠው ሕዝብ በእኩልነትና ያለአድሎ ያስተዳድራል ተብሎ ሊታመን አይችልም።

ከ30 ዓመታተ ጀምሮ እስካሁን ድረስ እየታየ ያለው እውነታም ይህው አድላዊነቱ ነው። “ክርስቶስ ለስጋው አደላ “ ዓይነት ስለሆነ  ይህን የዘር ፖለቲካ እርስ በእርሳችን ተበላልተን ከመጨራረሳችን በፊት በሕግ አምላክ ሊአስቆሙልን ይገባል።

የህዳሴውን ግድብ መገንባትና ብሎም በውሃ መሙላት ተከትሎ  የግብጽ መንግሥት በአገራችን ላይ የውጭውን ዓለም ድጋፍ ለማገኘት በዲፖሎማሲዊ፣ በፖለቲካዊና በሃይማኖት ረገድ ተጽኖ ለማሳረፍ የምትሯሯጥበት ወቅት መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። እነዚህ ጽንፈኛ የዞግ አቀንቃኞች ደግሞ የአገርን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት የሚአገኙትን የገንዘብ ዳረጎት እንዳይቀርባቸው ከግብጽ ጎን በመቆም ሰሞኑን በኦሮሚያ በሚኖሩ አማራዎችና ሌሎች ብሔረሰቦች ላይ የተፈጸመው  ሽብርና ዝርፊያ ዓላማው በሕዝቡ አንድነትና አብሮነቱ ላይ ሳንካ በመፍጠር የመንግሥትን የልማት አቅጣጫ ለማሰቀየር የተጸነሰሰ እኩይ ተግባር መሆኑ ይታወቃል።

እነዚህ የሕዝብን አብሮነትና የአገርን አንድነት የማይፈልጉ ሽብርተኞችን ገና ለገና የእኔ ጎሳ ናቸው  በሚል ወንጀል ሲፈጽሙ ፣ሰው ሲገድሉ፣ ያላግባብ ንብረት ሲያወድሙ፣ ቁሞ የሚአይ፣በለው እያለ ተባባሪ ሆኖ የሚአጠቃ፣ አለሞት ባይ ተጋዳይ ሁነው ራሳቸውን ለመከላከል ሲሞክሩ ደግሞ በመንግሥት ታጣቂዎችና ሹማምንት  እንዳአጥፊ ተቆጥረው እንድገድሉና እንዲሳደዱ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ድርጊት ቁርሾንና በደልን ከላይ ከላዩ እየጨመረና ጥላቻን እያባባሰ ከመሆዱ በፊት እጥፊዎቹን በቃቹሁ ማለት ይገባል።ከለዚያ ቆይቶ የሽግግሩን ወይም የዶክተር ዐቢይን መንግሥት በልቶ ፍጻሜው አገር በመበታተን ሊጠናቀቅ እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል።

ስለዚህ ዶከትር ዐቢይንና መንግሥታቸውን የምንጠይቀው በአሁኑ ሰዓት ለአንድነታችን ስጋትና ለአብሮነታችን ደንቃራ የሆኑ የአገር ጠላቶች ወያኔ፣የኦሮሞ ነጻ አውጭ ነኝ የሚለውና ከውጭ ጠላቶቻችን ዳረጎት የሚቸራቸው በውጭና በአገር ቤት የሚገኙ ጥቂት ባንዳዎች መሆናቸው ተለይቶ ታውቋል።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ወዳድና ሰላም ፈላጊ በመሆኑ ሽብር ፈጣሪዎች በአንድነቱና በአብሮነቱ ላይ የሚአካሄዱትን ሴራ መንግሥት በቁጥጥር ስር ያደርገዋል በሚል ዝምታን መርጦ በትግስት  ቢጠብቅም መንግሥት ግን ያሳያው ከመጠን ያለፍ ትግስትና ቸልተኝነት በሕዝብ ሕይወትና በአገር ንብረት ላይ በዙ ዋጋ አስከፍሎናል።

እነዚህ ሽብር ፈጣሪዎችን ሥረዓት ለማስያዝ መንግሥት ዝገምተኛ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደምና እየወስደ ያለውን ሕግን የማስከበር ሥራ አጠናክሮ ለቀጥልበት ይገባል። ይህም  ለሌሎች ትምህርት ሊሰጥ በሚችል መልኩ ፍትሕ በቶሎ እንዲበየን በማድረግ መንግሥትነቱን ሊአሳየን ይገባል።

 በሌላ በኩል መንግሥት አጋጣሚዎን ተጠቅሞ እየወሰደ ያለው  “ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን “ እንዲሉ ገና ለገና በሰላማዊ መንገድ ታግለው በድምጽ ሊአሸንፉኝ ይችላሉ ከሚል ስጋት ተነስቶ በአንዳንድ የድርጅት መሪዎችና የባልደራስ መሪን አቶ እስክንድር ነጋን ከሌሎች ሽብር ፈጣሪዎች ጋር በማዳመር  እንዲታሰሩ የተጠቀመበት ስልት የፍትሕ ሥረዓቱን ታአማኔነትና የመንግሥትን ቁቡልነት በከፈተኛ ደረጃ ከመሸርሸርና የመንግሥትን ተሸናፊነት ከመግለጽ በዘለለ የሚፈይደው አንዳችም ነገር የለም።

 የህ ሳይሆን የዞግ ፖለቲካ በፈጠረላቸው መደላደል ላይ ቁጥጥ በለው  የሥልጣን ጥማቸውን ለማሟላት ምክንያት እየፈለጉ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ሃይ ስለአልታባሉ አይደለም አገር ቤት  መጤና ስደተኛ በሆኑበት በውጭ አገርም የሚአካሄዱት መርን የለሽ፣ ያልተገራ ፣ኋላ ቀርና አሳፋሪ የሽብርተኝነት አካሄድ የገሪቱን ፀጥታ የሚአደፈርስና የልማት ሂደቷን የሚአደናቀፍ ብቻ ሳይሆን መሪዋን በሎቶ የአገሪቷንም ህልውና አድጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል መታወቅ አለበት።

ስለዚህ የአገር እንቅፈቶች የሆኑ ቡድኖችና ግለስቦችን እያባባሉና እያስታመሙ ከዓላማቸው ማዘናጋትና ማዳከም ይቻላል በሚል የተወሰደ ታስቢ እንኳ ቢኖር አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተፈጠሩ መልካም አግጣሚዎችን ተጠቅሞ ሽብርትኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል አገር የመታደግ ሥራ ለወስድ ይይገባል። ከለበለዚያ ልክ እንደ ሶቭየት ኅብረቱ መሪ ሚካኤል ገርቫቾብ በአሳዩት  ቸልተኝነትና ዳተኝነት የኅብረቱ አገራት እንደፈራረሱ ሁሉ ኢትዮጵያችንም የመፈራረስ ዕጣ ፈንታዋ እሩቅ ላይሆን ይችላል።

ዶክተር ዐቢይ የዘር ፖለቲካ በብዙ አገራት ተሞክሮ አልሠራም ። ሲጀመር “እኛና እነሱ የእኔ ይበልጣል ከአንተ” በሚል ዘይቤ የተቃኘ አስተዳደራዊ ሥረዓት እመራሉ ብሎ መነሳት እንኳን አገርን ቤተስብን ለማስተዳደር አዳጋች ነው። የአገር መሪ ሆኖ የአንድን የተውሰነ አካባቢ ጥቅም ማስጠበቅ በሎ ነገር አድሏዊ አሠራር ካልተወገደ በስተቀር ሁሉንም በአንድ ዐይን ማየት ያዳግታል። በዘር ፖለቲካ አበሳዋን ያየችውንና ብዙ ሽህ ዜጎቿን የአጣችው የሩዋንዳው መሪ ፖል ካጋሚ እንዲህ ብለዋል  “ብሔር ተኮር ፖለቲካ ለአፍሪካ መቃብሯን እንጅ እድገቷን አያፋጥንም “ እኔ ደግሞ እላለሁ መሪዋንም ይዞ ሥረአተ ፍጻሜዋም ይሆናል።

ስለዚህ እደግመዋለሁ ሞትና ሽረት አንዴ ነውና በአዋጅ የዘር ፖለቲካን ያስቁሙ። በባዶ ቤት የሚሰማ ጩህት ከፍተኛ ደምጽ እንዳለው ሁሉ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ የሚቀነቀነውን ጎሳ ተኮር ፖለቲካ በመጥላት ዝምታን በመምረጡ ጎጠኞች ድምጻቸው ከፍ ብሎ የሚሰማበት አጋጣሚ ስለተፈጠረ ብዙና ኃያል መስለው ቢታዩ ዕውነታው ግን በጣም አናሳና አቅመ ቢስ ናቸው።

መንግሥትን ተገዳዳሪ በመሆን ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት የባንዳ ልጆችና የሥልጣን ጥመኞች እፈራገጣለሁ ቢሉ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከመንግሥት ጎን ስለአለን አቅማቸውን አውቀው አርፈው አደብ ገዝተው ይቀማጣሉ።

ካለበዚያ መንግሥት በውስጡ በብዙ ሙስናና አቋም በአለማያዝ የሚቸገሩ ወላዋይ የትግል አጋር  ይዞ በበርካታ ውስብስብ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖማዊና ማሕበራዊ ችግሮች የተበተበች አገር እመራለሁና ሰላም አስፍናለሁ በሚል የሚደረግ ጉዞ የሕዝብን አሜነታ ካማሳጣቱና ድጋፊውን ጥርጣሪ ላይ ካመጣል ባለፈ  በሕይወት ከተርፉ እርሰውም ሆኖ ቤተሰበዎ አንደ ሚካኤል ገርቫቾብ እንኳን ይመሩት ይቀመጡበት አገር አልባ ለመሆነወት መተንበይ አያስፈልግም።

ስለዚህ እርሰዎ ጠንካራና ቆራጥ መሪ ይሁኑ እንጅ እልፍ አላፍ ኢትዮጵያን የምንወድ ዜጎቸዎ ከጎነወ አለን።  እርስዎ ከሚመሩት ብሔር እንኳ ጥቂት ያዙኝ ልቀቁኝ ከሚሉት በስተቀር ኢትዮጵያዊነቱን የሚወድ፣አብሮ ሠርቶ አብሮ መበልጸግ የሚፈልግ፣ ብዙ ሕዝብ አብርነወት አለን ። አወ ይቁረጡ ሕግ መንግስቱ ይቀየር !!!በዘርና በጎሳ መደራጀትም በአዋጅ ይከልከል!!!     

 

4 Comments

 1. ERE GORAW Zeraf !

  Under Abiy Ahmed’s road map, more false hope and fear is what is awaiting Ethiopia unless the “aristocrat nephtegna feudal” mobilizes towards self preservation on it’s own by not falling for the false hope and fear trap PM Abiy Ahmed’s Prosperity Doctrine arranged for Ethiopians. The recent attacks were so animalistic barbaric for the sole purpose of causing fear.
  A group plagued with fear does not mobilize for self preservation, instead fear makes a group rely on others who are in power for survival instead of the group relying on itself. Fear paralyzes human beings body , mind and soul.

  Prosperity gospel makes people have ‘false hope and fear’, says …

  ERE GORAW Zeraf !

 2. Fellow Ethiopians, we need a new constitutional order. Delay on this important and timely action is death for every one of us and the country. I think it is high time that the Ethiopian parliament convenes urgently, assesses the current situation in the country, and establishes a commission to draft a constitution /or amends the current one as appropriate, in a manner that would ensure the continued survival of Ethiopia as a country and equality, unity, and dignity of its people. This will also set the ground rule for the upcoming elections, ie; if we could ever live to elect and get elected in this country. My advice to Dr.Abiy and prosperity is hence, you have a one year Corona quarantine, please use it for good, i.e, to make a constitutional reform. This is not rocket science and is something doable. Next door Kenya has done it. If hell breaks loose, Mr. Prime Minister, you may never have such a historic opportunity again. Some people think wrongly that they will be able to live peacefully after killing and evicting from their homes their fellow countrymen and women. This is a false hope and an illusion, as in history it has always been relatively easy to win a war while it is extremely difficult is to win the peace. This is because it is not humanly possible to get robbed, looted, killed, displaced from your homes and families, and stay calm and let go. Look around and find out yourself, Syria, Libya, Yemen, Somalia, Iraq,… the list is long. If we can’t learn from the agonies of war and destruction around us and how it has reduced respected and proud citizens to beggars on the streets of neighboring countries and do something quickly, I doubt if we deserve to live as a nation. Action and not words will save Ethiopia, Mr. Prime Minister, please Act! If you don’t listen now, you may never be able to listen again, as we could meet in the rubbles of war and destruction as ordinary citizens on the streets of, Addis, Mekele, Bahirdar.or anywhere else in the mountains and valleys of the country, ( Asimba, Bale mountains, Ogaden, Dedebit?), .in defeat Trust me, it happened to EPRP, MESON, Derg, and now TPLF. I conclude with the following thesis of mine: If we Ethiopians have a common history we could perhaps agree on, I bet it is our History of MISSED OPPORTUNITIES. Rise to the occasion and prove me wrong Mr. Prime Minister! I challenge you.

 3. ግሩም ድንቅ አስተያየት ነው ። መንግሥት መስሚያ ጆሮ ኖሮት ቢሰማ መልካም ነበር ።
  የሰውን ልጅ ወደ አውሬነት የቀየረው ጎጥን መሰረት አድርጎ የተቀመጠው ህገመንግሥትና እሱን መመሪያው
  አድርጎ የተቀረጸው የጎሣ ፌደራሊዝም በህግ ካልታገደ በስተቀር መተላለቁ ይቀጥላል ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

free web page hit counter
free web page hit counter