ዳኛቸው ቢያድግልኝ biyadegelegnd@gmail.com ስለ አድዋው ድል የምንዘክረው አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ምስጢር በስጋና በነብሳቸን ውስጥ በመመላለሱ ነው። ይህ የአልገዛም ባይነታችንና ስለነጻነት የምንሰጠው ዋጋ ትልቅነት ነው በባዶ እግር፣ በጦርና ጋሻ፣ በውጅግራና በዲሞፍተር ታንክና አውሮፕላን እንድንደፍር ያደረገን። ነጻነት ማጣት የሞት እኩሌታ ስለሆነ ነው “ማን ይፈራል ሞት!!” የምንለው። ይህ በትምህርት፣ በልምድና የኑሮ ዘይቤ የተወሰደ ብቻ ሳይሆን የመጀመርያ የመሆን ጸጋ በእንበለ ዘራችን ውስጥ እንደ ጥበብ ተጠላልፎና ተቆላልፎ ስለተወራረሰ ነው። የኛን ሥሪት በሚዘውረው የሰው ዘር መነሻነታችን ሳቢያ ነው ለሌሎች ግፉአን ሁሉ ተምሳሌት የሆነው። ኢትዮጵያ የእውቀት ማፍለቂያ ማዕከል እንጂ የኩረጃ መዘክር አልነበረችምና ፈረንጆች እንቁልልጮሽ የሚሉንና ሌሎችን በገዙበት መንገድ እኛን የሚያሸንፉበት ጥበብ አልነበራቸውም። እንዲያውም ፈረንጆች ኢትዮጵያኖች ክፉኛ ይንቁናል